| የወንዶች መካንነት በፅንስነት... |
|
|
| Wednesday, 19 March 2008 | |
|
የወንዶች መካንነት በፅንስነት እድሜ የሚወሰን ነው
የተለመዱ የመካንነት ችግሮች፣ ዝቅተኛ የስፐርም ቁጥር ማምረት፣ የወንድ ዘር ፍሬ ካንሰርና የመሳሰሉ በወንዶች የዘር ፍሬያማነት ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች በእርግዝና ወቅት የሚፈጠሩ የአንዳንድ ሆርሞኖች መጠን ወሳኝነት እንዳለው በጥናት ተረጋገጠ፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው ግኝት ከስምንት እስከ 12 ሳምንት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ቴስቴስትሮን የተሰኘው የወንዶች ሆርሞን ያለው መጠን የወደፊቱን የዘር ፍሪያማነታቸውን እንደሚወሰን ነበር፡፡ በዘር ፍሬ ውስጥ ያለ ችግር ወይም የሽንት ቧንቧ የተዛባ አቀማመጥ በተለይ በወጣት ወንዶች ላይ የመካንነት ችግርን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ አዲሱን ጥናት ያካሄዱት ሳይንቲስቶች ኃላፊ ዶ/ር ሚካኤል ዊልሽ እንዳሉት “የወንዶች የመካንነት ችግር የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም የእኛ ግምት ግን ገና በፅንስነት እድሜ በእርግዝና ወቅት ጭምር የሚወሰን ነው፡፡ ይሁንና የስፐርም መጠን መቀነስና የዘር ፍሬ ካንሰር በተመሳሳይ የወንዶችን መካንነት የሚያስከትሉ ናቸው” በላቦራቶሪ በአይጦች ላይ በተደረገ ክትትልም የተገኘው ውጤት የሚያመለክተው የወንዶች መካንነት ችግር በእናታቸው ማህፀን ባሉበት ወቅት በሚፈጠር የሆርሞኖች መጠን ችግር ጭምር ሊሆን እንደሚችልም ነው፡፡ ከፍተኛ የበረዶ ክምር ማርስ ላይ ታየ በማርስ ላይ ከፍተኛ የሆነ የበረዶ ክምር መታየቱንና ከፕላኔቱ ከርሰ ምድር ውስጥም የውሃ ክምችት ሳይኖሩ እንደማይቀር ሳይንቲስቶች ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡ በረዶውን ማየት የተቻለው “ናሳ ማርስ ሪኮናይሳንስ” ኦርቢተር የተሰኘች መንኮራኩር በተተከለ ራዳር አማካይነት በፕላኔቷ መካከለኛው ሰሜናዊ ክፍል በተደረገው ጥናት መሆኑ ታውቋል፡፡ ከራዳሩ የተገኘው መረጃ የሚጠቁመው በማርስ ውስጥ የታየው ውሃ አብዛኛውን (ከ50 በመቶ በላይ) በበረዶ መልክ ያለ ነው፡፡ ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት በፕላኔቷ ላይ የታዩ የበረዶ ክምሮችና አለቶች የአማዞንያን ጊዜ ተብሎ በሚጠራው የዘመን አጋማሽ አካባቢ ማለትም ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዓመታት በፊት የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የአማዞንያን ጊዜ የሚባለው በማርስ ታሪክ ውስጥ በጣም ቅዝቃዜ የነበረበት ጊዜ ነው፡፡ መካከለኛ ከፍታ ባለው የማርስ አካባቢ በአማዞንያን ጊዜ ከፍተኛ የበረዶ ግግር እንደተፈጠረ ሳይንቲስቶች ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡ ከተፈጠረው የበረዶ ግግር መካከል አብዛኛውም እስካሁን ድረስ መቆየት መቻሉን ሳይንቲስቶች ገልፀዋል፡፡ ፕሮቲን - ከአይነ ስውርነት ለመዳን በአይን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮችን በመጉዳት አይነ ስውርነትን የሚያስከትሉ በሽታዎችን ለመከላከል ፕሮቲን እንደሚያግዝ ታወቀ፡፡ አይን ውስጥ በሚገኙ ጡንቻዎች መጎዳትና በስኳር በሽታ ምክንያት በሚከሰቱ ችግሮች አይን ውስጥ የደም ስር መጎዳት ስለሚከሰት ሰዎች ለአይነ ስውርነት ይጋለጣሉ፡፡ በኡታህ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ደግሞ ሁለቱም ችግሮች በተለይ እድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ ሁለቱም የበሽታ ዓይነቶች በአይን የደም ስሮች ላይ ችግር የሚፈጥሩና ጤናማ ያልሆኑ አዲስ የደም ስሮች መፈጠርን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችሉ ፕሮቲኖችንም ሳይንቲስቶች ለይተው ለማወቅ ችለዋል፡፡ አር.ኦ.ቢ.ኦ.ፎር (Robo4) የተሰኘው የፕሮቲን ዓይነት የተረጋጋና በትክክል የሚሰራ የደም ስር ለመተካት የሚያስችል መሆኑን በአይጦች ላይ ባደረጉት ምርምር እንዳረጋገጡ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ፕሮቲን የሚሰራ መድሃኒት በእድሜ መግፋት ምክንያት የሚከሰትን የጡንቻ ጉዳትና እንዲሁም በስኳር ህመም ምክንያት የሚከሰትን ተመሳሳይ ችግር ለመቅረፍ የተሻለ አማራጭ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ አባል አገራት የአየር ንብረት ጥበቃ ስምምነት ጊዜን አራዘሙ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ለመነጋገር የመጨረሻ ጊዜያቸውን በመወሰን ላይ ተስማምተዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ የሚያደርጉትን ንግግር በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ብራስልስ ውስጥ የተሰባሰቡት 27ቱ አባል ሃገራት የሁለት ቀን ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ በ2009 መጀመሪያ አዲስ ህግ እንደሚያወጡ ተስፋ አድርገዋል፡፡ የሃገራቱ ዋና ዓላማ እ.ኤ.አ በ2020 ዓ.ም ወደ አየር የሚለቀቅን የበካይ ጋዝ መጠን በ20 በመቶ መቀነስ ነው፡፡ ይሁንና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚያስከትሉትን ቀውስና ስለ ስምምነት መነጋገር ይፈልጋሉ፡፡ እንደ ጀርመንና ፈረንሳይ ያሉ አንዳንድ ሃገራት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በንግዱ ዓለም ያለው ተወዳዳሪነት ያሳስባቸዋል፡፡ እነዚህ ሃገራት በሃገር ደረጃ ሳይሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመለወጥ በሚደረገው ጥረት ግለሰቦች በተናጠል የሚያደርጉትን አሉታዊ አስተዋፅኦ መቀነስ እንዳለባቸው ያምናሉ፡፡ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ስዩዝ ዋና ዓላማ ደግሞ በሜዲትራንያን ጠረፍ የሚገኙ የአውሮፓ ሃገራትንና ከአውሮፓ ውጭ ያሉ እንደ እስራኤል፣ አልጄሪያና ቱኒዝያ ያሉ ሃገራትን ሁሉ ግንኙነታቸው እንዲጠብቅ ማድረግ ነው፡፡ አዲሱ ሮቦት እጅ ተገጠመለት ለዓለም አቀፉ የህዋ ማዕከል የተሰራው አዲሱ ሮቦት እጅ ተገጠመለት፡፡ ሪቻርድ ሊንሃን እና ሚካኤል ፎርማን የተሰኙት ጠፈርተኞች የሮቦቱን እጅ ለመግጠም ሰባት ሰዓታት እንደወሰደባቸው ተዘግቧል፡፡ በዓለም አቀፉ የህዋ ማዕከል ላይ ለተዘረጋው ፕሮጀክት ሥራ ለማከናወን ወሳኝ እንደሆነ የሚነገርለት ይኸው ሮቦት አንድ ነጥብ አምስት ቶን ክብደትና 4 ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የሮቦቱ እጆች አነስተኛ ክብደት ያላቸውን እንደ ኤሌክትሮኒክስ ቦክስ፣ ኮምፒውተር እና ባትሪ የመሳሰሉት ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግና ለማስወገድ ሥራ ላይ ይውላል፡፡ የሮቦቱን እጆች በኮምፒውተር አማካይነት በቅርበትና ምድር ላይ ያሉ የጠፈር ተመራማሪዎች ይቆጣጠሩታል፡፡ ሮኬቶች ለህዋ ቱሪዝም ገበያ የአውሮፓው ኢ.ኤ.ዲ.ኤስ ኩባንያ “አስትሪዬም” ክፍል (የኤሪያን ሮኬት አምራች ነው) ለንግድ የሚውልና የከፈሉ ደንበኞችን ከ100 ኪ.ሜትር ከፍታ በላይ የሚያደርስ መሳሪያ ለመሥራት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው 160,000 ፓውንድ ለከፈሉ የእድሜ ልክ ማጓጓዝ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ኩባንያው ከዚህም በተጨማሪ በዓመት ይህን አገልግሎት የሚሰጡ 10 አውሮፕላኖችን ለማምረት አቅዷል፡፡ የኩባንያው የቴክኒክ ኃላፊ ሮበርት ሌን “አውሮፕላኖቹን የሚያመርተው፣ እንቅስቃሴውን የሚያካሂደው፣ ትኬት የሚሸጠውና መስተንግዶውን የሚያከናውነው የተለያዩ አካላት በመሆናቸው እንደማንኛውም የቱሪዝም መስክ የንግድ ሞዴሉ የዘመኑ ዓይነት ነው” ብለዋል፡፡ አስትሪዬም የሚያመርታቸው አውሮፕላኖች እንደ ኤርባስና ቦይንግ ብዙ ባይሆኑም አስፈላጊ ናቸው፡፡ እንደ ሌን ገለፃ የአስትሪዬም ሮኬት አውሮፕላኖች እድገት ፈጣን ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |