Skip to main content
x

‹‹መሥራችና ባለቤት›› እና ‹‹መጤ›› ብሔረሰቦች ግንኙት ከሕገ መንግሥቱ አንፃር

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአገራዊ ማንነትና የአገር ግንባታ ጉዳይ ለብዙዎች አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡ ጉባዔዎች እየተካሄዱ ነው፡፡ የተወሰኑ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ለእነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው በመወያየትም ላይ ይገኛሉ፡፡ የተወሰኑ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድርጅቶችም እነዚህን ውይይቶችና የራሳቸውንም ፕሮግራም በማዘጋጀት ለሕዝብ እያስተላለፉ ነው፡፡

በዘገየ ንግድ አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የአጓጓዡ ኃላፊነት

በ1952 ዓ.ም. የወጣው የንግድ ሕግ ሥርዓት ካበጀላቸው ጉዳዮች መካከል የማጓጓዝና የማመላለስ ሥራ አንዱ ነው፡፡ የንግድ ሕጉ በሦስተኛው ክፍሉ ኢንሹራንስን ጨምሮ ለእነዚህ ጉዳይ ደንብ ሠርቷል፡፡ በባህር ላይ የሚደረግ የማጓጓዝ ተግባርን በሚመለከት የተለየና ራሱን የቻለ በዚሁ ዓመት የወጣ ሕግ አለ፡፡ የንግድ ሕጉ ትኩረት የሰጠባቸው በየብስና በአየር የሚደረጉ የማጓጓዝና የማመላለስ አገልግሎት ነው፡፡

የሥራ ማቆም መብትና እጅግ አስፈላጊ የሕዝብ አገልግሎት በኢትዮጵያ ሕግ

በሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በዚሁ ‹‹በሕግ አምላክ›› ዓምድ ከላይ በተገለጸው ርዕስ ክፍል አንድ ሆኖ የቀረበ ጽሑፍ ነበር፡፡ በዚህ ደግሞ ሁለተኛውን ክፍል እንቀጥላለን፡፡ የሚያተኩረው አስፈላጊ አገልግሎት የሚባሉት የሥራ ዘርፎች ውስጥ የተሠማሩ ሠራተኞች የሥራ ማቆም መብት ላይ ያለው ገደብ ነው፡፡

የማንነት ጥያቄ አወሳሰን በሕገ መንግሥቱ ወልቃይት በምሳሌነት

በቅርቡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መቐሌ ላይ ያደረጉትን ንግግር ተመርኩዞ የወልቃይት ጥያቄ አጀንዳ ሆኗል፡፡ እንግዲህ በአገራችን የተመሠረተው ፌዴራላዊ ሥርዓት ብሔርን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የብሔር ጉዳዮችን ለመፍታት ከሄዱበት መንገድ የተለየና ድፍረት የተሞላበት ስለመሆኑ በርካቶች ይስማማሉ፡፡

የሥራ ማቆም መብትና እጅግ አስፈላጊ የሕዝብ አገልግሎት በኢትዮጵያ ሕግ

ባለፈው ሳምንት በሠራተኞች የሥራ ማቆም ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተወሰኑ ሰዓታት ዓለም አቀፍ በረራዎች መስተጓጎላቸው ይታወቃል፡፡ የሥራ ማቆምን ምንነት፣ የመብቱን ይዘት፣ ገደብና ክልከላዎችን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሕግ አንፃር መቃኘት የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡

አገሪቱን ለማከም ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ ማከም በውብሸት ሙላት

አገራችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በአለመረጋጋትና በሰላም ዕጦት ውስጥ ከርማለች፡፡ ለሰላም ዕጦቱ ወይም አለመረጋጋቱ መነሻቸው ምንም ይሁኑ ምን፣ በዚህ ሰበብ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡ የአካል መጉደል ደርሷል፡፡ ንብረት ወድሟል፡፡ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡

ብሔራዊ ማንነትና ኢትዮጵያዊነትን እኩል ለማለምለም የሕገ መንግሥቱ ሚና

ሰሞኑን ለአገራችን ታላቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው የገዥው ፓርቲ፣ ኢሕአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ነው፡፡ ምርጫው ረዘም ያለ ጊዜ ወስዷል፡፡ አጀንዳነቱም ከፓርቲው አልፎ የመላው ሕዝብ ሆኗል፡፡ በተለይ ደግሞ አገሪቱን ካጋጠማት አለመረጋጋት ጋር ተያይዞም ሕዝብ አጀንዳነቱ በአንድ ፓርቲ (ግንባር) ውስጥ የሚደረግ እስከማይመስል ድረስ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ሕዝቡ የተለያዩ ፍላጎቶችን በማሳደሩ ከእነዚህ ፍላጎቶች አኳያ በመመዘን በተለያዩ ሚዲያዎች ማንፀባረቁ አጀንዳነቱን አጠናክሮታል፡፡

በጋብቻ ላይ ጋብቻና የሴቶች በገጠር መሬት የመጠቀም መብት

በጋብቻ ላይ ጋብቻ በዓለም ላይ ካሉት አገሮች 25 በመቶ በሚሆኑት አንድ ባል ሁለትና ከዚያ በላይ ሚስት (polygyny) ማግባትን የሚፈቅዱ ሲሆን፣ አንድ ሚስት ብዙ ባሎችን ማግባት (polyandry) ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ አንዳንድ አገሮች አንድ ባል ሁለትና ከዚያ በላይ ሚስት እንዲኖረው የሚፈቅዱት ለእስልምና እምነት ተከታይ ማኅበረሰቦች ብቻ ነው፡፡

በሦስት መንግሥታት የወጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ሲነፃፀሩ

አገራችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት መተዳደር ከጀመረች አንድ ወር አልፎታል፡፡ በተለመደውና በመደበኛው የሕግ አሠራር ሳይሆን ከወትሮው በተለየ አኳኋን በመተዳደር ላይ ናት ማለት ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሕግ ለመተዳደር መነሻ የሚሆኑት በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 ላይ ተገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ አንዱ በተከሰተ ጊዜ የፌዴራል መንግሥቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል፡፡

በንብ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ያረጋገጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ

የስም ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብኛል በማለት ክስ የመሠረቱት የቀድሞ የንብ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታፈሰ ቦጋለ ገብረ ወልድ፣ ስማቸው ስለመጥፋቱ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ በማቅረብና በማረጋገጥ ተቀናቃኛቸውን አቶ ኮሬ ባዌ ጨረቶን አሸነፉ፡፡ በስም ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል አቶ ታፈሰ የመሠረቱባቸውን የወንጀል ክስ ማስተባበል ወይም በበቂ ሁኔታ ተከራክረው መርታት ባልቻሉት አቶ ኮሬ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የገንዘብ ቅጣት ጥሎባቸዋል፡፡