Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ማርና የማር ውጤቶችን ወደ አውሮፓ...
ማርና የማር ውጤቶችን ወደ አውሮፓ... Print E-mail
Sunday, 16 March 2008
ማርና የማር ውጤቶችን ወደ አውሮፓ ለመላክ የሚያስችል ሕጋዊ ማረጋገጫ ተገኘ

ኢትዮጵያ ማርና የማር ውጤቶችን ወደ አውሮፓ ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ማረጋገጫ ማግኘቷን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ በአውሮፓ ገበያ ተወዳዳሪ በመሆን አገሪቱን በውጭ ምንዛሬ ተጠቃሚ ከማድረግ በተጨማሪ በዘርፉ ለተሰማሩ አምራቾችና ላኪዎች የተሻለ የማር ምርት ለማምረት ጥራቱን የጠበቀ ማር ለመላክ አንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት በማርና የማር ውጤቶች ምርት የተሰማሩ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን በህጋዊ መንገድ ለመላክ ሳይችሉ መቆየታቸውን፣ በአሁኑ ሰዓትም ምርቱን ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት ለመላክ የሚያስችል አመቺ ሁኔታ በመፈጠሩ ምርቱን በህጋዊ መንገድ መላክ እንደሚችሉ፣ ወደ ውጭ ለመላክ ህጋዊ ማረጋገጫውን ለማግኘት እንዲቻል የኔዘርላንድ የልማት ፕሮግራም ያደረገው ቀና ትብብር ከፍተኛና የሚያስደስት መሆኑን ገልጿል፡፡

(ዋልታ)

መንግሥት የአንድ ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ተፈራረመ

የስፔን መንግሥት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞኖች የሚካሄዱ የምግብ ዋስትና ተግባሮችን የሚያግዝ የአንድ ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ መፈራረሙን ገለፁ፡፡

የስፔን መንግሥት ለዞኖቹ የምግብ ዋስትና ተግባሮች የሚውለውን የአንድ ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ የተፈራረመው ከፌደራል ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴርና ከዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ጋር መሆኑን፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለፕሮግራሙ ማስፈፀሚያ ሦስት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቁሳቁስና የሎጅስቲክስ አቅርቦቶችን እንደሚያሟላ ገልጿል፡፡

(ዋኢማ)

ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝ ዕርዳታ እንደተቋረጠባቸው ገለፁ

በየካ ክፍለ ከተማ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች፣ ሲደረግላቸው የነበረው የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ራሳቸውን የሚችሉበት መንገድ ባለመመቻቸቱ ለችግር መጋለጣቸውን ገለፁ፡፡ ክፍለ ከተማው በበኩሉ እርዳታው የተቋረጠው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር ቀጣይ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎቹ በክፍለ ከተማው በኩል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአንድ ዓመት ከሁለት ወር ያህል የስንዴ፣ ምስር፣ የፋፋና የዘይት ድጋፍ በየወሩ ሲያደርግላቸው መቆየቱን ተናግረው፣ እርዳታው ሲጀመር ከበሽታው እስከሚያገግሙና የሲዲ4 መጠናቸው እስኪስተካከል እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም እህሉ ቀደም ሲል ከሚሰጣቸው መጠን እየቀነሰ መምጣቱን ጠቁመው፣ ራሳቸውን የሚችሉበት ሁኔታ ሳይመቻች በመቋረጡ መቸገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

(አዲስ ልሳን መጋቢት 3 ቀን 2000)

ጋንሱ የሚዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው

ታዋቂው የቻይና ጋንሱ የሙዚቃ ቡድን ሚሌኒየምን ምክንያት በማድረግ ከመጋቢት 11 ቀን እስከ መጋቢት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ተገለፀ፡፡

የሙዚቃ ቡድኑ በኢትዮጵያ ተገኝቶ ትርዒቱን ማቅረቡ፣ ሚሌኒየሙ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን መላው ዓለም የሚያከብረው መሆኑን የሚያመለክት እንደሆነ፣ ቻይናና ኢትዮጵያ በመልካ ምድራዊ አቀማመጥ የተራራቁ ቢሆኑም በባህል የተቆራኙ ህዝቦች መሆናቸውን የሙዚቃ ቡድኑ የሚያቀርበው ዝግጅት ምስክር መሆኑን የቻይና ኤምባሲ የባህል ካውንስለር ስንግያንኩን ገልፀዋል፡፡

(አዲስ ዘመን መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም)
 
< Prev   Next >