| የአዲስ አበባ ናዝሬት አዲሱ የመንገድ... |
|
|
| Sunday, 16 March 2008 | |
|
የአዲስ አበባ ናዝሬት አዲሱ የመንገድ ግንባታ ወጪ 4.5 ቢሊዮን ብር ተገመተ
ከአዲስ አበባ ናዝሬት ሊሰራ የታቀደው አዲሱ የመንገድ ሥራ 500 ሚሊዮን ዶላር (4.5 ቢሊዮን ብር) ሊፈጅ እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛኢድ ወልገብርኤል እንደገለፁት፣ ከአዲስ አበባ ናዝሬት ድረስ ሊገነባ የታቀደው አዲስ መንገድ አሁን ካለው ተለይቶ የሚሰራ ስለሆነ ወጪው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ የመንገዱ ዲዛይን በአንድ የደቡብ አፍሪካ አማካሪነት እየተሠራ በመሆኑና ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ትክክለኛ ዋጋውን መናገር ባይቻልም በቅድመ ጥናቱ ግምት መሰረት ወጪው ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ የዲዛይን ስራው በቀጣዩ ሦስራ ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህን መንገድ ግንባታ ወጪም በተወሰነ ደረጃ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል፡፡ ቀሪውን ወጪ ደግሞ በፕሮጀክተሩና ፋይናንስ ለማድረግ ፍላጎት ያሳዬ በርካታ የልማት አጋሮች እንዳሉና ከአንዳንዶቹ ጋርም በመነጋገር ላይ እንደሆኑ አቶ ዛኢድ አመልክተዋል፡፡ አሁን የሚጠበቀው የዲዛይኑ መጠናቀቅና የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ማሰባሰብ ሲሆን ይህ ሥራ እንደተጠናቀቀ ወደ ሥራ እንዲገባ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም የአቶ ዛኢድ ገለፃ ያስረዳል፡፡ የመንገዱ ዲዛይን እየተሰራ ያለው በአንድ ጊዜ ስምንት ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ ተደርጎ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ዲዛይን መሰረት በአንዴ ስምንት ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግደውን መንገድ ለመገንባት ሊገኝ የሚችለው የፋይናንስ መጠን የሚወስነው ሲሆን በአንዴ ስድስት ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ የሚችለው መንገድ ግን የማይቀር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ መንገዱ ከአዲስ አበባ ናዝሬት ያለውን የትራፊክ ፍሰት ከማቃለሉ በተጨማሪ ሁለቱን ከተሞች የሚያገናኙት መንገዶች ቁጥር ሁለት እንዲሆንና በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ርቀት በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች እንዲቀነስ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡ አዲሱ መንገድ አሁን ካለው መንገድ ጋር የማይገናኝና በመንገዱ ላይ የሚሽከረከሩ መኪኖችም በክፍያ እንደሚጠቀሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |