Skip to main content
x

ዜና

በደቡብ ኦሞ ዞን ለበርካቶች ሞት ተጠርጣሪ የሆኑ 11 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በደቡብ ኦሞ ዞን ለበርካቶች ሞት ተጠርጣሪ የሆኑ 11 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሰኞ ኅዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ከረፋዱ አሥር ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ ግጭት፣ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡
ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ስያሜውን ቀየረ
ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ስያሜውን ቀየረ
የብርሃን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባንካቸው ሲጠራበት የቆየውን ስም ብርሃን ባንክ በሚል ውሳኔ እንዲተካ ወሰኑ፡፡የባንኩ ባለአክሲዮኖች ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት ዛሬ ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሞተ
በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሞተ
በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ አርብ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት ሲጠፋ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች እንደተጎዱ ታውቋል፡፡ የግጭቱ መነሻ በሁለት ተማሪዎች መካከል የነበረ ጥል እንደሆነና ይህም ወደ ብሔር ግጭት እንዳደገ ታውቋል፡፡
ደም አፋሳሽ ግጭቶች የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤት አለመሆናቸውን ለመተንተን ውይይት ተጀመረ
ደም አፋሳሽ ግጭቶች የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤት አለመሆናቸውን ለመተንተን ውይይት ተጀመረ
በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ‹‹የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤቶች ናቸው›› ለሚሉ አካላት ምላሽ ለመስጠት፣ መንግሥት የፖለቲካ አመራሩንና ሠራተኞችን ማወያየት ጀመረ፡፡ በፌዴራል መንግሥት ደረጃ 80 ገጾች ያሉትና በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለአወያይ አመራሮች ተበትኗል፡፡
በኦሮሚያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ማስጀመር አልተቻለም
በኦሮሚያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ማስጀመር አልተቻለም
በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ትምህርት አለመጀመሩ ታወቀ፡፡ በክልሉ የሚገኙ የአምቦ፣ የመቱና የሃረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መማር ማስተማር ሥራቸው አልገቡም፡፡ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተሰማ ወርቅነህ ዓርብ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከማክሰኞ ኅዳር 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የነበረው የመማር ማስተማር ሒደት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡
ብሮድካስት ባለሥልጣን በአዋጅ መጓተት ተልዕኮዬን መወጣት  አልቻልኩም አለ
ብሮድካስት ባለሥልጣን በአዋጅ መጓተት ተልዕኮዬን መወጣት አልቻልኩም አለ
አንድ ክልል በማዕከላዊ ዲጂታል ኔትወርኩ ለመታቀፍ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሏል አራት በሳተላይት የሚሠራጩ ጣቢያዎች የባለቤትነት ይዞታቸውን እንዲያዛውሩ ታዘዘ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የአገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሥርጭት ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለመቀየርና ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን የቴሌቪዥን ሥርጭቶች ለመቆጣጠር የሚያስችል የሕግ ረቂቅ ባለመፅዱቁና ለዓመታት በመጓተቱ፣ የፕሮጀክት ሥራዎቹ ለማከናወን እንቅፋት እንደገጠመው አስታወቀ፡፡
ከ660 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ለመርዳትና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ አለች
ከ660 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ለመርዳትና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ አለች
በመስከረም ወር በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተቀሰቀሰ ግጭት ለተፈናቀሉ ከ660 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ እገዛ ለማድረግ ፍላጎቱ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ማስታወቂያ

ዓለም

የየመን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዓሊ አብደላ ሳላህ ግድያ አንድምታ
የየመን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዓሊ አብደላ ሳላህ ግድያ አንድምታ
የመንን ለ33 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩትና በአገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2011 በተቀሰቀሰ አብዮት ምክንያት በ2012 ሥልጣን የለቀቁት ዓሊ አብደላ ሳላህ፣ ሰኞ ኅዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም.   በቀድሞ አበሮቻቸው መገደላቸው ተሰምቷል፡፡
ኑሮ በባለ አምስት ኮከቡ የሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤት
ኑሮ በባለ አምስት ኮከቡ የሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤት
በወርቅ ቅብ የተንቆጠቆጠውና ለሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ድምቀትን የሚፈነጥቀው ባለ አምስት ኮከብ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል፣ ዛሬ እንደ ቀድሞው ለሀብታሞች የቅንጦት መስተንግዶ እየሰጠ አይደለም፡፡ ለዓይን የሚማርኩ አዳራሾቹ፣ የዋና ሥፍራው፣ መኝታ ቤቶቹና ሌሎችም አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎቹ የልዑላን ዓይነት መስተንግዶ ፈልገው ከሳዑዲም ሆነ ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን ማስተናገድ ካቆሙም ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡
ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ በመጨረሻው ሰዓት
ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ በመጨረሻው ሰዓት
ለ37 ዓመታት በዘለቀው አገዛዛቸው የሚታወቁትና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የመሰላቸውን ያለ ይሉኝታ በመናገር ተጠቃሽ የሆኑት፣ በ93 ዓመት ዕድሜያቻው ፕሬዚዳንት በመሆናቸው የዓለም አንጋፋው ርዕሰ ብሔር በመሆን የዓለም መነጋገሪያ በመሆን የሚታወቁት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ እ.ኤ.አ. በ2008፣ ‹‹ሥልጣን ላይ ያመጣኝ አምላክ ብቻ ነው የሚያወርደኝ፤›› ሲሉ በምርጫ ዘመቻው ወቅት መናገራቸው፣ ከበርካታ ለጥቅስ ከበቁ አባባሎቻቸው መካከል ይታወሳል፡፡
ሊባኖስን ሥጋት ላይ የጣለው የሳዑዲና የኢራን የውክልና ጦርነት ፍጥጫ
ሊባኖስን ሥጋት ላይ የጣለው የሳዑዲና የኢራን የውክልና ጦርነት ፍጥጫ
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት 11 ልዑላኖችን ጨምሮ 200 ባለሀብቶችን ከሙስና ጋር በተያያዘ ነው በማለት በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ነግሷል፡፡ የኢኮኖሚው መዋዠቅና በሳዑዲ የአክሲዮን ገበያ ማሽቆልቆል ለአገሪቱም ሆነ ለአካባቢው አገሮች የኢኮኖሚ ቀወስ አመላካች መሆኑም ይነገራል፡፡
‹‹ውስጠ ወይራ›› የተባለው የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑላንና ባለሀብቶች እስር
‹‹ውስጠ ወይራ›› የተባለው የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑላንና ባለሀብቶች እስር
ለሳዑዲ ዓረቢያ ልዑላን ቤተሰቦች፣ ጎምቱ ባለሀብቶች፣ እንዲሁም ሚኒስትሮች የቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት መልካም አልነበረም፡፡ አሥራ አንድ ልዑላን፣ በሥራ ላይ የነበሩ አራት ሚኒስትሮችና ቁጥራቸው ያልተገለጸ የቀድሞ ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ባለሀብቶች ቀድሞ የተቀነባበረ ነው በተባለ ሴራ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
በዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ መሪዎች ላይ የተመሠረተው ክስ
በዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ መሪዎች ላይ የተመሠረተው ክስ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ. በ2016 ባደረጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ፣ የቅስቀሳውን ዘመቻ ይመሩ በነበሩ አባላትና በሩሲያ መካከል ግንኙነት ነበር በሚል ጥርጣሬ መጫር የጀመረው በዚያው ጊዜ ቢሆንም፣ ጉዳዩ በይፋ እንዲጣራና ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ ምርመራዎች የተጀመሩት ዘንድሮ ነው፡፡
ማስታወቂያ

ምን እየሰሩ ነው?

ለከፋ አደጋ የተጋለጡት የአክሱም ሐውልቶችና ቅርሶች
ለከፋ አደጋ የተጋለጡት የአክሱም ሐውልቶችና ቅርሶች
የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዲናና መንግሥት የነበረችው አክሱም፣ ተመራማሪዎች እንደሚገልጿት የኃያል መንግሥት ዋና ከተማ፣ ቀጥሎም የሃይማኖት ማዕከል ብሎም የጥንት ሃይማኖታዊ መንግሥት በአፍሪካ ውስጥ የመሠረተች፣ አሁንም በርካታ ምዕመናን የምታስተናግድ የተቀደሰች ከተማ ነች፡፡ በውስጧም እጅግ በጣም የተቀደሰው ጽላትና የክርስትና ሃይማኖት የተለየው መገለጫ ይገኛል፡፡
ብራናዎቹን ማን ይታደጋቸው?
ብራናዎቹን ማን ይታደጋቸው?
ኢትዮጵያ የዓለም ቅርስ ከሆኑት እነዚህ ጥንታውያን መጻሕፍት ባሻገር  የበርካታ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ መስጊዶችና ሌሎችም ተቋሞች የቅርሶቹ ቀዳሚ መገኛ ሥፍራ ናቸው፡፡ ጥንታውያኑ መጻሕፍት አገር በቀል ዕውቀትን አምቀው እንደመያዛቸው ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው መረጃ የሚሸጋገርባቸው ድልድዮችም ናቸው፡፡ ድርሳናት እንደሚጠቁሙት፣ በጥንታውያን ገዳማትና መስጊዶች የሚገኙ የጽሑፍ ቅርሶች ምን ዓይነት ይዘት ያላቸው መጻሕፍት፣ በምን ያህል መጠን፣ በየትኛው ተቋም፣ እንደሚገኙ በቅጡ አለመታወቁ ቅርሶቹ ለስርቆት ከሚዳረጉባቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡
እንቆቅልሽ የሆነው የወተት ምርት
እንቆቅልሽ የሆነው የወተት ምርት
 ኢትዮጵያ በቀንድ ከብቶች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ፣ በዓለም ከ10 አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም ከወተት ሀብቷ ማግኘት የሚገባትን ያህል ጥቅም እያገኘች ስላለመሆኗ ይወሳል፡፡ በሌላ በኩልም ሌላው ዓለም ባለው የእንስሳት ቁጥር ልክ ወተትን በየገበታው በተለያየ መልኩ ሲጠቀም እንደሚታይ በኢትዮጵያ ግን ባሉት እንስሳት ልክ ኅብረተሰቡ ተጠቃሚ አለመሆኑ ይነገራል፡፡
‹‹አንድ ልጅ ሲደመር አንድ ላፕቶፕ አንድ ትልቅ ቢዝነስ ይሆናል››
‹‹አንድ ልጅ ሲደመር አንድ ላፕቶፕ አንድ ትልቅ ቢዝነስ ይሆናል››
አቶ ቴድሮስ ታደሰ፣ የሴንተር ፎር አፍሪካ ሊደርሺፕና የኤክስ ሀብ አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴድሮስ  ታደሰ የሴንተር ፎር አፍሪካ ሊደርሽፕ ስተዲስና የኤክስ ሀብ አዲስ መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ሴንተር ፎር አፍሪካን ሊደርሽፕ ስተዲስ የተቋቋመው ከስድስት ዓመታት በፊት ነው፡፡ የማማከር አገልግሎት፣ የወጣቶችና የሴቶች አመራር ብቃት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥልጠናዎችንም ያከናውናል፡፡ የድርጅቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴና በወጣቶች የፈጠራ ሥራዎች የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ሻሂዳ ሁሴን አቶ ቴድሮስ ታደሰ አነጋግራቸዋለች፡፡
‹‹ተግባራዊ ሳይንስ በአገራችን ገና አልዳበረም››
‹‹ተግባራዊ ሳይንስ በአገራችን ገና አልዳበረም››
አቶ ኢዩኤል ኃይሉ፣ የስቴም ሲነርጂ የቴክኖሎጂ ኃላፊ ስቴም ሲነርጂ ከስምንት ዓመት በፊት የተቋቋመ የተራድኦ ድርጅት ነው፡፡ በምሕፃረ ቃል ስቴም የሚባለው ድርጅቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢንጂነሪንግና ማቴማቲክስ (ሒሳብ) የሚሠራ ሲሆን፣ 13 ማዕከሎች በተለያዩ አካባቢዎች አቋቁሟል፡፡ ታዳጊዎች በተግባር የተደገፈ የሳይንስ ሥልጠና እንዲያገኙ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ፣ የሳይንስ ሙዚየሞች በማቋቋምና ሳይንሳዊ ውድድሮች በማካሄድም ይታወቃል፡፡
የምርት ጥራት ከቀበሌ ጀምሮ ቅድሚያ ካልተሰጠው በምርት ገበያ ብቻ በሚደረግ ቁጥጥር የትም አይደረስም
‹‹የምርት ጥራት ከቀበሌ ጀምሮ ቅድሚያ ካልተሰጠው በምርት ገበያ ብቻ በሚደረግ ቁጥጥር የትም አይደረስም››
ዶ/ር ብርሃኑ አምሳሉ፣ የመልካሳ ማዕከል የቆላ ጥራጥሬ ሰብሎች ምርምር አስተባባሪና ተመራማሪ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሥር በሚገኘው የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የቦሎቄ ተመራማሪ ዶ/ር ብርሃኑ አምሳሉ  በማዕከሉ የቆላ ጥራጥሬ ምርምር ሥራዎችን በኃላፊነት ያስተባብራሉ፡፡