Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow በጥቁር ገበያ የውጪ ገንዘብ...
በጥቁር ገበያ የውጪ ገንዘብ... Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
በጥቁር ገበያ የውጪ ገንዘብ ሲመነዝሩ የተያዙ በዋስ ተፈቱ

የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የጥቁር ገበያ መንዛሪዎች በትላንትናው እለት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዋስ ተለቀቁ፡፡ በፖሊስ ለኤግዚቢትነት ከያዘው የውጪ ምንዛሪ ከዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ ቀጥሎ የቻይና ገንዘብ (ሬሚዋቢ) በቁጥሩ ከፍተኛ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ..የተጠና.. ባለው ዘመቻ ከሃያ አምስት የጥቁር ገበያ መመንዘሪያ ሱቆች 35 ተጠርጣሪዎችን መያዙ አይዘነጋም፡፡

የፌደራል ፖሊስ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፀው የተጠርጣሪዎቹ ድርጊት በወንጀል የሚያስከስስ በመሆኑ የክሱ ሂደት ይቀጥላል፡፡

በተያያዘ ዜና ድንገት በተደረገ አሰሳ ፖሊስ ከያዘው የውጭ ገንዘቦች ማለትም ዶላር፣ ዩሮና ፓውንድ በተጨማሪ የቻይና፣ የኳታር፣ የታይላንድና የቱርክ ገንዘቦች መያዛቸውን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

የቻይና ገንዘብ ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣው በብዛት ከቻይና ዕቃዎችን የሚያስመጡ ነጋዴዎች በመበራከታቸው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የቻይና ዜግነት ያላቸው ከአነስተኛ የሸቀጥ ሥራ ጀምሮ በከፍተኛ የንግድ ሥራ እየተሰማሩ መምጣታቸው የቻይና ገንዘብ በጥቁር ገበያ እንዲፈለግ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ፖሊስ ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ባደረገው ድንገተኛ አሰሳ ከጥቁር ገበያ ከ1.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መያዙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >