Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
የኢሕአዴግ አሥረኛ ጠቅላላ ጉባዔና የሥልጣን ቅብብሎሹ ዋና ዜና

በጥር ወር 1983 ዓ.ም. የትጥቅ ትግል ላይ እያለ የመጀመርያ ጠቅላላ ጉባዔውን በትግራይ ክልል በቆላ ተምቤን የጀመረው ኢሕአዴግ አሁን አሥረኛ ጉባዔውን በመቐለ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ‹‹ሕዝባዊ አደራን በላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን››

ተጨማሪ ያንብቡ...

መንግሥት የውጪ ዕርዳታ ባይኖርም የተጎዱ ዜጎችን መታደግ የምችልበት አቋም ላይ እገኛለሁ አለ ዋና ዜና

ከውጭ ሰብዓዊ ዕርዳታ ተገኘም አልተገኘም በዝናብ ዕጥረት ለተጎዱ 4.5 ሚሊዮን ዜጎች፣ መንግሥት ዕርዳታ የሚሰጥበት አቅም እንዳለው አስታወቀ፡፡የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በበልግና በክረምት ወራት የዝናብ እጥረት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው 4.5 ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 230 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

-ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸውን ተቃወሙ

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት ገቢ ማድረግ የነበረባቸውን 500 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ኦዲት እያስደረገ መሆኑን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

-ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡ 241.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን፣ ኢኮኖሚው እየተነቃቃ ከመሄዱ አንፃር ገበያው የሚፈልገውን የገንዘብ መጠን አለማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ የተሰማራው ግዙፉ የደቡብ ኮሪያ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ኪንግናም ኢንተርፕራይዝስ፣ ሕልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች፣ ላለፉት 30 እና ከዚያ በላይ ዓመታት ከኖሩበትና ሀብት ንብረት ካፈሩባት ሥፍራ በኃይል እንዲለቁ መደረጉ እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ አካላትን ለፍትሕ እንዲያቀርብ፣ አስፈላጊውን ዕርዳታና ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቀ፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

የዓረቦን ገቢው በዕቅዱ ልክ አልሄደም

•በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የሚባለውን ካሳ ከፈለ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለደንበኞቹ የሰጠው የመድን ሽፋን 1.2 ትሪሊዮን ብር መድረሱንና በ2007 በጀት ዓመት ብቻ 2.1 ቢሊዮን ብር ዓረቦን ማሰባሰቡን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ በኢንዱስትሪ እስከዛሬ ያልተመዘገበ የካሳ ክፍያ መክፈሉንም አመልክቷል፡፡  

ተጨማሪ ያንብቡ...


-የፋብሪካው ሠራተኞች ሥጋታቸውን ገልጸዋል

ታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ ጫሊ ጅሩ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑባቸው ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር፣ ቦረን ሪል ስቴትና ድሬ ኃይላንድ አክሲዮን ማኅበር አክሲዮኖችን ለሦስተኛ ወገን እንዳይሸጡና እንዳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲጓዝ ዓባይ በረሃ ውስጥ በተገለበጠው አውቶቡስ ምክንያት በደረሰው የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ካሳ እንዲከፍል በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተላለፈበት ስካይ ባስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት በማግኘቱ ውሳኔው ታገደ፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

ከጃፓን የመንግሥትና የግል ተቋማት የተውጣጡና ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 80 የጃፓን ልዑካንን ጨምሮ፣ ከ300 በላይ ባለሥልጣናትና ተሳታፊዎች የሚታደሙበት የአፍሪካ ጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...


ገጽ 1/317