Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Sep 30th
Home arrow Sections arrow ዘውዲቱ ሆስፒታል ሥራውን ሊያቋርጥ ይችላል
ዘውዲቱ ሆስፒታል ሥራውን ሊያቋርጥ ይችላል E-mail
Wednesday, 09 January 2008
ዘውዲቱ ሆስፒታል ተገቢውን አገልግሎት በህብረተሰቡ እየሰጠ ባለመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ሊያቋርጥ እንደሚችል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

ረጅም እድሜ ያስቆጠረው ዘውዲቱ ሆስፒታል ጥገና ባለማግኘቱና የአገልግሎት መስጫ መሳሪያዎቹ በቂ ባለመሆናቸው ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን፣ ሆስፒታሉ ሥራውን በአግባቡ እንዲያካሂድ ከሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ትኩረት የማይሰጠው ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለማቋረጥ እንደሚገደድ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡

/አዲስ ልሣን፣ ታህሣሥ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም./

ቅርሶችን ሣይንሳዊ በሆነ መንገድ መመዝገብ ተጀመረ

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በአገሪቱ ያሉትን ቅርሶች ሳይንሳዊ በሆነ የመረጃ ቋት ለመመዝገብ የሚያስችል ሥራ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የመረጃ ቋቱ በአገሪቱ ያሉትን ቅርሶች ዓይነትና ብዛት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመመዝገብ ህገ ወጥ የቅርሶች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጿል፡፡

/አዲስ ዘመን፣ ታህሳስ 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም./

ከዝንጅብል የሚገኘው ገቢ ዝቅተኛ ነው

በወላይታ ዞን በየዓመቱ እስከ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ዝንጅብል ቢመረትም ከምርቱ እየተገኘ ያለው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ገለፀ፡፡ ከዞኑ ባለፉት አምስት ወራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ከተላከ የዝንጅብል ምርት አምስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡

በዞኑ በዝንጅብል ከተሸፈነው ስምንት ሺ ሄክታር መሬት በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ቢቻልም አምራቾቹ የሚያገኙት ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን፣ አርሶ አደሩ ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማቅረብ ባለመቻሉና በዘላቂነት ምርቱን ወደ ውጭ አገሮች ለመላክ የተጠናከረ የገበያ ሰንሰለትና ላኪ ድርጅቶች አለመኖር ከምርቱ ዝቅተኛ ገቢ እንዲገኝ ተፅእኖ ማሳደሩን፣ በዞኑ ምርቱ በስፋት የሚመረትባቸው ኪንዶ ኮሻ፣ በሎሶ ስሆና፣ ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎች የዝንጅብል መጭመቂያ ፋብሪካዎችን መትከል የሚቻልበትን ሁኔታ መመቻቸቱን ገልጿል፡፡

/ዋኢማ/

መኖሪያ ቤት ተቃጥሎ የ45ሺ ብር ንብረት ወደመ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ከ45 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ገልፆ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ መዳኑንም ተናግሯል፡፡
የሲሊንደር ጋዝ አፈትልኮ የተነሳው ቃጠሎ ወደ ሌላ ሳይዛመት አንድ ሰዓት ከስምንት ደቂቃ ብቻ ቢወስድም በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ 13 ሺ ሊትር ውሃ በመጠቀም መቆጣጠር መቻሉን ገልጿል፡፡

/ኢዜአ/

አርሶ አደሮች ከመስኖ ልማት ከ15ዐ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኙ

በደቡብ ወሎ ዞን በመስኖ አትክልትና ቅመማ ቅመም ያመረቱ አርሶ አደሮች ከሽያጩ ከ15ዐ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ገለፁ፡፡

አርሶ አደሮቹ ገቢውን ያገኙት ባለፈው የመኸር ወቅት በመስኖ ካለሙት 34 ሺህ 620 ሄክታር መሬት ሲሆን፣ ከአንድ ሚሊዮን 854 ሺህ 550 ኩንታል የሚበልጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ሽያጭ እንደሚገኝበት ተናግሯል፡፡

/ኢዜአ/

 
< Prev   Next >