መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹በሥልጣን ዘመኔ ሰላም ዘለቄታዊ እንዲሆንና የኑክሌር መሣርያ እንዳይኖር የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል እገባለሁ፡፡

የዛሬ 68 ዓመት አንድ አቶሚክ ቦምብ በአንድ ቀን ከ100 ሺሕ የሚበልጡ ጃፓናውያን ወገኖቻችንን ውድ ሕይወት ቀጥፏል፡፡ ከዚያ ሰቆቃ በሕይወት የተረፉ ሊነገር የማይችል ስቃይ፣ የአካል መጉደልና መከራ የየዕለቱ የኑሮዋቸው አካል ሆኗል፡፡››

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የሒሮሽማ አቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ 68ኛ ዓመት መታሰቢያ በማስመልከት ማክሰኞ ዕለት ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ እ.ኤ.አ ኦገስት 6 ቀን 1945 የአሜሪካ አየር ኃይል ቢ29 የጦር አውሮፕላን በመጠቀም ‹‹ሊትል ቦይ›› በመባል የሚጠራውን የአቶሚክ ቦምብ በሒሮሺማ ከተማ ላይ በመጣል ከ100 ሺሕ በላይ ጃፓናውያንን ሲገድል፣ ከሦስት ቀናት በኋላ ደግሞ በናጋሳኪ ከተማ ላይ በጣለው የአቶሚክ ቦምብ ከ200 ሺሕ በላይ ጃፓናውያን ማለቃቸው ይታወሳል፡፡ አሜሪካ ይኼንን ጥቃት የፈጸመችው በፐርል ሐርበር ጃፓን በባህር ኃይሏ ላይ ለፈጸመችው ጥቃትና እልቂት ምላሽ ነበር፡፡