Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow “በወርቅ ማጭበርበር የለሁበትም፣...
“በወርቅ ማጭበርበር የለሁበትም፣... Print E-mail
Sunday, 16 March 2008
Image“በወርቅ ማጭበርበር የለሁበትም፣ ብር አላተምኩም አልታሰርኩም”

አቶ ሳቢር አርጋው
የአልሳም ባለቤት

ከወርቅ ማጭበርበር ጋር ምንም ንክኪ እንደሌላቸው፣ የተጭበረበረ ብር በማሳተም ወንጀል እንደሌሉበትና በየትኛውም ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረው እንዳልታሰሩ የአልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሊቀመንበርና ባለንብረት አቶ ሳቢር አርጋው ገለፁ፡፡
አቶ ሳቢር ይህንን የገለፁት በወርቅ ማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ መታሰራቸውን ተከትሎ እሳቸውም “ታስረዋል፣ ከአገር ጠፍተዋል፣ በህይወታቸው ላይ አደጋ ደርሷል፣ በሳሙና ካርቶን ብር እያሳተሙ ያሰራጫሉ . . . “ የሚል ወሬ በስፋት መሰራጨቱ በስራቸውና በቤተሰባቸው ላይ ተፅዕኖ እያደረገ መሆኑን ህዝብና መንግሥት እንዲያውቅላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

“ወንድም የለኝም” ያሉት አቶ ሳቢር የእሳቸው ወንድም የሆነ ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ታስሯል መባሉንም “የፈጠራ ወሬ” ይሉታል፡፡ አያይዘውም “በወርቅ የለሁበትም፣ ብር አላሳትምም፣ አልታሰርኩም” በማለት ህዝብና መንግሥት ሊጠብቃቸውና ከጀርባቸው እየተሰራ ያለውን እንዲዋጋላቸው ጠይቀዋል፡፡

“ከአገር ወጥተው አንድ ወር ቆይተዋል” መባላቸውን ሲሰሙ መገረማቸውን የገለፁት አቶ ሳቢር “እንግሊዝ አገር ለስራ ሄጄ ወንጀለኛ እየተባልኩ ስሜ ሲነሳ በሦስተኛው ቀን ሥራዬን ትቼ ወደ አገሬ ተመለስኩ” ብለዋል፡፡

በእሳቸው ላይ እንዲህ ዓይነት ወሬ ሊወራ የቻለው በምን ምክንያት እንደሆነ ጠይቀው በትክክል የሚያውቁት ነገር እንደሌለ፣ ነገር ግን ከመርካቶ በትንሽ ንግድ የተጀመረ ሥራ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ የሚደሰት እንዳለ የሚከፋ ጠላትም ስለማይጠፋ የተከፉ ያደረጉት እንደሆነ አቶ ሳቢር ተናግረዋል፡፡ “ሁሉንም ግን” ይላሉ አቶ ሳቢር “ሁሉንም ጊዜ ይፋ ያወጣዋል፡፡ እኔ ግን ወደ ህግ እሄዳለሁ” ብለዋል፡፡

የቢ-29 ሳሙና ምርት ለምን ከገበያ ጠፋ በሚል ለተጠየቁት የሳሙና ፋብሪካው 44 በመቶ የእሳቸው 56 በመቶ የኢንዶኔዥያ ባለሀብት መሆኑን አቶ ሳቢር ጠቁመው፤ የምርት እጥረት ሊከሰት የቻለው ጥሬ እቃ የሚያቀርበው ኢንዶኔዥያዊው የንግድ ሽሪካቸው የአቅርቦት መጠኑን በመቀነሱ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

“ችግሩን አስቀድሜ ለንግድና ኢንዱስትሪ አሳውቄያለሁ” የሚሉት የአልሳም ባለንብረት በአሁኑ ወቅት የቢ-29 ሳሙና ለጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ) በአራት ብር ገደማ እያስረከቡ መሆናቸውንና ዋጋውን ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ከዋጋ መናር ጋር በተያያዘ ካለፉት ሰባት ወር ጀምሮ ከመንግሥት ጋር በመተባበር እየሰሩ እንደሆነ የአልሳም ባለንብረት ገልፀዋል፡፡ እንደ ባለንብረቱ ገለፃ በተፈጠረው የዋጋ መናር ሳቢያ “የመሰረታዊ አላቂ እቃዎች አቅርቦት እንዴት መሻሻል አለበት?” በሚለው ጉዳይ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ዋጋን ለማረጋጋት የሰሩት ሥራ ያስቆጣቸው ግለሰቦች የስም ማጥፋት እያካሄዱባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

አልሳም ሕብረተሰቡ ያጋጠመውን የዋጋ መናርና የኑሮ ውድነት በመረዳት ከመንግሥትና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር አጥብቆ እንደሚሰራ አቶ ሳቢር ተናግረዋል፡፡ በድርጅቱና በራሳቸው ላይ የስም ማጥፋት የሚያራምዱትን በስራና በህግ እንደሚያሸንፉም ተናግረዋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >