Skip to main content
x

‹‹ለሕፃናት በሕፃናት››

ለወትሮው ሕፃናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ሲደረግ፣ አዋቂዎች ተሰባስበው ይመክራሉ፡፡ ሕፃናትን ይገጥሟቸዋል ብለው ላመኑባቸው ችግሮች የመፍትሔ ሐሳቦች አስቀምጠውም ይለያያሉ፡፡ ሕፃናት፣ በአዋቂዎች የተደነገገላቸውን  ያለ ጥያቄ ተቀብለውም ይዘልቃሉ፡፡ የዘንድሮው የዓለም ሕፃናት ቀን ይኼንን የዘልማድ አካሄድ ለመለወጥ ያለመ ነበር፡፡

ለአዳዲስ ፈጠራ ስንቅ የሆነው ይበልታ

ዳጉሳ የተለያየ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች የሚመረት ድርቅና በሽታን መቋቋም የሚችል ሰብል ነው፡፡ በተለይም በቆላማና ደጋማ ቦታዎች በስፋት መመረት ይችላል፡፡ ነገር ግን ተፈላጊነቱ ከሌሎች ሰብሎች አንፃር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተመረተ የሚገኘውም በ454,662 ሔክታር መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡

በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ ተጋላጭነትን የሚቃኝ ቡድን ተንቀሳቀሰ

የተረጂዎች ቁጥር ከ8.5 ሚሊዮን ሊቀንስ ይችላል ከኦሮሚያና ከሶማሌ የተፈናቀሉ ዜጎች ለማቋቋም የሰላም ኮንፈረንስ ይጠበቃል እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 1 ቀን 2018 በኋላ በድርቅ ምክንያት የሚኖረው የተረጂዎች ቁጥር ለማወቅና የሚያስፈልገውን በጀት ከወዲሁ ለመመደብ፣ የመጨረሻውን ቅኝት የሚያካሂድ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር በድምፅ ብክለት ምክንያት 12 ብሎኬት ፋብሪካዎችን ዘጋ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የድምፅ ብክለት እያደረሱ ነው ያላቸውን 12 የብሎኬት ፋብሪካዎች ዘጋ፡፡ ባለሥልጣኑ ዓርብ ኅዳር 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኙ ብሎኬት ፋብሪካዎችን መዝጋቱን አስታውቋል፡፡

ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ ቤቶች ግንባታ አለመጠናቀቁና የውኃ ችግር ሊፈታ አለመቻሉ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ከአምስት ዓመታት የግንባታ ጊዜ ቆይታ በኋላ በ2009 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ በዕጣ ካስተላለፋቸው የ40/60 የጋራ መኖርያ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ፣ በክራውን የሚገኙ ሕንፃዎች ግንባታ ሊጠናቀቅ አለመቻሉና የውኃ ቆጣሪ ሊገባ እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡

ለቤቶች አስተዳደር የወጡ መመርያዎች ከአንዱ በስተቀር በዘጠኙ ክፍላተ ከተሞች ተግባራዊ መሆን ጀመሩ

ነዋሪዎች ቅሬታ እያሰሙ ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ አሻሽሎ ባወጣው መመርያ ቁጥር 4 መሠረት፣ ከአራዳ ክፍለ ከተማ በስተቀር ዘጠኙ ክፍላተ ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን በመመርያው መሠረት እየተስተናገድን አይደለም ያሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

የማታ ትምህርት ወደ ውድቀት?

ከትውልድ ቀዬዋ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ስምንተኛ ክፍልን አጠናቃ ነበር፡፡ የቀን ተማሪም ነበረች፡፡ አዲስ አበባ ከመጣች ወዲህ ግን የቀን ተማሪ የመሆን ዕድል አላጋጠማትም፡፡ በሰው ቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትምህርቷን የማታ ቀጠለች፡፡

የቴክኖሎጂ ወጋገን

የአሥራ አራት ዓመቱ ይትባረክ አረፋይኒ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ታዳጊው የተለያዩ ፈጠራዎችን የመሥራት ልምድ አለው፡፡ ከሠራቸው ሥራዎች መካከል ወላጆቹ ቤት ውስጥ የሚገለገሉበት በስልክ የሚሠራ ፕሮጀክተር አንዱ ነው፡፡

ለኮንፈረንስና ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት ማግኘት የሚችሉበት አሠራር መመቻቸቱ ተነገረ

ከአፍሪካ አገሮች ለኮንፈረንስ፣ እንዲሁም ከአውሮፓና ከአሜሪካ ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት የሚያገኙበት አሠራር መመቻቸቱን፣ የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ አስታወቀ፡፡

ከ60 በላይ የታክሲ ማኅበራት ያለቀረጥ ታክሲዎችን ለማስገባት ያቀረቡት ጥያቄ በመዘግየቱ ቅሬታ አቀረቡ

ከሦስት ሺሕ በላይ አባላት ያሉዋቸው 65 የታክሲ ማኅበራት፣ ያለቀረጥ አዳዲስ ታክሲዎችን ለማስገባት ያቀረቡት ጥያቄ በመዘግየቱ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ቅሬታውን ያቀረቡት የታክሲ ማኅበራት ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአዲስ አበባን ገጽታ የሚቀይሩና ዘመናዊ መሣሪያ የተገጠመላቸው ከሦስት ሺሕ በላይ ታክሲዎችን ለማስገባት ከአንድ ዓመት በፊት ለመንግሥት ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር አልተገባም፡፡