| ብዥታው ተወግዷል |
|
|
| Sunday, 16 March 2008 | |
|
የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ገጠርና ከተማ ከ10000 በላይ ጠንካራ አባላትን ለማፍራት ችሏል፡፡ ሐብሊ ሕዝባዊ ድርጅትነቱን የሚያረጋግጥበት በክልሉ መሠረታዊ ድርጅት ተወክለው የሚመጡትን ጠንካራ አባላቱን በአግባቡና በደንቡ መሠረት በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ መወከልና ማቀፍ ሲችል ብቻ ነው፡፡
በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 18 የሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ የመተርጎም ሥልጣን በተሰጠው መሠረት ይህንን ውክልና እንደ መብት እንጂ እንደ ኮታ ባለመመልከቱ በሐረር ለሚገኙና ከመሠረታዊ ድርጅቶች ተወክለው ለሚመጡ የድርጅቱ ጠንካራ ታጋዮች በድርጅቱ የሚታገሉበትን መድረክ በጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ ቀደም ከነበረው 15ዐ የአባላት ውክልና በተጨማሪ ከክልሉ ሦስት የገጠር ቀበሌ አስተዳደሮች (ወረዳዎች) ተወክለው ለሚመጡ ለየእያንዳንዳቸው አሥር አባላት በድምሩ ሠላሳ እና ከጥንታዊው የሐረር ከተማ ውጪ ለሚገኙ አራት የከተማ ቀበሌ አስተዳደሮች (ወረዳዎች) ለየእያንዳንዳቸው 1ዐ በድምሩ 4ዐ አባላት በጥቅሉ 7ዐ ተጨማሪ የድርጅቱ ጠንካራ አባላት ለመጡበት አካባቢ በጠቅላላ ጉባዔ አባልነት እንዲወከሉ በተጨማሪም ለፈዲስ፣ ለኮምቦልቻ፣ ለሐረማያ፣ ለደደርና ለጭሮ ለእያንዳንዳቸውዱ 1ዐ የጉባዔ አባላት መተዳደሪያው ደንብ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላላ ጉባዔውን የአባላት ብዛት በ12ዐ ከፍ እንዲል በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴው በአብላጫ ድምፅ ለመወሰን ችሏል፡፡ አዲስ ነገር ወይም ለውጥ ምንጊዜም ቢሆን ሁሉም አካል በአንዴ አይቀበለውም፡፡ በዚህም መሠረት የካቲት 23 እና የካቲት 30/2000 በወጣው የአማርኛ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በድርጅታችን ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ እንደተፈጠረ ስማቸው እንዲጠቀስ ካልፈለጉ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የድርጅቱ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባል ተገልጿል የሚል ዜና ወጥቷል፡፡ ጋዜጣው ሚዛን ላይ ሳያስቀምጥ የግለሰቦችን ፍላጎትና ማመልከቻ ተቀብሎ ማስተናገዱ ጋዜጣው የነበረውን ታዋቂነትና ተአማኒነት የሚያሳጣው ይሆናል፡፡ ሐብሊ ሕዝባዊ ድርጅትነቱን ለማጠናከር በቅርቡ በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአብላጫ ድምፅ የተወሰነው ውሳኔ ይበልጥ እንዲብራራላቸው ከምንጩ ለማረጋገጥ የፈለጉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የድርጅቱ አባላትና የብሔረሰቡ ሽማግሌዎች ተሰባስበው ሐረር ከተማ በመምጣት ጥያቄያቸውን ለድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አካላት አቅርበው በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ ማግኘታቸውንና የነበራቸው ብዥታም እንደተወገደ ተማምነው ወደ መጡበት አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደ ዘገበው ተፈጠረ የተባለው ውዝግብ አዲስ አበባ የሚገኙትን የድርጅቱ አባላት የማይወክል መሆኑን እየገለፅን በአንዳንድ ግለሰቦች የግል ጥቅምና ፍላጎት ሐብሊ የጀመረውን ለውጥ ባለመቀበል የመነጨ በመሆኑ ..ሌባ እናት ልጇን አታምንም.. ከማለት በስተቀር የምንጨምረው አይኖረንም፡፡ ድርጅቱ እንኳን ከአባላቱ ከማንኛውም ግለሰብና አካላት ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሩን ክፍት በማድረግ የዴሞክራሲን ግንባታ ይበልጥ ለማጠናከር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ የሐብሊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ከሐረር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |