Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በኬንያ የተካሄደው ግጭት በእቅድ...
በኬንያ የተካሄደው ግጭት በእቅድ... Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
በኬንያ የኘሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት በእቅድ የተከናወነ መሆኑን መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድን ገለፀ ሲል ቢቢሲ ዘገበ፡፡
 
በቡድኑ ገለፃ መሰረት በኩኩዩ ጐሣዎች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በእቅድ የተከናወነ ነው፡፡ ለዚህም የጥቃቱ ተካፋዮች ከምርጫው በፊት ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ ፖሊስ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጐሳ ግጭት ለማብረድ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀሙን አሳውቋል፡፡ በኬንያ ግጭት ከአንድ ሺ አምስት መቶ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከስድስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡

የምርጫ ውዝግቡን ለመፍታት በቀድሞ የተመድ ዋና ፀሀፊ ኮፊ አናን አደራዳሪነት በተካሄደው ውይይት የኘሬዚደንት ምዋይ ኪባኪ መንግሥትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሥልጣን ክፍፍል ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ከኡጋንዳ የተለቀቀ አሲድ የአካባቢ ብክለት አስከተለ

ከኡጋንዳ የተለቀ አሲድ የኡጋንዳና የኬንያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ብክለት ማስከተሉን የአሶሲየትድ ዘገባ አመለከተ፡፡

በዘገባው መሠረት የሞንባሳ መዝናኛ አካባቢ ተበክሏል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም በብክለቱ ለህመም መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የሞንባሳ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ የሚገኘውን የትራንስፖርት ኢንተርኘራይዝና የኮባልት ካምፓኒ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ የኢንተርኘራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ ዩቲጄ ቬና ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የተመድ ወታደሮች ከሰርቮች አካባቢ ወጡ

በኮሶቮ የሰርቮች መኖሪያ አካባቢ በተነሳ አመፅ በአካባቢው የተሰማሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላም አስከባሪ ኃይሎች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቢቢሲ ዘገባ መሠረት በአካባቢው በተነሳው አመፅ በትንሹ ሦስት የተመድ ወታደሮችና ሁለት የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት ወታደሮች ቆስለዋል፡፡

በኮሶቮ የሚገኙ ሰርቮች የኮሶቮን የነፃነት እወጃን በመቃወም ባስነሱት በዚሁ አመፅ የቦንብ ፍንዳታና ቃጠሎ ደርሷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወታደሮች ከሀምሳ በላይ ሰርቮችን በቁጥጥር ሥር አውለዋል፡፡

የኮሶቮን የተናጠል የነፃነት እወጃን በተመለከተ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሀሳብ ልዩነት ፈጥረዋል፡፡ በዚህም በርካታ የአባል ሀገራቱ ለኮሶቮ ነፃነት እውቅና ሲሰጡ አንዳንድ ሀገራት ተቃውመዋል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ለሶሶቮ ነፃነት እውቅና የሰጠ ሲሆን ሩሲያ የተቃውሞ አስተያየት ሰንዝራለች፡፡

የቻይና መንግሥት በቲቤት አማፅያን ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዛተ

የቻይና መንግሥት በቲቤት አመፅ የተካፈሉ ሰዎች ላይ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ገልጿል ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

የቻይና መንግሥት አመፁ እንዲያበቃ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ትላንት ተጠናቋል፡፡ በኔፓልና በህንድ የሚገኙ ቲቤታውያን በቻይና መንግሥት ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ በቻይና የሚገኙ ቲቤታውያን ከቻይና ለመገንጠል ባላቸው አቋም አመፅ ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡

የቻይና ቲቤታውያን ሀገሪቱ መንግሥት ላይ እያካሄዱ ያለው አመፅ በቻይና የኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
 
< Prev   Next >