| ራይስ ከሊቢያ ዲፕሎማት ጋር ተወያዩ |
|
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንዳሊዝ ራይስ ከሊቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አብዱራህማን ሸጋም ጋር በዋሽንግተን ውይይት ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
በዋሽንግተን በተደረገው በዚሁ ውይይት ሊቢያ የሰብዓዊ መብት እንድታከብር ኮንደሊዝ ራይዝ አሳስበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሊቢያ መንግሥት በአሸባሪዎች ጥቃት አደጋ የደረሰባቸው ወገኖች የሚያሰሙትን ቅሬታ መፍታት እንዳለበት አክለው አሳስበዋል፡፡ የአሜሪካና የሊቢያ መንግሥት ግንኙነት እ.ኤ.አ ከ2003 ወዲህ እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ በዋሽንግተን የተደረገው ውይይት አንድ ሰዓት ገደማ የፈጀ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ በአሜሪካና በሊቢያ መካከል በከፍተኛ ባለስልጣናት በኩል ውይይት ሲደረግ ይህ ከሰላሳ ስድስት ዓመት ወዲህ የመጀመሪያው እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ቻይና ለዝንቧቡዌ እርዳታ ሰጠች ቻይና አምስት ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታ ለዝንቧቡዌ መንግሥት መስጠቷን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ በዝንቧቡዌ የቻይና አምባሳደር እርዳታውን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት እ.ኤ.አ በ2008 ወደ አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ገልፀዋል፡፡ በዝንቧቡዌ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ረከሀገሪቱ ሕዝቦች ሀያ አምስት በመቶ የሚሆኑትሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ አቅርቦት እንደሚኖሩ ተዘግቧል፡፡ በሀገሪቱ በተደረገው የምግብ ምርት ጥናት አንድ ሚሊዮን ቶን የምግብ እጥረት እንዳለ ተገል..ል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም በሀገሪቱ ባለው የምግብ እጥረት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች በምግብ እጥረት አጠያያቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገል..ል፡፡ በአይዋ የፕሬዚዳንታዊ እጩነት ውድድር ሁካቢና ኦባማ አሸነፉ ሚክ ሁካቢና በራክ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2008 በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ እጩ ሆነው ለመቅረብ እየተደረገ ባለው ውድድር በአይዋ ማሸነፋቸውን ቪኦኤ ዘገበ፡፡ በአይዋ ከሪብሊካን ፓርቲ ሚስተር ሚክ ሁካቢ ሚቲ ሮሚኒን ሲያሸንፉ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ሚስተር ባራክ ኦባማ፣ ጆን ኤድዋርድንና ሂላሪ ክሊንተንን አሸንፈዋል፡፡ በአይዋ ውጤት መሠረት ከዴሞክራቲክ ባራክ ኦባማ 37.6 በመቶ ጆን ኤድዋርድስ 29.7 በመቶ፣ ሂላሪ ክሊንተን 29.5 በመቶ፣ እንዲሁም ቢል ሪቻርድሰን 21 በመቶ ውጤት አግኝተዋል፡፡ ዘጠና ስድስት በመቶ በተጠናቀቀው የሪፐፕሊካን ውድድር ሚክ ሁካቢ 34.3 በመቶ፣ ሚቲ ሮሚኒ 25.3 በመቶ፣ ፍሬድ ቶምሰን 13.4 በመቶ አግኝተዋል፡፡ ሙሸራፍ በቡቶ ግድያ እጃቸው እንደሌለ አስታወቁ የፓኪስታኑ ፕሬዚዳንት ፔርቬዝ ሙሻራፍ በቀድሞዋ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናዚር ቡቶ ግድያ ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሻራፍ እኔ ከተማረና ከሰለጠነ ቤተሰብ የተገኘሁ ነኝ፤ ቤተሰቤ በመርህና በስነ ምግባር ያምናል፤ ሰዎችን በመግደል ያሳደገኝ ቤተሰብ አያምንም ሲሉ በግድያው ውስጥ አለመሳተፋቸውን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ግድያውን አስመልክቶ እየተደረገ ያለው የማጣራት ሥራ ያላረካቸው መሆኑን መግለፃቸውን የሲ.ኤን.ኤን ዘገባ አመልክቷል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |