| ኢንተርአፍሪካ ግሩፕ የፓርቲዎች... |
|
|
| Wednesday, 19 March 2008 | |
|
ኢንተርአፍሪካ ግሩፕ የፓርቲዎች የክርክር መድረክ አዘጋጀ
ኢንተርአፍሪካ ግሩፕ በቀጣይ ወር በሚካሄደው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ላይ ለሚሳተፉ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ ኢንተርአፍሪካ ለሪፖርተር ጋዜጣ በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ከመጋቢት 13 እስከ 28 ቀን 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በባህርዳር፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በአዋሳ፣ በጊምቢ፣ በወልዲያ፣ በዱብቲ፣ በአዳማ፣ በአዋሳ፣ በሆሳዕና፣ በወላይታ ሶዶ እና በአዲስ አበባ ከተማ የክርክር መድረክን እንዳዘጋጀ ገልጾ ይህንኑ የሚያከናውኑ ሶስት ቡድኖች ማዋቀሩን፣ አወያዮቹም ነፃና ገለልተኛ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ግለሰቦች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ በዚሁ የክርክር መድረክ ላይ ይሳተፋሉ ብሎ ድርጅቱ የዘረዘራቸው ፓርቲዎች ኢዴአፓ መድኅን፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ሐብሊ፣ ኢዴኃኅ፣ ሶሕዴፓ፣ ኦብኮ፣ ኦፌዴን፣ አብዴፓ፣ አርዱፍ፣ ኦነግ፣ ገሥአፓ፣ ደኢህዴን፣ ወህዴግ፣ መኢብን፣ ኢዲዩ፣ ቅንጅት ናቸው፡፡ ሆኖም የፓርቲዎቹ ክርክር ቀጥታ የሚዲያ ሽፋን ስለማግኘት ወይም ያለማግኘቱ ጉዳይ ላይ ኢንተርአፍሪካ በመግለጫው ላይ የጠቀሰው ነገር የለም፡፡ ኢንተርአፍሪካ ግሩፕ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲጠናከሩ እና በተለይ በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የውይይትና ክርክር ባህል እንዲያዳብሩ ለመርዳት ሲጥር የቆየ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑ ይታወሳል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |