Skip to main content
x

ደቡብ ግሎባል የተከፈለ ካፒታሉን 620 ሚሊዮን ብር አድርሳለሁ አለ

ከ16ቱ የግል ባንኮች የባንክ ኢንዱስትሪውን ዘግይቶ የተቀላቀለው ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2009 ሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 67.7 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አስታወቀ፡፡ የተከፈለ ካፒታሉንም ወደ 500 ሚሊዮን ብር አደርሳለሁ ብሏል፡፡

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ

ከአንድ ሚሊዮን በታች (እንደ ዓለም ባንክ የዓምና ትንበያ ለ940 ሺሕ በላይ) የሚቆጠር ሕዝብ እንዳላት የሚነገርላት የጂቡቲ ሪፐብሊክ፣ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው የሁለቱ አገር ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል፣ በአኗኗር፣ በሃይማኖትና በሌላም አኳኋን በደም የሚዛመዱ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት አገር ነች፡፡

ብርሃንና ቡና ባንክ የምርት ገበያን ሥርዓት ተቀላቀሉ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ክፍያና ርክክብ ለሚያስፈጽሙ ሁለት ባንኮች ተጨማሪ ባንኮች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው ባንኮች ቁጥር 12 ማድረሱንና ለተመሳሳይ ሥራ አምስት ባንኮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

በአገር ውስጥ ለሚከናወኑ ግዥዎች ከውጭ መክፈል የሚቻልበት ሥርዓት ተዘረጋ

በውጭ የሚኖሩ አፍሪካውያን በተለይም ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው ለተለያዩ አገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም የሚችሉበት ‹‹መላ›› የተሰኘ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ሥራ ጀመረ፡፡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የስልክ፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የዕድር፣ የትምህርት ቤት፣ የሆስፒታል፣ የኢንሹራንስና ሌሎች የቤተሰቦቻቸውን የቤት ውስጥ ወጪዎችን ጭምር መክፈል የሚችሉበት ሥርዓት ሲሆን፣ ሥርዓቱን የዘረጉት ክፍያ ፋይናንሺያል ሰርቪስና ማስተር ካርድ በጥምረት ሆነው ነው፡፡

ብርሃን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ወደ 1.4 ቢሊዮን ብር አሳደገ

ከፍተኛ ባለአክሲኖችን በማሰባሰብ ቀዳሚ ሆኗል ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው የ2009 የሒሳብ ዓመት ብቻ ከአምስት ሺሕ በላይ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን በማሰባሰብ የባለአክሲዮኖቹን ቁጥር ከ14 ሺሕ በላይ እንዳደረሰና የተከፈለ ካፒታሉን 91 በመቶ በማሳደግ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ እንዳሳደገ ተገለጸ፡፡

ፅዳት በየወሩ የመጨረሻዋ ቅዳሜ

ለአዲስ አበባ ከተማ ከ1956 ዓ.ም. ጀምሮ ለቆሻሻ መጣያነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በ37 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈው ረጲ በዘልማድ ‹‹ቆሼ›› የሚባለው በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለቆሻሻ መጣያነት የተመረጠው በወቅቱ ከከተማው ወጣ ብሎ ስለሚገኝና በነዋሪዎች ላይ ምንም ዓይነት የጤና ችግር እንደማያደርስ ስለታመነበት ነበር፡፡  

ብሔራዊ ባንክ በአስመጪዎች ከመሸጫ ዋጋቸው በታች የሚቀርቡ ደረሰኞች እንዳይስተናገዱ መመርያ አወጣ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ ወደ አገር የሚገቡ ምርቶችና ሸቀጦች ከዓለም አቀፍ ዋጋቸው በታች በሆነ ሒሳብ በባንኮች በኩል ይከፈቱላቸው የነበሩ የቅድመ ክፍያ ሰነድ (ሌተር ኦፍ ክሬዲት - ኤልሲ)፣ ካሁን በኋላ በትክክለኛ ዋጋቸው እንዲስተናገዱ የሚያስገድድ መመርያ በቅርቡ አወጣ፡፡

የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመገንባት ቢስማሙም መቀናጀት ተስኖአቸዋል

ተጠያቂው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ይቀርብበታል ተብሏል በኢትዮጵያ የሚገኙ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ተቋማት በአዲስ አበባ ያሏቸውን ፕሮጀክቶች ተናበው ለማካሄድ ቢስማሙም፣ ቅንጅቱ የተሟላ ባለመሆኑ ስምምነታቸው ፈተና ገጥሞታል፡፡ ተቀናጅተው እየሠሩ ባለመሆኑ ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ የሚሆኑ ኃላፊዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሚሰበስቡት ስብሰባ ሪፖርት ይቀርብባቸዋል ተብሏል፡፡

የአይኤምኤፍ ኃላፊ ለሁለት ቀናት ቆይታ እንደሚመጡ ይጠበቃል

ጠቅላይ ሚስትሩን ጨምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ያነጋግራሉ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስቲያን ላጋርድ፣ ከሐሙስ ታኅሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት ቆይታ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ክሪስቲያን ላጋርድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ሲጠበቅ፣ በማግሥቱ ማለትም ታኅሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት በሚካሄደው የውይይት መድረክ ንግግር እንደሚያሰሙ ታውቋል፡፡

በኤሌክትሪክ ማመንጨት ለሚሰማሩ የግል ኩባንያዎች የተቀመጠው የማመንጫ ጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው

ታዳሽ የኃይል ማመንጫዎችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ለሚሳተፉ የግል ኩባንያዎች ይሰጥ የነበረው የጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው፡፡ የጊዜ ገደቡን ለማራዘም የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 ማሻሻል የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅም ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡