Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow የሁለት ሲሚንቶ ፋብሪካዎች...
የሁለት ሲሚንቶ ፋብሪካዎች... Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
የሁለት ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት የጥራት ደረጃ እየተፈተሸ ነው

የማምረት ሥራ የጀመሩ ሁለት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚያመርቱትን ሲሚንቶ የጥራት ደረጃን የኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃ ባለሥልጣን እየፈተሸመሆኑ ተገለፀ፡፡

የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሲሳይ አሰፌ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ባቀረቡት ናሙና መሠረት ፍተሻ እየተደረገባቸው ያሉት ሲጂሲ እና አቢሲኒያ የተባሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡

በቻይናና በሕንድ ባለሃብቶች የተቋቋሙት ሁለቱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት ሥራ የጀመሩ ሲሆን ምርታቸውን በቀጥታ ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት በባለሥልጣኑ የምርታቸውን ጥራት ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚገባቸው የጠቆሙት አቶ ሲሳይ ከማረጋገጫው በፊት ምርታቸውን ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ መሸጡ ተመራጭ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሁለቱም ፋብሪካዎች ምርት ናሙናዎች በባለሥልጣኑ ባለሙያዎች እየተፈተሹ ቢሆንም ደረጃቸውን ጠብቀዋል አልጠበቁም የሚለውን ውጤት ለመግለፅ 25 ቀናት አካባቢ ይወስዳል፡፡ ከፋብሪካዎቹ ናሙና የተወሰደው ከአንድ ሳምንት በፊት እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ግን ሲጂሲ የተባለው የቻይና ኩባንያ በቆቃ አካባቢ በተከለው ፋብሪካው በማምረት ላይ የሚገኘውን ሲሚንቶ ለገበያ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል፡፡

 
< Prev   Next >