Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow አል አሙዲን በደቡብ አፍሪካ...
አል አሙዲን በደቡብ አፍሪካ... Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
Image
ሼህ መሐመድ አል አላሙዲን
አል አሙዲን በደቡብ አፍሪካ መሬት ሊገዙ ነው


ሼህ መሐመድ አል አላሙዲን በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ውስጥ ሳንድቶን በተባለ አካባቢ የሚገኝን መኖሪያና ሆቴል ያረፈበትን መሬት ለመግዛት በሂደት ላይ መሆናቸውን ዘ ታይምስ የተባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ይፋ አደረገ፡፡
ከትናንት በስቲያ በተሰራጨው ይኸው ጋዜጣ ዘገባ መሠረት ከአለማችን ቱጃሮች አንዱ የሆኑት ሼህ መሀመድ አልአሙዲ ከአለማችን ቱጃሮች መካከል በ97ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቅሶ በሰሜናዊ ጆሃንስበርግ ሳንድቶን በተባለ አካባቢ የሚገኘው ይህ ቦታ 11ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት እንዳለው አመልክቷል፡፡

የመሬቱ እና የንብረቱ ዋጋ 200 ሚሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ የተገመተው  ይህ ቦታ ጆሃንስበርግ ውስጥ ከሚገኙ አንደኛ ደረጃ ከሚሰጣቸው ቦታዎች አንዱና ሐብታሞች የሚኖሩበት አካባቢ ነው፡፡ አላሙዲን ይህን ሊገዙት ያሰቡትን ቦታ በግንባር ተገኝተው መመልከታቸውን ጋዜጣው ጠቁሟል፡፡  

ጉዳዩን አስመልክቶ የመሬቱ ባለቤቶች አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ ባይሆኑም አልአሙዲን መሬቱን ለመግዛት ፍላጎት ካሳዩ ወገኖች የሚመደቡ ሲሆን እስከ 150 ሚሊዮን ራንድ ለማውጣት ተስማምተዋል፡፡

በመሬቱ ላይ 35 ልዩ ልዩ የመኖሪያ ቤቶችና 125 ክፍሎች ያሉት ሆቴል ያለው ሲሆን ባለሃብቱ በቦታው ላይ ምን አይነት ግንባታ እንደሚያካሂዱበት ግን አልጠቀሰም፡፡

በጋዜጣው ዜና መሠረት፣ የአልአሙዲን የግዢ ሃሳብ ከተሳካ በደቡብ አፍሪካ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የውጪ አገር ቢሊየነሮች አንዱ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ይህንን ቦታ ለመግዛት 138 ሚሊዮን ራንድ ቀርቦ እንደነበር ጋዜጣው አስታውሷል፡፡
 
< Prev   Next >