| የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ... |
|
|
| Wednesday, 19 March 2008 | |
|
የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤት ቀረበ
የኤክሳይዝ ታክስ ይሰበሰብባቸው ከነበሩ በ19 ክፍሎች ከተከፋፈሉ የምርት አይነቶች ውስጥ በሰባቱ ላይ ይጣል የነበረው ኤክሳይ ታክስ እንዲቀንስና ኤክሳይ ታክስ ሳይጣልበት በቆየ በአንድ ምርት ላይ ደግሞ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣል የሚያስችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀርቧል፡፡ ኤክሳይዝ ታክስ በማኅበራዊ ኑሮ ላይ ጫና በሚያስከትሉ እንዲሁም መሠረታዊ ጠቀሜታ በሌላቸው ምርቶች ላይ የሚጣል መሆኑን በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቁሟል፡፡ እንደ ውስኪ ያሉ ደግሞ ይጣልባቸው የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ 25 በመቶ ጭማሪ ተደርጎበታል፡፡ ኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው 19 የምርት አይነቶች ውስጥ ማሻሻያ የተደረገባቸው የለስላሳ መጠጦች (ከፍሬ ጭማቂዎችና እነዚህን ከመሳሰሉት በስተቀር)፣ በዱቄት መልክ የተዘጋጁ ለስላሳ መጠጦች፣ በፋብሪካ የተመረተ የታሸገ ውሃ በፋብሪካ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ ወይም የተዘጋጁ ልብሶች ናቸው፡፡ በረቂቅ አዋጁ መሠረት ማንኛቸውም የለስላሳ እና በዱቄት መልክ የተዘጋጁ መጠጦች ከዚህ ቀደም ይከፈልባቸው የነበረው የ40 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ወደ 30 በመቶ፣ በፋብሪካ የተመረተ የታሸገ ውሃ ይከፈልበት የነበረው 30 በመቶ ወደ 20 በመቶ ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል፡፡ የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ አዋጁ በተወሰኑ ምርቶች ላይ ቢቀንስም እስካሁን ድረስ ኤክሳይስ ታክስ የማይከፈልበትን የአውሮፕላን ነዳጅ 30 በመቶ እንዲከፈልበት ይደነግጋል፡፡ 50 በመቶ ብቻ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልበት የነበረው ውስኪ ከሌሎች ምርቶች ጋር ሲነፃፀር የተጣለበት የኤክሳይዝ ታክስ አነስተኛ በመሆኑ 75 በመቶ እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/1995 መሠረት ከታህሳስ 23 ቀን 1995 ጀምሮ የሚፀና የኤክሳይዝ ታክስ መጠኑ ከ10 እስከ 100 በመቶ የሚከፈልበት ሲሆን ይህ ታክስ ተግባራዊ ከሚሆንባቸው 19 ምርቶች መካከል ሽቶዎች በተለያዩ የአልኮል መጠጦች (ቢራ ውስኪና የወይን ጠጅን ሳይጨምር) 100 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል፡፡ ከእነዚህም ምርቶች ቀጥሎ ከፍተኛ የኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸው የነበሩት ሲጋሬት ሲጋራ፣ ሲጋራ ሎስ፣ የፒፓ ትንባሆ፣ ሱረትና ሌሎች የትምባሆ ውጤቶች 75 በመቶ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚሆኑ የማጠቢያ መኪናዎች 80 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል፡፡ በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ተደራራቢ ኤክሳይዝ ታክስን ለማስቀረት በአውቶሞቢል መገጣጠሚያዎችና በተሰፉ ልብሶች ላይ ይጣል የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ በእነዚህ ምርቶች ላይ በግብአት ላይ የተከፈለው ታክስ እንዲቀነስ አስተያየት ቀርቧል፡፡ እነዚሀ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የሚመለከተው የረቂቅ አዋጁ አንቀጽ “በፋብሪካ ከጨርቃ ጨርቅ የሚሰሩ ወይም የሚዘጋጁ ልብሶች አገር ውስጥ ሲመረቱ እና ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ ሲገጣጠሙ ሊከፈል የሚገባው የኤክሳይዝ ታክስ በሚሰላበት ጊዜ ለእነዚህ እቃዎች ማምረቻ የዋሉ ግብአቶች ወደ አገር ሲገቡ የተከፈለው ኤክሳይዝ ታክስ ተቀናሽ ይደረጋል” በሚል እንዲተካ ይጠይቃል፡፡ በመኪና መገጣጠም ሥራ ላይ ከተሰማሩ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግ. ማ. ኃላፊዎች ተደራራቢ ታክስ መቀነሱ ምርቶቻውን ለተጠቃሚው የሚያቀርቡበትን ዋጋ እንዲቀንስ ያስችላል ብለዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ቀርቧል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |