መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹አሁን ኩሩ ባለኑክሌር አገር ሆነናል፡፡ የአገራችንን ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችሉንን የፋይናንስና ሌሎች ጥረቶች የምናሳካበት አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮልናል፡፡

በዚህም መሠረት የሕዝባችንን ሕይወት ለመለወጥ ሙሉ ትኩረታችን ያለንን ሀብት በሙሉ በኢኮኖሚ የጠነከረች አገር ለመምሥረት መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ራስን ለመከላከል የሚያስችለውን የኑክሌር መሣርያ በቋሚነት መታጠቅ ዋነኛው ዓላማችን ነው፡፡››

የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን አገራቸው የኑክሌር ጦር መሣርያን በብዛትና በጥራት በማምረት መታጠቋን መቀጠል እንዳለባት በፓርቲያቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡

የኑክሌር ጦር መሣርያዋን ከአሜሪካና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ለመደራደሪያነት እየተጠቀመችበት ነው የሚለውን ስሞታ ያጣጣሉት ወጣቱ ፕሬዚዳንት፣ ይልቁንም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የኮሪያ ልሳነ ምድር በሰሞኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መውደቁ ይነገራል፡፡