| ፒቲኤ ባንክ ካፒታሉን ወደ 140... |
|
|
| Wednesday, 19 March 2008 | |
|
ፒቲኤ ባንክ ካፒታሉን ወደ 140 ቢሊዮን ሽልንግ ሊያሳድግ ነው
ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት በአባልነት ያቀፈው የፒቲኤ ባንክ የካፒታል አቅሙን ከ38 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወደ 140 ቢሊዮን ለማሳደግ ማቀዱ ተገለፀ፡፡ ባንኩ ከትናንት በስቲያ ያወጣው መግለጫ ጠቅሶ ቢዝነስ ዴይሊ እንደዘገበው የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ የታቀደው የባንኩን ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግና በአካባቢ አገራቱ ያለውን የገንዘብ ፍላጐት ተንቀሳቃሽ ገንዘብን በማይነካ መልኩ ለማሟላት ያቀደ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት የአፍሪካ ልማት ባንክ አሁን ካለው 5.8 በመቶ ባንኩ ሀብት ተጨማሪ 3.3 ቢሊዮን ሽልንግ የተጣራ ካፒታል ያስገባ ሲሆን 476 ሚሊዮን ሺልንጉ በአጭር ጊዜ የሚከፈል ቀሪው ተዘጋጅቶ በአስፈላጊ ጊዜ የሚወጣ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የፒቲኤ ባንክ የባለአክሲዮኖች አወቃቀር በአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ እንደማይለወጥ ለዚህም ሌሎች ባለአክሲዮኖች ተቀራራቢ የሆነ ካፒታል የማስገባት አቅም እንዳላቸው ተገል..ል፡፡ የባንኩ አዲስ የካፒታል አወቃቀር ባለፉት አራት ዓመታት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣው የቢዝነስ እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው ዓመት ባንኩ በአካባቢ አገራቱ ለሚገኙና 35 ቢሊዮን ሺልንግ ለሚያወጡ ፕሮጀክቶች ብድር የሰጠ ሲሆን የ24 በመቶ እድገት እንዳለውም ለንግድ እንቅስቃሴ እገዛ የሚውል 100 ሚሊዮን ሽልንግ መስጠቱ ተጠቁሟል፡፡ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሚ/ር ሙታሂ ሙሬቲ እንደገለፁት አዲሱ የካፒታል አወቃቀር ባንኩ ተወዳዳሪ የሆነ ዋጋ ለፕሮጀክቶቹና ለንግድ እንቅስቃሴዎች የሚያደርገውን እገዛ አንደሚያቀላጥፈው ተናግረዋል፡፡ የፒቲኤ ባንክ ቅድሚያ ትኩረት በኮሜሳ አባል አገራት አገሮች የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የባንኩ ባለድርሻ ባለአክሲዮኖች ከኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ታንዛኒያ፣ ዝምባቡዬ፣ ቡሩንዲ፣ ኮሞሮስ፣ ጅቡቲ፣ ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ኡጋንዳ ሲሆኑ ከአካባቢ አገራቱ ወጪ ቻይና መሆኗ ተጠቁሟል፡፡ ባንኩ በኬንያ የሚገኙ ድርጅቶች አገልግሎት ሲሰጥ ለመሠረተ ልማት ግንባታና ለአገልግሎቶች ማስፋፊያ ከሚሰጠው እገዛ በማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል 500 ሚሊዮን ሽልንግ መስጠቱ ተጠቁሟል፡፡ ባንኩ በተጨማሪ በብድር ለኬንያ አየር መንገድ፣ ለኬንያ ወደብ ባለስልጣን አቲ ሪቨር ለተባለ የማዕድን አውጪ ኩባንያ ብድር መስጠቱና ገልፍ አፍሪካ ለተሰኘ ባንክ ማቋቋሚያ እገዛ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ ፒቲኤ በምሥራቅ አፍሪካ ለሚገኙ አገራት ከውጭ ለሚያስገቡት ነዳጅ ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |