Skip to main content
x

ዜና

በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ለዶ/ር መረራ ጉዲና አቀባበል አደረጉ
በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ለዶ/ር መረራ ጉዲና አቀባበል አደረጉ
ዛሬ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀትር በኃላ ለዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር ቤት መለቀቃቸውን ተከትሎ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በዶክተሩ መኖሪያ አካባቢ ተገኝተው አቀባበል አደረጉላቸው። የተጠረጠሩበት ክስ በመንግሥት ተቋርጦ ከእስር ቤት የተለቀቁት ዶ/ር መረራ፣ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ በሚወስደው ዋና መንገድ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከቀትር በኃላ ገብተዋል፡፡
ግብፅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የለኝም አለች
ግብፅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የለኝም አለች
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በቀጥታ በቴሌቪዥን ለግብፃውያን ባስተላለፉት መልዕክት፣ አገራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የላትም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ‹‹በቀጣናው ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ጠንቅቀን የምናውቅ በመሆኑ ግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአገሮችን ሉዓላዊነት አትደፍርም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ግብፅ ከወንድሞቿ ጋር ወደ ጦርነት አትገባም፡፡ ምክንያቱም ሰላም አንዱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፤›› ማለታቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ‹‹ከማንኛቸውም ጎረቤቶቻችን ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ዕቅዱም ሆነ ፍላጎቱ የለንም፤›› ሲሉ በቀጥታ በተላለፈው የቴሌቪዥን ሥርጭት መናገራቸውን የዜና አውታሮች ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የሠራተኞች ደመወዝ ብዝበዛ ነው ሲል ወቀሰ
ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የሠራተኞች ደመወዝ ብዝበዛ ነው ሲል ወቀሰ

የዓለም አቀፍ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሏቸው ክፍያዎች ዝቅተኛ በመሆናቸው ወቀሳ

መንግሥት በፍርድ ቤቶች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚፈጥሩ ተጠርጣሪዎችን አስጠነቀቀ
መንግሥት በፍርድ ቤቶች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚፈጥሩ ተጠርጣሪዎችን አስጠነቀቀ
ተጠርጥረው የተከሰሱበት ጉዳይ በፍርድ አደባባይ እየታየ በችሎቶች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር የጀመሩ ተከሳሾችም ሆኑ ሌሎች ተጠርጣሪዎች፣ ክስ ማቋረጥም ሆነ ምሕረት ማድረግ ማለት የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ይቆማል ማለት እንዳልሆነ አውቀው፣ የሕግ የበላይነትን ማክበር እንዳለባቸው መንግሥት አስጠነቀቀ፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና ጨምሮ የ22 ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ
ዶ/ር መረራ ጉዲና ጨምሮ የ22 ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ
በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ጉዳያቸውን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በቀጠሮ በመከታተል ላይ የነበሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና እና 22 ተከሳሾች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑ ተረጋገጠ፡፡ በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ፊርማ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ ዶ/ር መረራም ሆኑ ሌሎች በክስ ላይ የነበሩ ተከሳሾች ክሳቸው ተቋርጧል፡፡
‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን››
‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን››
የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በመገንባት ጫናውን ለብቻቸው እንደተሸከሙ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን መልዕክት ሲያደርስና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በተነጋገረበት ወቅት መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የልማት ባንክን የተበላሸ ብድር ለማስተካከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ
የልማት ባንክን የተበላሸ ብድር ለማስተካከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ 25.3 በመቶ የሚሆነው የተበላሸ ብድር በመሆኑ፣ ይኼንን የተበላሸ ብድር ምጣኔ ወደ ገደቡ ለመመለስ በባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቋመ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ገደብ ያስቀመጠ ቢሆንም፣ የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር መጠን 25.3 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

አወዛጋቢው የትራምፕ ንግግር
አወዛጋቢው የትራምፕ ንግግር
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዓመት በፊት ከነበረው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ጀምሮ ለስደተኞች ያላቸው አቋም አሉታዊ ነው፡፡ ‹‹ወንጀለኞች ናቸው›› የሚሏቸውን የሜክሲኮ ስደተኞች ለመቆጣጠር በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር መካከል ግንብ እንደሚያስገነቡም የተናገሩት በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ነበር፡፡ ስደተኞች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉም እንዲሁ፡፡
የዶናልድ ትራምፕን የመምራት ብቃትና የዋይት ሐውስን ውጥንቅጥ ያብጠለጠለው አወዛጋቢ መጽሐፍ
የዶናልድ ትራምፕን የመምራት ብቃትና የዋይት ሐውስን ውጥንቅጥ ያብጠለጠለው አወዛጋቢ መጽሐፍ
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን የኑክሌር መሣሪያ ፕሮግራማቸውን የሚያዩት አገራቸውን ከአሜሪና ከደቡብ ኮሪያ ሊሰነዘር ከሚችል ጥቃት እንደ መከላከያ አድርገው ነው፡፡ ሁለቱ የሰሜን ኮሪያ ተቀናቃኞች ግን ይህን አይቀበሉትም፡፡ ሁሌም የሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ፕሮግራም እንደ ኮነኑ፣ በልሳነ ምድሩም የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንዳደረጉ ነው፡፡
ዓለማችንን በትምባሆ ኢንዱስትሪ ከተደቀነባት አደጋ እንዴት እንታደጋት?
ዓለማችንን በትምባሆ ኢንዱስትሪ ከተደቀነባት አደጋ እንዴት እንታደጋት?
ትምባሆና ከትምባሆ ጋር ተያያዥ የሆኑ ምርቶች ለጤና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ጠንቅ አንደሆኑና በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየጎዳ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትልልቅ ዓለም አቀፍ የትምባሆ አምራች ኩባንያዎች፣ ምርታቸው ጤና ላይ ሰለሚያደርሰው ጉዳት ለዘመናት አሳሳች የሆነና የውሸት መረጃዎችን ሲያወጡና ሲፈበርኩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡
ሊቢያ ውስጥ መፈናፈኛ ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን የመታደግ አዲስ ጅምር
ሊቢያ ውስጥ መፈናፈኛ ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን የመታደግ አዲስ ጅምር
በቅርቡ በሲኤንኤን አማካይነት የተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምሥል ሊቢያን የስደተኞች የምድር ገሃነም አድርጓታል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለማሰብ የሚከብድ የባሪያ ንግድ የሚካሄድባት አገር መሆኗ ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ በተለይ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች ስደተኞች በሊቢያ ውስጥ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው መከራ የሚያዩበት፣ በአገሬው ሰዎች ሳይቀር ጉልበታቸው በነፃ የሚበዘበዝበት፣ በተጨናነቁ እስር ቤቶች ስቃይ የሚፈጸምባቸው፣ ከዝርፊያ በተጨማሪ ግድያ ሳይቀር የሚፈጸምባቸው ስደተኞች በመቶ ሺዎች ይቆጠራሉ፡፡
የኤኤንሲ አዲሱ መሪ ሲሪል ራማፎሳ
የኤኤንሲ አዲሱ መሪ ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካ አውራ ፓርቲ ‹‹አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ›› (ኤኤንሲ) በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ወደ አንድ ያመጣሉ የተባሉትን ሲሪል ራማፎሳ መሪ አድርጎ መርጧል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራውን ኤኤንሲ የሚረከቡት ባለሀብቱ ራማፎሳ፣ በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስናም ያስተነፍሳሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡ አገሪቱም እ.ኤ.አ. በ2019 ለምታደርገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም  ራማፎሳ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሆኖም በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል ሊፈጠር ይችላል ተብሏል፡፡
ቨላድሚር ፑቲን በዶናልድ ትራምፕ ላይ የበላይነት ያስገኘላቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ድንገተኛ ጉብኝት
ቨላድሚር ፑቲን በዶናልድ ትራምፕ ላይ የበላይነት ያስገኘላቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ድንገተኛ ጉብኝት
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሰንበቻውን በመካከለኛው ምሥራቅ ነውጥ የፈጠረ ድርጊት ከፈጸሙ ከቀናት በኋላ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ በመካከለኛው ምሥራቅ ያልተጠበቀ ጉብኝት በማድረግ የበላይነቱን ይዘዋል፡፡ ትራምፕ የእስራኤል ዋና ከተማ ኢየሩሳሌም መሆኗን ዕውቅና በመስጠት የአሜሪካ ኤምባሲ ወደዚያ እንደሚዛወር አስደንጋጭ ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ተቃውሞ ተቀስቅሶባቸዋል፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ምን እየሰሩ ነው?

የሦስት አሠርታት የረድዔት ጉዞ
የሦስት አሠርታት የረድዔት ጉዞ
የካናዳ ክርስቲያናዊ የሕፃናት መርጃ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ተሠማርቶ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ማከናወን ከጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል፡፡ ድርጅቱ እስካሁን ባከናወናቸውና ወደፊት ሊሠራ ባቀዳቸው እንቅስቃሴ ዙሪያ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ፈለቀ ታደለ (ዶ/ር)ን ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡
‹‹ለየት የሚያደርገን ሰሊጥን በብቸኝነት ወደ ደቡብ ኮሪያ መላካችን ነው››
‹‹ለየት የሚያደርገን ሰሊጥን በብቸኝነት ወደ ደቡብ ኮሪያ መላካችን ነው››
ተወልደው ያደጉት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ነው፡፡ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአክሱም ከተማ በመማር ላይ እያሉ በድንገት ታላቅ ወንድማቸውን ፍለጋ በ1966 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡
ለወደፊት ስኬት መሠረት የሚጣልበት ልጅነት
ለወደፊት ስኬት መሠረት የሚጣልበት ልጅነት
ወ/ሮ አሰፋች ኃይለ ሥላሴ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝ አፍሪካ (ዩኒሳ) በሳይኮሎጂ ከሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ላይ አተኩሮ አግኝተዋል፡፡ ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በማማከር ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አካል ጉዳተኛ ሕፃናትና ወጣቶች ላይ ሠርተዋል፡፡
የአካል ጉዳተኞች ድምፅ
የአካል ጉዳተኞች ድምፅ
ተስፋዬ ገብረማርያም የቲኤፍቲ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነው፡፡ የሚንቀሳቀሰው በክራንች በመታገዝ ነው፡፡ ሁለት እግሩን ያለ ድጋፍ እንዳይንቀሳቀስ ያደረገው የአካል ጉዳት የደረሰበት ገና ልጅ ሳለ ነበር፡፡ አጋጣሚው ሮጦ ላልጠገበው ተስፋዬና ቤተሰቦቹ ከባድ ሐዘን ውስጥ የከተታቸው ነበር፡፡ በተለይ እናቱ ዳግመኛ ልጅ ለመውለድ እስኪወስኑ ድረስ አጋጣሚው አስደንግጧቸው እንደነበር ተስፋዬ ይናገራል፡፡
‹‹የአይቲ ኢንዱስትሪ በዓለም መሪ ሆኖ ሳለ በአገራችን ግን እንደ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ ይቆጠራል!››
‹‹የአይቲ ኢንዱስትሪ በዓለም መሪ ሆኖ ሳለ በአገራችን ግን እንደ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ ይቆጠራል!››
 ሳይበርሶፍት ባለፉት 19 ዓመታት ለተለያዩ ተቋሞች ልዩ ልዩ ሲስተሞችን የሠራ የአይቲ (ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ተቋም ነው፡፡ የመንግሥትና የግል ተቋሞች በዲጂታል ሲስተም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻልም የድርሻቸውን እየሰጡ ነው፡፡ የፍትሕ፣ የትምህርትና የጤና ተቋሞችን ጨምሮ የ702 ድርጅቶችን ሲስተም አልምተዋል፡፡ በተቋሙ እንቅስቃሴ ዙሪያ የሳይበርሶፍት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተከስተብርሃን ሀብቱን ምሕረተሥላሴ መኰንን አነጋግራቸዋለች፡፡
ሕፃናት የተሻለ እንዲኖሩ የማድረግ ስንቅ
ሕፃናት የተሻለ እንዲኖሩ የማድረግ ስንቅ
የሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) በዓለም ላይ ያሉ ሕፃናት የተሻለ የመኖር ዕድል እንዲያገኙ መሥራት ከጀመረ ከ60 ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ በየአገሮቹ በተቋቋሙ የሕፃናት አድን ድርጅቶች ሥራዎች ሲከናወኑ  ቢቆዩም፣ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰባቱ ድርጅቶች ተዋህደው በአንድ ጥላ ሥር ሆነዋል፡፡ ድርጅቱ ሕፃናት በተለይም ለችግር የተጋለጡ ከችግራቸው እንዲወጡና የተሻለ ሕይወትን እንዲኖሩ ይሠራል፡፡ ከድርጅቶቹ ውህደት በኋላም የተሻለ ውጤት እንደተመዘገበ የድርጅቱ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡