Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow ባለስልጣኑ የተፈቀደለት በጀት...
ባለስልጣኑ የተፈቀደለት በጀት... Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
Image
አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል
ባለስልጣኑ የተፈቀደለት በጀት ስላነሰው ተጨማሪ 400 ሚሊዮን ብር ጠየቀ


መንገዶችን ለመጠገን በመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የተመደበለትን በጀት ጨርሶ ተጨማሪ የ400 ሚሊዮን ብር በጀት መጠየቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በፌዴራል ስር የሚገኙ መንገዶች ከ20 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በመድረሳቸው ጥገና የሚያስፈልጋቸው መንገዶች ቁጥር አድጓል፡፡ በዚህም መሠረት ለጥገና የሚያስፈልገው በጀት እየጨመረ ስለመጣ ለጥገና የሚመደበው በጀት ማደግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በ2000 የበጀት ዓመት ከመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ባለስልጣኑ ለሚያካሄዳቸው የተለያዩ የመንገድ ጥገናዎች የተመደበለት 550 ሚሊዮን ብር ቢሆንም የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ገንዘቡ እያለቀ በመሆኑ ተጨማሪ የ400 ሚሊዮን ብር በጀት ጥያቄ ለማቅረብ መገደዳቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለጥገና የተያዙ 30 የመንገድ ፕሮጀክቶች ያሉ መሆናቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህም ከፍተኛ የመንገድ ጥገና ናቸው፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሚፈጁት በጀት በበጀት ዓመቱ ለጥገና ከተፈቀደው በላይ ነው፡፡

“መንገዶቻችን ያሉበት ሁኔታ በተቻለ መጠን ከ70 እስከ 80 በመቶው በጥሩ ሁኔታ እንዲጠጋ እንፈልጋለን፡፡ አሁን በሃምሳና በስልሳ መካከል ነው” የሚገኙት ያሉት አቶ ዛይድ በተገነቡበት ደረጃ መሠረት በመጠገን ሊኖር የሚገባውን ደረጃ እንዳይዙ መደረግ አለበት፡፡

ባለስልጣኑ ከመንገድ ፈንድ እንዲመደብለት ከጠየቀው 400 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውናቸው 180 የመንገድ ፕሮጀክቶች በመንግሥት የተመለደበለት በጀት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ 1.7 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቅርቦ አዎንታዊ ምላሽ ማግኘቱን ዳይሬክተሩ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ካሮድፈንድና ከመንግሥት የተፈቀደለት ተጨማሪ በጀትም 2.1 ቢሊዮን ብር እንዲደርስ አድርጐታል፡፡  

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >