መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹በምርጫው የተሸነፉት ከፈለጉ ራሳቸውን ማጥፋት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ቢሞቱ እንኳን ሥጋቸውን ውሻ አይበላውም፡፡ ምክንያቱም የምዕራባውያን አሻንጉሊቶች ናቸውና፡፡››

የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ ባለፈው ሰኞ የአገሪቱ ብሔራዊ ጀግኖች ቀን ሲዘከር ለአንድ ሰዓት ያህል ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ የ89 ዓመቱ ሙጋቤ በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞርጋን ሻንጋራይን በሰፊ ውጤት ቢያሸንፉም፣ ሻንጋራይ የሕዝቡ ድምፅ ተሰርቋል በማለት ወደ ፍርድ ቤት አምርተዋል፡፡ 

ሙጋቤ ግን የተቀናቃኛቸውን ፓርቲ ኤምዲሲ ወይም የሻንጋራይን ስም ሳይጠቅሱ በደፈናው ‹‹ተቃዋሚዎች›› በማለት ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥታቸው ዲሞክራሲን በማቅረብ ውሰዱ ወይም ተውት ማለቱን ገልጸው፣ ሕዝቡ ግን በድምፁ ዲሞክራሲን ማስፈኑን አስረድተዋል፡፡ ተቃዋሚዎቻቸው ግን የሙጋቤ ድል ለዚምባቡዌና ለዲሞክራሲ ሞት ነው እያሉ ናቸው፡፡