ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ነባርና አዲስ አመራሮች ማድረግ ወይም ማለፍ የማይችሏቸውን ቀይ መስመሮች አሰመሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ያቀረቧቸውን የካቢኔ አባላት ማንነትና የሚሸጋሸጉ ሚኒስትሮችን ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ‹‹የሚሾሙትም ሆነ ባሉበት የሚቀጥሉት እንዲገነዘቡ የምፈልገው፣ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብበት የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከል ግዴታና አንደኛው ቀይ መስመር ነው፤›› ብለዋል፡፡
ዜና
ቢዝነስ | Apr 22
የህንድ የግብርና ምርቶች ኩባንያ ካሩቱሪ ግሎባል በኢትዮጵያ ሲንያንቀሳቅሳቸው የነበሩና በመንግሥት የተወረሱበትን እርሻዎች ዳግም እንደ አዲስ ለማስጀመር፣ ከመንግሥት ጋር ዕርቅ ማውረዱን አስታወቀ፡፡ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥም እንደ አዲስ ስምምነት በመፈረም በጋምቤላ እርሻው ሥራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡
ፖለቲካ | Apr 22
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው በተሾሙት አቶ አሰግድ ጌታቸው ምትክ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አዳሙ አያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡
ፖለቲካ | Apr 22
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሥር ከሚገኙ ሰባት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ፣ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሱ የቆዩ ሥር የሰደዱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታቱን አስታወቀ፡፡
ፖለቲካ | Apr 22
አምስቱ የፍትሕ ተቋማት የሚባሉት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አስታወቁ፡፡
ቢዝነስ | Apr 22
በ120 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ከሦስት ዓመታት በፊት የተጀመረው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ፣ ግንባታው መጠናቀቁንና በሰኔ ወር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ ረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በ37 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፖለቲካ | Apr 19
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የ16 ሚኒስትሮችን ሹመት አቅርበዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡ ተሿሚዎቹም ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡
ለዜና መጽሔታችን ይመዝገቡ
ፖለቲካ
ርዕሰ አንቀጽ
ክቡር ሚኒስትር
ማኅበራዊ
ዓለም
ዓለም | Apr 18
አሜሪካ፣ ፈረንሣይና እንግሊዝ በመተባበር ዓርብ ሚያዚያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ሌሊት የሶሪያ መንግሥት የኬሚካል መሣሪያዎችን ለማምረት ይጠቀምባቸዋል የተባሉ ሦስት ሥፍራዎችን ዒላማ ያደረጉ 105 ሚሳይሎችን ወደ ምዕራብ ሶሪያ አስወንጭፈዋል፡፡
ዓለም | Apr 11
ሶሪያ ከሰባት ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በሕዝብ እምቢተኝነት አምሳል በተነሳው ቀውስና ተከትሎ በመጣው፣ በበሽር አል አሳድ በሚመራው በሶሪያ መንግሥትና በአማፅያን መካከል የሚደረገው የእርስ በርስ ጦርነት ማብቂያ ‹ላም አለኝ በሰማይ› እየሆነ ነው፡፡
ዓለም | Apr 04
‹‹ጊዜ የጣለው ዛፍ ምሳር ይበዛበታል፤›› እንዲሉ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ የቀድሞ የትዳር አጋር ኖምዛሞ ዊኒፍሬድ ዛንዩዌ ማዲኪዜላ ወይም በአጭሩ እንደሚጠሩት ዊኒ ማንዴላ፣ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የነጮች የግፍ አገዛዝ አፓርታይድን ለማጥፋት ካደረጉት ትግልና የቀድሞ ባለቤታቸው ኔልሰን ማንዴላ በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ ባለቤታቸውን ከማበረታታት አንስቶ የአፓርታይድ ትግሉን በማቀጣጠል ከነበራቸው ሚና ይልቅ፣ ነፃ የተባሉባቸውም ሆነ የተፈረዱባቸው የሙስና፣ የማጭበርበርና የግፍ ግድያዎች ክሶች በታሪካቸው ጎልተው ተጽፈዋል፡፡
ዓለም | Mar 28
አምላክ የሞት መልአክ የሆነውን አዛኤል ፕሬዚዳንቱን ይዘህልኝ ና ብሎ ወደ ግብፅ ይልከዋል፡፡ መልአኩም ግብፅ ሲደርስ በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ታስሮና ተደብድቦ፣ ተሰቃይቶ ይለቀቅና ወደ አምላኩ ይመለሳል፡፡ ይኼንን ያየው አምላክ ‹እኔ እንደላኩህ አልነገርካቸውም አይደል?› ሲል ይጠይቀዋል፡፡
ዓለም | Mar 21
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ቭላድሪሞቪች ፑቲን እ.ኤ.አ. ማርች 18 ቀን 2018 እንዲካሄድ ቀን የተቆረጠለትን ምርጫ እንደሚያሸንፉ ሳይታለም የተፈታ እንደሆነ የተረዱት ምዕራባውያን የመገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫውን ውጤት በቅድመ ትንበያ የድምፅ መለኪያዎች ተንብየው የፑቲንን ማሸነፍ ካወጁ ቆይተዋል፡፡
ዓለም | Mar 14
ለዓመታት አሜሪካን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚያስችሉ የኑክሌር መሣሪያዎችን ሠርቻለሁ በማለትና የተለያዩ የኑክሌር አረር የተገጠመላቸው ሚሳይሎችን ስትሞክር የቆየችው ሰሜን ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ማሳየቷ ብዙዎች በግርምትና በአድናቆት የተመለከቱት ሁነት ነበር፡፡
ምን እየሰሩ ነው?
ምን እየሰሩ ነው? | Apr 11
ብርጋዴር ጄኔራል ደስታ ገመዳ በክብር ዘበኛ ጦር አካዴሚ ሠልጥነው ከወጡ የመጀመርያው ዙር ተመራቂዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ መታሰቢያነቱ እሳቸውን ጨምሮ የአካዴሚው የመጀመርያ ኮርስ የጦር መኰንኖች የሆነና ታሪካቸውን የሚያወሳ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡
ምን እየሰሩ ነው? | Apr 04
አቶ ሰናይ መኰንን የአይከን ኢትዮጵያ ሮቦቲክስ ኤዱኬሽን ኤንድ ኮምፒቲሽን ማዕከል መሥራች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2011 የተመሠረተው አይከን ኢትዮጵያ ታዳጊዎችን በዲዛይን ኢንጂነሪንግና ፕሮግራሚኒንግ የማብቃት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማስቻል ሥራ ይሠራል፡፡ ድርጅቱ ለታጊዎቹ መሠረታዊ የሮቦቲክስ ጽንሰ ሐሳብና ሌሎች ወሳኝ ቀመሮችን ካስተማረ በኋላ እርስ በርስ እንዲወዳደሩ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጥተው በሌላው የዓለም ጫፍ ከሚገኙ አቻዎቻቸው እንዲወዳደሩ ያደርጋል፡፡
ምን እየሰሩ ነው? | Mar 28
አቶ ኖኅ አዝሚ ሳማራ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሠራና አዝሚ ዩኤስኤ ኤልኤልሲ ኩባንያ መሥራች፣ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ሲሆን፣ የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመርያና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ተወልደው ባደጉበት ከተማ አዲስ አበባና ዳሬሰላም ታንዛኒያ ውስጥ ነው፡፡ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ እንግሊዝ አገር አቅንተው የመሰናዶ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡
ምን እየሰሩ ነው? | Mar 21
አቶ ሙላት ፎጌ የአማጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው በማምረት፣ በትራንስፖርትና በወጪና ገቢ፣ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የተሠማራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጀቱም በቤተሰብ የተቋቋመ ነው፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርጅታቸው ‹‹ለመጀመርያ ጊዜ›› የእንቦጭ አረም መከላከያ ማሽን ከቻይና ከሁለት ሚሊዮን ብር በመግዛት አገር ውስጥ አስገብቷል፡፡
ምን እየሰሩ ነው? | Mar 14
በግእዝ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያለው የነገሥታት ውሎና ጉዞ የሚያትተው ዜና መዋዕል በተለይ ከ14ኛው ምዕት ጀምሮ ከሙያ መዋሉ ይገለጻል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ባሉት ዘመናት በአክሱም ከመጀመርያ መቶ ዘመን ወዲህም ታሪክ ጠቀስ ጽሑፎች በድንጋይ ላይም ሆነ በብራና ላይ ለመጻፋቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡
ምን እየሰሩ ነው? | Mar 07
የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ የተቋቋመው አምና 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ በመላው አገሪቱ በጥቃቅን፣ ታዳጊና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁ 2000 ማኅበራት አማካይነት የተመሠረተ ነው፡፡