Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow አገራዊ የዋጋ ግሽበት 18 በመቶ ደረሰ
አገራዊ የዋጋ ግሽበት 18 በመቶ ደረሰ Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በየካቲት 2000 ዓ.ም 18 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ አመለከተ፡፡
በኢንዴክሱ መሠረት በየካቲት ወር 2000 ዓ.ም የተመዘገበው አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 18 በመቶ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከታየው 13.5 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነፃፀር በ4.5 ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በየካቲት ወር 2000 ዓ.ም የተመዘገበው አገራዊ የምግብ ዋጋ ግሽበት 23.7 በመቶ መሆኑ ታውቋል፡፡ በየካቲት ወር 10.5 በመቶ አገራዊ ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ተከስቷል፡፡

ኢንዴክሱ በየካቲት ወር 2000 ዓ.ም የተመዘገበው 23.7 በመቶ የምግብ የዋጋ ግሽበት ከየካቲት 1999 በጀት አመት ከታየው 14.5 ጋር ሲነፃፀር 9.2 ጭማሪ ማሳየቱን አመላክቷል፡፡

ለምግብ ዋጋ ግሽበት በበርበሬ ዋጋ ላይ የታየው የዋጋ ንረት በዋነኝነት ተጠቃሽ ሆኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የየካቲት ወር 2000 ዓ.ም የአገር አቀፍ ጠቅላላ የችርቻሮ ዋጋ ኢንዴክስ ከየካቲት ወር 1999 ዓ.ም ጠቅላላ ኢንዴክስ ጋር ሲነፃፀር 22.9 ከመቶ ማደጉ ታውቋል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >