Skip to main content
x

መሬታችን ከተደራጀ ዘረፋ ይጠበቅ!

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍትጊያ ውስጥ መሬት ዋነኛው መዘውር ከሆነ ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡ ከፊውዳሉ ሥርዓት አንስቶ ሥልጣንን መንጠላጠያ በማድረግ የመሬት ዘረፋና ወረራ እየጎለበት የሚታየውም ለዚህ ነው፡፡ በዚህ በኩል ሊታማ የማይችለው የደርግ ሥርዓት ነው ቢባል ሐሰት የለውም፡፡ ደርግ መሬት ላራሹ አለ እንጂ እንዲህ እንደ አሁኑ ደሃው መኖሪያ ሳይሆን መቀበሪያ እየተቸገረያ መሬት በወራሪዎች ሲቸበቸብና በአመራሮች ሲቀራመት አልታየም፡፡ ቢኖርም በጣም ውስንና እዚህ ግባ በማይባል ደረጃ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ከቋንቋ ወደ ግዛታዊነት ቢሸጋገርስ?

በክፍል አንድ ሕገ መንግሥቱ ስለብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ መብቶችና የፌዴራሊዝሙን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉምና ችግሮች ተመልክተናል፡፡ በክፍል ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ የቋንቋ ፌዴራሊዝም መተግበር ከተጀመረ ወዲህ የታዩትን ችግሮች ተመልክተናል፡፡ በክፍል ሦስት ምን ማድረግ ይገባናል የሚል ሐሳብ እንዳስሳለን፡፡

ፈልጎ ማግኘቱ ከባድ የሆነብን ኢትዮጵያዊነት

በየትም ቦታና ጊዜ ያለፈው ዘመን የደስታና የሐዘን መጪው ጊዜ የተስፋና የሥጋት መሆኑ ይነገራል፡፡ በአገራችን ሁኔታ አሁን መጪው ጊዜ ከሥጋት ይልቅ የተስፋ ዘመን መስሎ ይታያል፡፡ ከሦስት ዓመት ወዲህ በተፈጠረው ያለመግባባትና ያለመረጋጋት ብዙ ጥፋት በመድረሱ፣ የደስታ ሳይሆን የሐዘን ወቅትን አስተናግደናል፡፡ ቂም ዘርተን በቀል አጭደናል፡፡

ይቅርታና ምሕረት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ

ምንም እንኳን በዚህ ጽሑፍ የምናወሳው ይቅርታና ምሕረት ሰፋ ያለ፣ ጠለቅ ያለ ፍልስፍናን የተከተለ፣ አካባቢያዊ፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ያለው ነው፡፡ ቢሆንም እንደ መንደርደሪያ፣ ከራሳችን የይቅርታና የምሕረት ታሪክ በመነሳት ነገሩን ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

ማይጨው ሲታወስ

የማይጨው ጦርነት የተካሄደው ከ82 ዓመታት በፊት መጋቢት 22 ቀን 1928 ዓ.ም. ነው፡፡ ማይጨው በስተስሜን በተያያዘ የተራራ ሰንሰለቶች የተከበበ ሲሆን፣ ሌላው አካባቢ ወጣ ገባና ሜዳማ ነው፡፡ አሁን የማይጨው ከተማና የማይጨው ዩኒቨርሲቲ አርፈውበት ይገኛል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ኃይለ ሥላሴ ‹‹ሕይወቴና የኢትዮጵያ ዕርምጃ›› በተባለው አንደኛ መጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ ጦሩ ወደ ውጊያ የገባው በአራት ክፍል ተመድቦ ነው፡፡

ማን ማንን ተስፋ ያድርግ?

ችግሮቻችንን ለይተን ካወቅን መፍትሔውንና ተስፋ የምናደርግበትን ማወቅ እንችላለን፡፡ መሪዎቻችን በምን ጉዳይ ላይ ምን ያህል ሕዝባችን ተስፋ ያድርጉ? ሕዝቡስ ምን ያህልና በምን ጉዳይ ላይ መሪውን ተስፋ ያድርግ? አንዳችን አንዳችን ላይ ተስፋ ማድረግ የምንችለው በትክክል ችግራችንን ስናውቅ፣ ችግራችንን ለመቅረፍ እየተጓዝንበት ያለውን መንገድ በትክክል ካወቅነው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም አወቃቀርና ችግሮቹ

በክፍል አንድ ሕገ መንግሥቱ ስለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብቶች የፌዴራሊዝሙን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉምና ችግሮች ተመልክተናል፡፡ ቀጥለን የምንመለከተው በኢትዮጵያ ቋንቋ ፌዴራሊዝም መተግበር ከተጀመረ ወዲህ የታዩትን ችግሮች የሚዳስስ ይሆናል፡፡ ቀደም ብለን ግን እስኪ ትንሽ ባለፉት ጥቂት አሥርተ ዓመታት የነበሩትን የአገራችንን ታሪካዊ ሁኔታዎችና ወደ ቋንቋ ፌዴራሊዝም የተጓዝንበትን መንገድ እንቃኝ፡፡

የአገር ወዳድነት ብልኃት አጣዳፊነት

አንድን ሕዝብ ወደ አዲስ የፖለቲካ ሕይወትና ዘመን ለመምራት ለየት ያለ የለውጥ አስተሳሰብ ያለው ፓርቲና እውነተኛ መሪ ያስፈልጋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በመጀመርያ ሕዝባዊ ንግግራቸው ይኼን አስቸጋሪነቱ የታወቀ ጀብድ ለመፈጸም ትክክለኛውን መልካም ነገር አስቀምጠዋል። ቁርጠኝነትና ትህትና በተሞላው ንግግራቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ቅርብ ጊዜያት ለተሠሩት ስህተቶችና ቀውሶች ይቅርታ በመጠየቅ፣ በኢትዮጵያዊነታቸው እንደሚኮሩ ተናግረዋል።

የአዲሱ መሪ ሐሳብና ያልተነካው ሙስና

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሲያስመርጥ አይደለም የራሱ የገዥው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችን ይቅርና  ሕዝቡንም ሆነ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን (ተቃዋሚ ከማለት ይህ ስያሜ የተሻለ ያቀራራርባል፣  እንጠቀምበት ብለው የጠየቁትም እሳቸው ናቸው)፣ ተስፋ እንዲያሳድሩ  ያደረጋቸው ንግግርና የቀጣዩ ጊዜ አቅጣጫን ለምክር ቤቱና ለመላው ሕዝብ አቅርበዋል፡፡