| ኑሮ ከተወደደ ሳሎንም አይሞቅም |
|
|
| Wednesday, 19 March 2008 | |
ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል፤ እያልን ስንቴ ራሳችንን እያፅናናንና ራሳችን ለራሳችን ማስተዛዘኛ እያሰማን እንኑር?ኑሮ ከተወደደ አይደለም መቃብር፣ ሳሎንም አይሞቅም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የዓለምን የኑሮ ሁኔታ እያናጋው ነው፡፡ ትራንስፖርትን ብቻ ሳይሆን ከፔትሮሊየም የሚሰሩ በርካታ የምርት ውጤቶች፣ ከነዳጅ የሚሰሩ በርካታ ኢንዱስትሪዎች ስላሉ ነው፡፡ በነዳጅ የሚሰራው የሲሚንቶ ፋብሪካችን በከሰል እንደሰራ ሆኖ ካልተቀየረ የሲሚንቶ ዋጋ ሲንር ይኖራል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመናሩ በአገራችን የኑሮ ውድነትን አስከትሏል፡፡ ሆኖም ግን በአገራችን ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት ሁሉ ከነዳጅ ዋጋ ንረት ጋር አይያያዝም፡፡ መንግሥት የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ሊሰራቸው የሚገቡ ተግባራት አሉ፡፡ መጀመሪያ ከዓለም የነዳጅ ዋጋ ንረት ጋር ተያይዘው በአገራችን የሚከሰቱት የኑሮ ውድነቶችን በተገቢ ጥረት አስደግፎ ለሕዝብ ግልፅ ያድርግ፡፡ በቁጥጥር ማነስ ወይም በነጋዴዎች ስግብግብነት ብቻ ሳይሆን ተወደደም ተጠላም በዓለም የሚታይ ችግር በእኛ አገርም መታየቱ በግልፅ ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡ ሕዝብም ግልፅ ይሆንለታል፡፡ መንግሥትም ከአቅሙ በላይ ነውና አይወቀስበትም፡፡ ሁለተኛ፣ ራሱ መንግሥት በፖሊሲው ምክንያት የተከሰቱ የኑሮ ውድነቶችን ይመርመር፡፡ ሱር ታክስ ያስከተለው የኑሮ ውድነት እንዳለም በግልፅ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ በቅንጦት እቃዎች ሱር ታክስ ቢጣል ተቃውሞ የለንም፡፡ ገቢው ለልማት ይፈለጋልና፡፡ ነገር ግን የቅንጦት እቃ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ይሁን፡፡ ይለይ፡፡ በኒዶ ወተት ላይ ሱር ታክስ ተጨምሯል፡፡ ኒዶ ወተት የቅንጦት ዕቃ አለመሆኑን ለመረዳት ግን ባለሙያ መሆንን አይጠይቅም፡፡ መንግሥት የሱር ታክስ ፖሊሲውን ይፈትሽ፡፡ ሦስተኛ፣ ስግብግብ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠርና ሕዝብን ከጉዳት ለመከላከል በአስፈላጊ ምርቶች ላይ የዋጋ ተመን ያስቀምጥ፡፡ ነፃ ገበያ ማለት እንዳለ በሁሉም ነገር ላይ ዋጋ አለመተመን ማለት አይደለም፡፡ መሠረታዊ በሆኑ ፍጆታዎች ላይ ዋጋ መተመን ነፃ ገበያን አይፃረርምና መንግሥት ይህንን ያድርግ፡፡ ገበያ ይወስነው ተብሎ የቤንዚን ዋጋ ለነዳጅ ማደያዎች አልተተወም፡፡ መንግሥት ወሰን አስቀምጧል፡፡ በሌሎች ተፈላጊ ዕቃዎች ላይም እንደዚያ ይደረግ፡፡ ከዚያ ዋጋ በላይ የሸጠ ይቀጣ፡፡ አራተኛ፣ ምርት ይጨመር፡፡ ምርት ሲጨምር ዋጋ ይቀንሳል፡፡ የኑሮ ውድነትን ይከላከላል፡፡ የበርበሬ፣ የጤፍ፣ የስንዴ ምርት መጨመር ይቻላል፡፡ አሰራርና ፖሊሲን ማስተካከል ነው፡፡ ማበረታቻ እየሰጡ ምርት ማሳደግ ለኢትዮጵያውያን የሚሳነን እርምጃ መሆን የለበትም፡፡ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በግሉ ዘርፍ የማይመረቱ ከሆነ መንግሥት ይጀምራቸው፡፡ ከትናንሽ የገበሬ መሬቶች በተጨማሪ ሰፋፊ ኮሜርሻል እርሻዎችም ይኑሩ፣ ይቀጥሉ፣ ይበረታቱ፡፡ አምስተኛ፣ የሸማቾች ማኅበር እንዲፈጠሩና እንዲጠነክሩ መንግሥት ድጋፍ ያድርግ፡፡ መንግሥት ብቻውን ዋጋ መቆጣጠር አይችልም፡፡ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡፡ የኅብረተሰቡን ድጋፍ ማግኘት የሚቻለውም በተናጠል ሳይሆን በተደራጀ መልኩ ሲሆን ነው፡፡ ስድስተኛ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ቅድመ ዝግጅትና ትንበያ ይደረግ፡፡ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጀንሲ የተባለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ስለሆነ መንግሥት እየተዘጋጀ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር ሲታይ ግን ሊደረግ የሚገባው ቅድመ ዝግጅት ከአንድ መሥሪያ ቤት ኃላፊነት በላይ ነው፡፡ በርበሬ ጠፋ፣ ጤፍ አነሰ፤ እየተባለ ኅብረተሰቡ መደናገጥ የለበትም፡፡ ሰባተኛ፣ ሥራ መፍጠርና ገቢ መጨመር ሌላው መወሰድ ያለበት እርምጃ ነው፡፡ ሥራ አጡም ሥራ ካገኘ፣ ባለአነስተኛ ገቢም ገቢው ከጨመረ በተሳካ ሁኔታ ሊቋቋመው ይችላል፡፡ ሳሎን ሊሞቅ የሚችልበት አንዱ መንገድም ገቢን በማሳደግ ነውና በድህነት ላይም ከማጭበርበር ውጭ የሆነ ገቢ ሊጨምር ይገባል፡፡ እነዚህ የጠቃቀስናቸው ነጥቦች አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ሁኔታው ይበልጥ እንድናስብበትና እንድንከታተለው የሚያስገድደን ግን የበልግ ሁኔታ ነው፡፡ እስከአሁን ድረስ መታወቅ የነበረበት የበልግ ዝናብ አልታየም፡፡ የበልግ ዝናብ ካልዘነበ ለእንስሳት የሚሆን ሳርና ለሰው የሚሆን ምግብ ይቀንሳል፡፡ ለተጨማሪ የኑሮ ውድነት እንዳረጋለን፡፡ ስለዚህ በልጉ ቀይ ካርድ እያሳየ ስለሆነ ከወዲሁ አስፈላጊ ዝግጅት ይደረግ፡፡ ፖሊሲዎች ተአምር ይሰራሉ፡፡ በትክክለኛ ፖሊሲና ተግባር ኑሮአችንን አሻሽለን፣ አስተካክለንና ተቆጣጥረን ሳሎናችንን ማሟሟቅ እንችላለን፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
የሰሜን ኮሪያው ዜጋ ቴሌን በማጭበርበር ታሰረ
በአሰግድ ተፈራ
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሠሜን ኮሪያ ዜጋ የሆነ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲገለፅ ግለሰቡ በሕገ ወጥ መንገድ የራሱን ሰርቨር ተክሎ ወደ አሜሪካና አውሮፓ የስልክ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
የሃቀኛ ተፎካካሪ ቤት ተዘግቶ ያድራል!
በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ኃያልነት ፈተና
ደቡብ አፍሪካ ለሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ ልትሰጥ ነው
የደቡብ አፍሪካ መንግስት በአቢይ ክልል ለሚገኙ ሱዳናውያኖች 40 ቶን የሚመዝን ድንኳን፣ ብርድልብስ፣ የወባ መከላከያ አጎበር፣ ፍራሽ፣ ምግብና ልብሶች እርዳታ ሊሰጥ ነው፡፡
የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ጉዳቱና ጥቅሙ
"በእኛ አገር እውቀት እንደ...
"በእኛ አገር እውቀት እንደ ገንዘብ እየተቆጠረ አይደለም"
ካፒቴን መኮንን ሃብት ይመር
ካፒቴን መኮንን ሃብት ይመር ኢኮ የሁሉነሽ የጋዝ ምድጃዎችና የእርሻ መሣሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ኢኮ የሁሉነሽ የነጭ ጋዝ ምድጃን በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡
የሚቆጠብ ባይኖርም ይቆጠባል
በምሕረት አስቻለው
ለረዥም ዓመታት ከክፍለ ሀገር ቅቤ፣ አይብና እህል እያመጡ ይነግዱ ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እቃዎች ስለተወደዱባቸው ወደ ጉሊት ችርቻሮ ንግድ መግባታቸውን ይናገራሉ ወ/ሮ ፋንቱ ብዙነህ፡
የተራቀቁ ሌቦች ለቤጂንግ...
የተራቀቁ ሌቦች ለቤጂንግ ኦሊምፒክ አስግተዋል
የቤጂንግ ኦሊምፒክ በኤሌክትሮኒክስ ወንጀል ለሚፈጽሙ ሰዎች የተጋለጠ መሆኑን የደህንነት ድርጅቶች ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዲያስፖራው በአገሩ ልማት...
የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ
በምሕረት አስቻለው
"ማጥናት ለእኔ እንደመዝናናት ነው፡፡ እለት በዕለት የተማርኩትን አጠናለሁ፡፡ ደብተሬ ጠርዝ ላይ ዋና ዋና ነጥቡን እጽፋለሁ፡፡ ቋሚ ጓደኛዬ የምለው በግቢ ውስጥ የለኝም፡፡ በአጋጣሚ ካገኘሁት ተማሪ ጋር እሆናለሁ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት በትምህርትና በጥናት ሁኔታ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ የዚያ ዓይነት ግንኙነት የለኝም፡፡ ይህ ለውጤቴ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል" ያለችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ነጥብ በማምጣት ከሥነ ኤዱኬሽን ኮሌጅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ወጣት ማስተዋል መኮንን ነች፡፡
ኦሊምፒክን በቲቪ፣ ኢ ቲቪን በኦሊምፒክ
ከበደ አስቻለው
የኦሎምፒክ ጨዋታዎችና ውድድሮች በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን መሰራጨት እስኪጀመር ድረስ የኦሊምፒክ ንቅናቄ ከአርባ ዓመት በላይ እድሜ አስቆጥሯል፡፡ የመጀመሪያው የ1896 የአቴንስ የኦሊምፒክስ ጨዋታዎች የተዘገቡትና ዜናቸው የተሰማው በጋዜጣና በጋዜጦች ብቻ ነበር፡፡ የወቅቱ ሪከርዶች እንደሚያመላክቱት ለአቴንስ ውድድር እውቅና ያገኙት (አክሬዲት የተደረጉት) ጋዜጠኞች በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ነበሩ፡፡
ፍርድ ቤት ምን ያህል ይናገራል? ያናግራልስ?
የመንግሥት መሠረታዊና ዋና ዋና ሥልጣኖች የህግ አውጭነት፣ የህግ አስፈጻሚነት እና የዳኝነት ስልጣኖች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ አንዱን የመንግሥት ዓይነት ከሌላው የመንግሥት ዓይነት የሚለየው የተጠቀሱት መሠረታዊ ስልጣኖች ተጠቅልለው፣ ጨርሰውና አካተው በአንድ ሉዓላዊ የሥልጣን አካል እጅ መግባታቸው ወይም መውደቃቸው፣ አለዚያም እነዚህ የመንግሥት መሰረታዊ ሥልጣኖች ሊለያዩና ለየቅልና እኩል ለሆኑ ሦስት የሥልጣን አካላት መደላደላቸው ነው፡፡ እንደ አሜሪካ ባለ ኘሬዚዳንታዊ የመንግሥት ሥርዓት የመንግሥት የህግ አውጭዎች፣ የህግ አስፈጻሚነት የዳኝነት ሥልጣን እንደቅደም ተከተላቸው ለፓርላማ፣ ለኘሬዚዳንቱ (እና ለካቢኔው) እንዲሁም ለፍርድ በት የተሰጡ በመሆናቸው ከዚህ በመነጨ አሰራር በተለይም የዳኝነቱ አካል ሦስተኛው ዘርፍ (ዘ ሰርድ ብራንች) ይባላል፡፡
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ከወረቀት ዘሏልን?
በሠለሞን ጎሹ
በድምቀት እየተካሄደ ቆይቶ ዛሬ የሚጠናቀቀው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ከመጀመሩ በፊት ቻይና ለአካባቢ ጥበቃ የምትሰጠው ትኩረት የላላ መሆኑን በማንሳት ምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙሀን ውርጅብኝ ሲያወርዱባት ነበር፡፡ ቻይና በቅርብ ዓመታት በኢኮኖሚው ረገድ ያደረገችው እምርታ ዜጎቿ በንፁህና ጤናማ አካባቢ ለመኖር እንዲችሉ ባለማድረጉ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱባት ይገኛሉ፡፡ የቻይና በቴክኖሎጂ መራቀቅ ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና የሚሰጥበት ስርዓት እስካልዘረጋ ድረስ ጥያቄዎቹ ወደፊትም ይቀጥላሉ፡፡
በምሕረት ሞገስ
ዛሬ እንደቀድሞው በተበላሹ መኪኖች ሥር እየተንከባለለ አይሠራም፡፡ የመካኒክነት ሥራውን ተወት አድርጐ ሞባይሉንና መፅሐፍ ቅዱሱን በጥቁር ቦርሳው አዝሎ በየመንገዱ ይዘዋወራል፡፡
29ኛው ኦሊምፒያድ በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ነው፡፡ በቤጂንግ ሲካሄድ ለሰነበተው የቤጂንግ ኦሊምፒክ ቻይናውያን ልዩ ድምቀትን የሰጡት በዝግጅቱ ብቻ ሳይሆን በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የበላይነታቸውን ጭምር ማረጋገጣቸው ስለስኬታቸው እንድናስብ እንገደዳለን፡፡
ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት እንደምትፈጽም አስታወቀች
የዩናይትድ ስቴትስና የፖላንድ የፀረ ሚሳኤል ግንባታ ስምምነት አዲስ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እንደሚፈጥር ያስጠነቀቀችው ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል አስታውቃለች፡፡
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.