Skip to main content
x

‹‹እያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ልጅ በጉዲፈቻ ቢያሳድግ የጎዳና ተዳዳሪነትን መቅረፍ ይቻላል፡፡››

ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የዓለም የሕፃናት ቀንን አስመልክቶ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ባዘጋጀው መርሐ ግብር ብሌን ገመቹ የተባለች ታዳጊ የተናገረችው ነው፡፡ ኅዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የተካሄደው መርሐ ግብሩ የሕፃናት ፓርላማ አባላት የተለያዩ  ሚኒስትሮችን እንዲወክሉ የተደረገበት ነበር፡፡

‹‹ከኤርትራ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ከባድ የድንበር ጦርነትና ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት የአሜሪካ መንግሥት ቁርጠኛ ነው፡፡››

በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደርና በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአሁኑ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ኃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ ሰኞ ህዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ከዋሺንግተን ዲሲ በስልክ ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ

‹‹አያቴ የዛሬ 50 ዓመት በረገጣት መሬት ታሪክን በመድገሜ ደስተኛ አድርጎኛል፡፡››

ኢትዮጵያን እየጎበኙ ያሉት የኖርዌይ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አልጋ ወራሽ ልዑል ሃኮን ማገኑስ፣ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የክብር አቀባበል ባደረጉላቸው ጊዜ የተናገሩት፡፡

ፍሬከናፍር

«የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝርን በአማርኛ ለመጻፍ የመረጥኩበት ምክንያት፤ አማርኛ እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ የዓለማችን የጽሑፍ ቋንቋዎች አንዱ በመሆኑ ነው። በዓለም እንዲህ ዓይነት ቋንቋዎች ጥቂት ናቸው። ይህ ውብ ፊደላት ያሉት ቋንቋ በኢትዮጵያና በጥቂት ሰዎች በኤርትራ ይነገራል።»

‹‹የግብር ከፋዩን ገንዘብ እያነሳችሁ ማንንም መሸለም አትችሉም፡፡››

የገንብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርሲቲዎችና የፌደራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎችን ለሁለት ቀናት ጠርተው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ ወጪ ቅነሳ በቀረበው መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት አንዱ በስፖንሰርሲፕ፣ በሽልማትና በመሰል ድጋፎች መልክ የሕዝብ ገንዘብ እያነሱ መስጠት እንደማይቻል፣ እንዲህ ያለው ልማድ መቅረት እንደሚገባው ከገለጹት የተወሰደ፡፡

 

 

‹‹በማንኛውም ጊዜ የኑክሌር ጦርነት ሊጀመር ይችላል፡፡››

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰሜን ኮሪያ ምክትል አምባሳደር ኪም ኢን ርዩንግ፣ ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የጦር መሣሪያ ቅነሳ ኮሚቴ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ዋሽንግተን ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ መሠረት፣ ምክትል አምባሳደሩ የኮሪያ ልሳነ ምድር አጠቃላይ ሁኔታ ለኑክሌር ጦርነት መቀስቀስ ጫፍ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

ድሮ እና ዘንድሮ

የመስቀል ደመራ በዓልን ለማክበር የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካቶሊኮስ (ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት) አዲስ አበባ ከተገኙና ካከበሩ በኋላ ኢትዮጵያን በይፋ የጎበኙት የሕንዱ ፕሬዚዳንት ራም ናት ኮቪድ ናቸው፡፡ በሸራተን አዲስ ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር በመሆን የንግድ ማኅበረሰቡን አግኝተው ነበር፡፡

‹‹አሁን በደረስኩበት ደረጃ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስላሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ ለመልቀቅ ድርጅቴንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቄያለሁ፡፡››

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል ተብሎ መሰንበቻውን በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ መሆናቸውን ተከትሎ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም

‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትወርክ ጥራት ማነስ

‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትወርክ ጥራት ማነስ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የሚከናወኑ የፋይናንስ ግብይቶች በተጠቃሚውም በአገልግሎት አቅራቢውም በኩል አስተማማኝ እንዳይሆኑ ከማድረጋቸውም በላይ፣ የፋይናንስ ተቋማት ሰፊ መልክዓ ምድራዊ ሽፋን ያለው የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል፡፡››