Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የጉጂ ኦሮሞ ሥነ ቃል
የጉጂ ኦሮሞ ሥነ ቃል Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
Imageሥነ ቃል ለአንድ አገር ታሪካዊ ማስረጃዎች ምንጭነት ከሚረዱ ባህላዊ ወይም ፎክሎራዊ ቅርሶች መካከል ይመደባል፡፡
በጉጂ ጎሣ ሥነቃል ላይ ጥናት ያደረጉት አቶ ገነነ ዑዴሣ እንደገለፁት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች የሕዝብ አኗኗር፣ ልምድ፣ ወግ፣ አምልኮ ወዘተ. በጽሑፍ ላይ የሰፈሩ ባለመሆናቸው የሥነቃል ጥናት የተለየ ትኩረትን ይሻል፡፡ ሥነ ቃል ተጠንቶ ካልተጻፈ ስለሚረሳ ጠፊ ነው፡፡ በጎሣው ውስጥ ስላለው የሥነቃል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታና ባህላዊ ገጽታ ሥነቃሉ የሚገጠሙበትንና የሚዘፈኑበትን አጋጣሚ አጥኚው ተመልክተውታል፡፡

ዌዱ (የሙገሣ ዘፈን) በዌዱነት የሚታወቁ ዘፈኖች በሁለት ይከፈላሉ፤ የሚለያዩበት በሚሞገሱት ነገሮች ልዩነት ነው፡፡

ዌዱ ሎኒ (የከብት ሙገሣ ዘፈን) ለጉጂ ጎሣ ከብቶች ዋና የገቢ ምንጭ በመሆናቸው ይወደዳሉ፣ ይከበራሉ፣ ይወደሳሉ፣ ከፍተኛ እንክብካቤም ይደረግላቸዋል፡፡ እነዚህ የፍቅር፣ የክብርና የሙገሳ ስሜቶች ሕዝቡ በተለያዩ ዜማዎች በሚዘፍኗቸው አያሌ የዌዱ ሎኒ ዋና ጭብጥ፣ ከብቶችንና ጌቶቻቸውን ማወደስ ነው፡፡ ታታሪ ከብት አርቢዎች ሀብታምና ለጋሶች ይሞካሹበታል፡፡ እንዝላሎችና ስስታሞች ይወቀሱበታል፡፡

ከብት ስንል ላም፣ ኮርማ፣ በሬ፣ ጥጃ፣ ፍየል፣ ፈረስ እና አህያን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ የቤት እንስሳት በሙሉ የየራሳቸው የሆነ ዌዱ አላቸው፡፡ ዌዱዎቹ የሚዘፈኑት በቅደም ተከተል ሲሆን፣ የዌዱዎች ሁሉ መጀመሪያ ሀያዩ ሆሬ ነው፡፡ ሀያ ዩ ሆሬ ማለት ሀያዩ የተባለ ሰው ብዙ ከብት አረባ ማለት ነው፡፡ በሀያዩ ሆሬ ከብቶች በአጠቃላይ ሲወደሱ በተከታታይ ዌዱዎች ማለትም በዌዱ ኮርማ-ኮርማ፣ በዌዱ ሳንጋ-ሰንጋ፣ በዌዱ ያቢ-ጥጃ፣ በዌዱ ሬኤ-ፍየል እና አርቢዎቻቸውን ያሞግሳሉ፡፡

የዌዱ ሎኒ ተጫዋቾች ተሰብስበው በመቀመጥ እያጨበጨቡና እየተቀባበሉ በመግጠም ይዘፍናሉ፡፡

ሁለተኛው የዘፈን ዓይነት ዌዱ ጋጉራ (የቀፎ ሙገሣ ዘፈን) ነው፡፡ የጉጂ ጎሣ ቀፎ ሰቅሎ ማር ቆርጦ መጠቀም የቆየ ልማድ መሆኑን የጎሣው ሽማግሌዎች ያወሳሉ፡፡ ከቀፎ የሚገኝ ጥቅም ከፍተኛ በመሆኑ ቀፎም የራሱ በሆነ ዌዱ ይሞገሳል፡፡ ታታሪ ቀፎ ሰቃይ የሚበረታበትን ያህል ሰነፉ በዌዱ ጋጉራ ይንኳሰስበታል፡፡ ዌዱ ጋጉራ የሚዘፈነው የቀፎ እንጨት ፈለጣ እና ቀፎን በሳር የመሸፈኑ ሥራ ሲከናወን እንዲሁም ጎበዝ ቀፎ ሰቃይ የማር ጠጅ አስጥሎ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ጋብዞ ሲደሰቱ ነው፡፡

ዘፋኞቹ በማር ወይንም በማር ገንዘብ የተገዙትን እንስሳት በሙሉ በመኩራራት መንፈስ ያሞግሳሉ፡፡

የጉጂ ጎሳ አያሌ ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶችን ያከናውናል፡፡ የገዳ የሥልጣን ዝውውር፣ የድግስና የጋብቻ በዓላት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በሥነ ሥርዓቶቹ በተለይም በገዳ የሥልጣን ዝውውር ወቅት ኅብረተሰቡ በገዳ አስተዳደር ወደ ተወሰኑ ቦታዎች ተጎዳኝቶ ተገቢው ባህላዊ ክንዋኔ ሲከናወን ባለማቋረጥ ቀንና ሌሊት ይዘፈናል፡፡ በዚህ ታላቅ በዓል ላይ ለወንዶች ከሚቀርቡት ዘፈኖች መካከል ቄጣላና ሰርብቻ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡

ጀግንነት በጉጂ ኅብረተሰብ ዘንድ የተለየ ግምት ይሰጠዋል፡፡ ይከበራል፣ ይፈራል፣ ይደነቃል፣ ይሞገሳል፡፡ በአንጻሩ ፊሪ ይናቃል ይጠላልም፡፡ ስለዚህ ወንድ ልጅ ሁሉ ደፋር እና ጀግና መሆን አለበት የሚል የቆየ እምነት አለ፡፡ ጀግንነት የሚለካው አንድ ሰው በአደን፣ በዘመቻ ወይም በጥል ወቅት በሚፈጽመው የድፍረት ዳዲሣ-ፉከራ ራሱን፣ ሌሎች ጀግኖችን፣ ጓደኞቹንና ዘመዶቹን ያወድሳቸዋል፡፡ ፈሪዎችንና ጠላቶችን ያወግዝበታል፡፡

በጌራርሣ ግጥሞች የጀግኖች የአደን ሁኔታ፣ ውጣ ውረዱንና የዘመቻ አስቸጋሪነት ሲዘረዘሩበት፣ በዳዲሣ ግጥሞች ደግሞ ፎካሪው የገደላቸውን እንደ ነብር አንበሣ፣ ዝሆን፣ አውራሪስ፣ ጎሽ ያሉትን ትላልቅ አውሬዎችና በጦርነት የገደላቸውን ሰዎች አንድ በአንድ ይዘረዝራሉ፡፡

በአብዛኛው ጀግኖች፣ የሚያቅራሩት፣ የሚሸልሉትና የሚፎክሩት በኩዳ (አንድ ሰው ጠላቱ ወይም ትልቅ አውሬ ሲገደል ከብት ታርዶ የሚዘጋጅ በዓል) ላይ ቢሆንም ሌሎች አጋጣሚዎችም ላይ ይቻላል፡፡ ሥነ ሥርዓቱ የሚካሄደው ቁጭ ተብሎ ነው፡፡ ወኔ የተናነቀው ጀግና ብድግ ብሎ ሊፎክር ይችላል፡፡

ሴቶች እንደ ወንዶቹ ዘምተው ወይም አድነው በመግደል ባያቅራሩና ባይፎክሩም የጀግና ባሎቻቸውን ዘመዶቻቸውን የጀግንነት ውሎ የሚያወሱባቸው የተለያዩ ዘፈኖች አሏቸው፡፡ ለምሳሌ ውርሴዩታ (አውራሪሶቹ) የሚባለው ዘፈን ለአውራሪስ ገዳዮች የሚዘፈን ዕውቅ ዘፈን ነው፡፡

በአገራችን ስለ ፍቅር የማያንጎራጉርና የማያዜም የኅብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ ሁሉም የፍቅርን ረቂቅነት ስለሚረዳው ቅኔ ይቀኛል፡፡ ስንኝ ይቋጥራል፡፡ ጉጂም እንደዚሁ፡፡ በኅብረተሰቡ የፍቅር ዘፈን ዌሎጃላላ እንደሚባል አቶ ገነነ ያስረዳሉ፡፡  

ጎላ ብሎ የሚታየው የጉጂ ኅብረተሰብ የፍቅር ዘፈን ጎረምሶችና ኮረዳዎች ያፈቀሯቸውን በማድነቅ፣ በመካብ፣ በማሞካሸት እና የጠሏቸውን በመንቀፍ የሚዘፍኑት ዌሉ ጃላላ ይባላል፡፡ የተፋቀሩ እረኞች ከየከብቶቻቸው መንጋ ጋር ሆነው ለተፋቃሪዎቻቸው እንዲሰማ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያዜማሉ፡፡

ዌሎ በባሌ አካባቢም በተለየ ዜማ ይዘፈናል፡፡ የጨዋታም ምንጭ ባሌ ነው የሚሉ ሰዎች ቢኖሩም የጉጂ ኅብረተሰብ ዌሎ ተጫዋቾች ጨዋታውን የሚጀምሩት እንዲህ በማለት ነው፡፡
ዌሌ እሳት ሀንበሬ ስላሌት በሬ፣   
ዌሉኦ አፋርታማን ጋሌ፣
አፈርታማ ላሌ ዶት ኬሳ ሸኒ፣
ዋነ ነጅብኒፍ ዶቃቴቱ ሰኒ፡፡
የአማርኛ ትርጉሙ የሚከተለው ነው፡፡
(ዌሉን የለመድነው እዚህ ሳይሆን እሰላሌ ነው
ለዌሉ ምሽት የወጣነው አርባ ነበርን
ከአርባችን አውጭዎች (አዌሉ) አምስት ነበሩ
የተጣላሁት ለተቀመጠችው ጥቁር (ልጅ) ነው፡፡)

በጉጂ ኅብረተሰብ የዕለቱ ሥራ ተጠናቆ ማታ የእንቅልፍ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ከሚጫወቱአቸው የጊዜ ማሳለፊያ ጨዋታዎች አንዱ ሂቦ (እንቆቅልሽ) ነው፡፡ ሂቦን የሚጫወቱት እኩል አባላት ያሏቸው ሁለት ቡድኖች ሲሆኑ፣ የአባላቱ ብዛት ወሰን አይኖረውም፡፡ አንደኛው ወገን ጥያቄ ሲጠይቅ ሌላው መልስ ይሰጣል፡ የቀድሞው ተጠያቂ ቡድን በተራው ጠያቂ ይሆናል፡፡ አሸናፊው የሚለየው ብዙ ትክክለኛ መልሶችን በመመለስ ነው፡፡

በጉጂ ኅብረተሰብ ውስጥ ካሉት ሁለት የእንቆቅልሽ ዓይነቶች እንደ ሂቦ ሲባል በዚህ ዓይነቱ እንቆቅልሽ አጠቃላይ የሆኑ የሚያመራምሩ ጥያቄዎች ይጠይቃሉ፡፡ ጠያቂው ሂቦ - እንቆቅልሽ ሲል ተጠያቂው ህብብ-ምን አውቅልህ ይላል፡፡ አጫጭርና ረጃጅም የሂቦ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ሁለተኛው ዓይነት እንቆቅልሽ ሂቦጠሬ በመባል ይታወቃል፡፡ የዚህ እንቆቅልሽ ዋና ዓላማ አንድ ሰው በአቅራቢያው ስላሉ የተለያዩ ቤተሰቦች ቁጥር የማስታወስ ችሎታን መፈተን ነው፡፡ አዋቂ ወንድ በኮርማ፣ አዋቂ ሴት በላም፣ ወንድ ልጅ በወይፈን፣ ሴት ልጅ በጊደር ተመስለው ጥያቄው ይቀነባበራል፡፡ የአቶ ገነነ ምሳሌዎች ጉዳዩን ያብራሩታል፡፡

ጠያቂ፡ ሂቦጠሬ (እንቆቅልህ)
ተጠያቂ፡ ጠሬ (ምን አውቅልህ)
ጠያቂ፡ ኮርማ ጠሬ (ኮርማ እንቆቅልህ)
ተጠያቂ፡ አጣሬ (ምን አውቅልህ)
ጠያቂ፡ አጣሬ (ላም እንቆቅልህ)
ተጠያቂ፡ ጠሬ (ምን አውቅልህ)
ጠያቂ፡ ጅብቻ ጠሬ (ወይፈን እንቆቅልህ)
ተጠያቂ፡ ጠሬ (ምን አውቅልህ)
ጠያቂ፡ ጠሬ ጄጂ ዎራ ሀገነ ሀም (ምን አውቅልህና ይህንን ቤተሰብ ነገረኝ)
ተጠያቂው የተጠየቀውን ቤተሰብ ለመለየት ፍለጋ እንደቀረው ቤተሰቡ የሚገኝበት ክልል ከምን መልስ እንደሆነ በአራቱም አቅጣጫ ማስወሰን ይችላል፡፡

ይሁንና ከላይ በተጠየቀው ሂቦጠሬ መሠረት ተጠያቂው በክልሉ ያለ አባዎራ፣ የቤት እመቤት እና አንድ ወንድ ልጅ ያቀፈ ቤተሰብ መፈለግ ይኖርበታል፡፡

በሔኖክ ያሬድ
 
< Prev   Next >