Skip to main content
x

ማማጥስ አሁን ነው!

ሰላም! ሰላም! ያው እንደ ወትሮዬ ለጎጆዬ መሞቅ ላይ ታች እላለሁ። ታዲያ ሚዛን ካልጠበቃችሁ ላይ ታች ማለቱም እንደ ሎተሪ ዕጣ ብርቅ ነው። ማለቴ በ‘ትራንስፎርሜሽን’ ዕቅዱ ውጤት፣ በራሳችን ስንፍና አልያም በአስፈጻሚዎች ቸልታ ተቋዳሽ መሆን ካልቻልን ለማለት ነው። መቼም በአደባባይ ሚስጥራችን ልንቆዝም መሰለኝ ሳምንት ተቀጣጥረን የምንገናኘው። አይደል እንዴ? ምን ይታወቃል? ሁሉን እያወቅነው ጓሮ ለጓሮ መንሾካሾክ እንጂ በግልጽ መወያየት እንፈራለን ብዬ ነው።

ተናግረን ነበረ ሰሚ አጣን እንጂ!

ሰላም! ሰላም! በቀደም ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግራ ጎኔ ተኝቼ ማን ወክሎኝ እንደሆነ አላውቅም፣ ማንን እንደ ወከልኩም እንጃ፣ በአንዴ ከደላላነት ወደ ፖለቲከኝነት ተመንድጌ ለምርጫ ስወዳደር በህልሜ ሳይ ቀውጢ ጩኸት ሰማሁ። ‹‹ገና ሳልመረጥ ይኼ ሕዝብ የሚጮህብኝ ምን አድርጌው ነው?›› ስል ማንጠግቦሽ፣ ‹‹ኧረ ውረድ!›› ስትል በሰመመን እሰማታለሁ። ‹‹ገና ሥልጣን ላይ ሳልወጣ ምን ብዬ ነው የምወርደው?›› ስላት ብርድ ልብሱን ገፈፈችኝ። የጥር ስስ ንፋስ ላዬ ላይ ሽው ሲል ብድግ አልኩ። ለካ ጩኸቱ ከጎረቤት ነው። ‹‹ህልምና ቅዠት መምታታታቸው ሳያንስ በምርጫና በተመራጭነት ዕጣ ያለተፈጥሯችን ይጫወቱብን ጀመር ማለት ነው?›› እያልኩ ሮጬ ወጣሁ። ነገር በዝቷል ዘንድሮ። ከነገሩ በጥቂቱ ላጫውታችሁ።

በር ሲዘጋ መስኮት በር ይሆናል!

ሰላም! ሰላም! ‹ሁዳዴ ከመግባቱ በፊት…› እያለ አንዳንዱ ይኼን ቁርጥ ሲቆርጥ ሳይ ቅበላ እየመሰለኝ ተቸግሬያለሁ። ዳሩ ካላንደር ሳይ ገና ብዙ ቀናት ይቀራሉ። ታዲያ ምንድነው እንዲህ በፆም አሳቦ መፈሰክ እያልኩ ግራ እየገባኝ ነው። አቤት ሆድና ሰው ተባለ። ‹ከውስጥ የሚወጣ እንጂ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰውን አያረክሰውም› እንዳላለን ቃሉ  ብሎ ብሎ ትዝብትም ወደ ሆድ ገባ። ሰውና አፉ የማይገባበት የለም አትሉም? መቼስ እንደ ዘንድሮ አልተዛዘብንም።

ይኼኔ ነው መሸሽ!

ሰላም! ሰላም! ይኼውላችሁ በቀደም የሠፈራችን ወጣቶች ‹‹ሲቲ ይበላል፣ የለም ዩናይትድ...›› ብለው ብር ለማስያዝ ገና ሳይነጋ ቤቴ ድረስ መጡ። አምላክ ሲወዳችሁ ገና ፊታችሁን ሳትታጠቡ መንቀሳቀሻ አበል አምጥቶ እጃችሁ ላይ ቁጭ ያደርጋል። ‹‹መቼ ነው የምሰጣችሁ? ስላቸው፣ ‹‹ገና በሰኔ የእንግሊዝ ፕሪሚየም ሊግ ሲያልቅ ነው፤›› አለኝ ተወካያቸው። እኔም፣ ‹‹እግዜር ይስጥልኝ፤›› ብዬ አምስት ሺሕ ብሬን ቆጥሬ ተቀበልኩ። ሰው ቀላል ልማታዊ ሆኗል እንዴ? ይኼ የመታደስና አምራች ዜጋ የመሆን ሥልጠና ውጤት ብቻ እንዳይሆን። ዝም ብዬ ስጠረጥር ግን እሱ ይመስለኛል። በየአቅጣጫው እጅግ በጣም አምራች ዜጎች በዝተዋል። የዛሬ ሳምንት ከሰዓት በኋላ የሆንኩትን አልነገርኳችሁም። ጠዋት ጠዋት እያገኛችሁኝ ነዋ ምን ይደረግ?

አገር ሰማንያ አለው እንዴ?

ሰላም! ሰላም! ይኼውላችሁ እኔም በተራዬ ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ ጊዜ አንድ ቡቲክ ገብቼ ‹ስኪኒ› ሱሪ ገዛሁ። አገር ተደበላለቀ ነው የምላችሁ። ለነገሩ አገሩም የአገሩ ሰውም ከተደበላለቀ ቆይቷል። ያው የተደባለቀብንና የተደበላለቀብን መለያየት ካልቻልን ድሮስ ምን ልሆን ኖሯል? እና አንበርብር ‹ሲኪኒ› ሱሪ ገዛ ብሎ ሠፈርተኛው ሁሉ ሲያማኝ፣ ገና ምኑን ዓይታችሁ ብዬ ካፖርቴንም አስጠበብኩት። ነገርና ሰው እያደር ሲጠብ ታዲያ እኔ ምን ላርግ? ባይሆን በአለባበስ ልመሳሰላ።

መፈተሽስ ራስን ነው!

ሰላም! ሰላም! ‹‹እነሆ ከ17 ዓመታት ብሶት የወለደው ትጥቅ ትግልና ብሶት ከገፋፋው የ17 ቀናት 'የዝግ ስብሰባ' ያተረፍነው ነገር ቢኖር የማይታረም ጥፋትን በጥልቅ ተሃድሶ ስም፣ የሕግ የበላይነትን በይቅርታ አሳቦ መሸወድ ነው፤›› ያለኝ ማን ነበር? የታሰሩት ይፈታሉ ሲባል ሰምቶ አዳሜ ቀላል ይቀባጥር መሰላችሁ? “የታሰሩት እየተፈቱ እንዴት አዳዲስ ያስራሉ?” እያለ ነዋ። ድንቄም ሕግና የሕግ የበላይነት . . . ‹‹በቃ ግን ይህች አገር የሥልጣን እንጂ የሕግ የበላይነት የማይገዛት አገር ሆና ልታረጅ ነው?›› ሲል ልጃቸውን ሰምተውት ኖሮ ባሻዬ፣ ‹‹ከዚህ በላይ እንዴት ታርጅልህ? ማለት ካለብህማ እንዲህ በዋዛ ፈዛዛ እንዳፋዘዝናት ክርስቶስ መጥቶ ሊገላግለን ነው ወይ ነው ማለት ያለብህ፤›› አሉት። አሁን ይኼን ሁሉ የሚያባብለን ምን እንደሆነ አውቃችኋል አይደል? የሰሞኑን የኢሕአዴግ መግለጫ ነዋ። አንድ ቀልደኛ ወዳጅ አለኝ።

እንዳላየን አልፈን ነገር ብናበርድስ?

ሰላም! ሰላም! ባሻዬ ሬዲዮናቸውን ይዘው ጋቢያቸውን አጣፍተው ይለፈልፋሉ። ብርዱ ነው ግብሩ እንዳትሉኝ። ምን የማያስለፈልፈን ነገር አለ ዘንድሮን ሁሉም ለፍላፊ ሆነና አዳማጭ ጠፋ እንጂ። እና ጠጋ ብዬ ሳዳምጣቸው፣ “አንድ ቋንቋ አላግባባን ብሎ እየተደነቋቆርን ጭራሽ አዲስ ቋንቋ?” ይላሉ። ‘ለግዕዝ ቋንቋ ትኩረት አልተሰጠም’ የሚል ፕሮግራም ሥራዬ ብለው እያዳመጡ።

ለጩኸታችን ስፖንሰር የት እንፈልግ?

ሰላም! ሰላም! የዘንድሮ ንፋስና ሰላም መላ ቅጡ ጠፍቶበታል። የወጉን ለማድረስ እኔና እናንተ ሰላም ብንባባል ግን አይከፋም። ሰላምታም ታክስ እስኪጣልበት ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ ወጉንማ ማን ወግ ብሎት? አታዩንም እንዴ በየቦታው ተሰነጣጥቀን ስንዳማ። እኔና ማንጠግቦሽ ቢቸግረን 'አባታችን ሆይን' 'ኢኮኖሚያችን ሆይ' በሚለው ተክተነዋል። ልቀንጭብላችሁ? ምን ቆርጦኝ። አደራ ታዲያ እናንተም ስትነሱ ስትቀመጡ ይህን ፀሎት ደጋግሙት። ‹‹ኢኮኖሚያችን ሆይ በልማታዊ ባለሀብቶቻችን ጉያ የምትኖር በረከትህ ለእኛ ለአኗኗሪዎችም ትምጣ። መቀመጫህ ከላይ ከላይ እንደሆነ ሁሉ ወደ ታችም ይሁን።

ስንቱን አስፈቅደን እንዘልቀዋለን?

ሰላም! ሰላም! መቼም አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስብላሉ። ‹አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርሙኛል› እንዲል ጥላሁን ገሠሠ። አንድ የሬዲዮ አድማጭ በቀደም ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው። ደወለና “ሃሎ?” አለ። “ሃሎ አስተያትዎን ይቀጥሉ፤” ሲባል፣ “አይ እኔ እንኳን ምንም የምለው የለኝም። ብቻ አንተን በጣም ስለምወድህና ስለማደንቅህ ይኼን ለመንገር ነው፤” አይለው መሰላችሁ ጋዜጠኛው? እና እኔ ምለው ካርዴን በላው ተብሎ ቴሌ ላይ ብቻ ተለቅሶ ይሆናል እንዴ? ኧረ የምር ዕድሜና ጉልበታችንን ቅርጥፍ አርገን እየበላን ያለን እኛው ራሳችን አይደለንም ወይ? እንዲያው ለነገሩ ነገሩ ሁሉ ዞሮ ዞሮ ልጅነት ላይ መላከኩ አይቀርም።

ትንፋሽ አጠረን እኮ?

ሰላም! ሰላም! ባሻዬ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት በትዊተር እንደሚጀመር ታይቶኛል ብለው አካውንት ከፈቱና አረፉት፡፡ “በአርበኝነቱ ዘመን ቢሆን ዝናር እንታጠቅ ነበር፡፡ ጊዜው ግን በቃላት መራገጥ ሆኗል። ታዲያ ማን ተራግጦ ማን ይቀራል?” አሉኝ መደነቄን ዓይተው፡፡