| የልደት ቅኔ - ዘአምላኪየ |
|
| Tuesday, 08 January 2008 | |
|
ልደተ ክርስቶስ ባዕል አወፈዮሙ በቃና፣ ሀሊበ ለሙሴ ወለጴጥሮስ መና፣ እስመ ይገብር ምሕረት በዘቦ ክሂሎተ ኲሉ ብዕልና፡፡ ትርጉም የክርስቶስ ልደት/ባለጠጋ፣ ምስጢር ሃብታም ሰው ለአንዱ ወተት ለሌላውም ዳቦ እንደፍላጎቱ ሊሰጥ እንደሚችል፣ የክርስቶስ ልደት ለሙሴ ወተት ለጴጥሮስም ዳቦ ሰጣቸው፤ ማለት ውሃውን ወተት ድንጋዩንም ዳቦ አደረገ ማለት እንደሆነ በቅኔው ተመስጥሮአል፡፡ ታሪክ ሙሴ ማለት በጥንት የግብፃውያን ቋንቋ ውሃ ወይም ከውሃ የተገኘ ማለት ነው /ዘፀአ. 2፡10/፡፡ ጴጥሮስ ማለትም በግሪክ ቋንቋ ድንጋይ ማለት ነው /ማቴ. 16፡18/፡፡ ክርስቶስ በተወለደበት እለት የወንዞች ውሃ ወተት፣ ወይንና መአር፣ ድንጋዮችም ዳቦ ሆነዋል፡፡ እንጨቶችም ሁሉ ጣፋጭ ፍሬ አፍርተዋል ይባላል /ዝማሬ ዘልደት/፡፡ /የግእዝ ቅኔያት የስነ ጥበብ ቅርስ 3ኛ፣ 1995/
|
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |