መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹አሜሪካ በዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የምታነሳው፣ ራሳቸው ሙጋቤ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ለውጥ ሲያካሂዱ ብቻ ነው፡፡››

በቅርቡ በዚምባቡዌ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙጋቤና ፓርቲያቸው ዛኑ ፒኤፍ ተቀናቃኙን ሙቨመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ የተባለውን በጠቅላይ ሚኒስትር ሞርጋን ሻንጋራይ የሚመራውን ፓርቲ በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸው ለአሜሪካና ለምዕራባውያን ባለመዋጡ፣ የአሜሪካ መንግሥት ካወጣው መግለጫ የተወሰደ፡፡ አሜሪካ ምንም እንኳ በአደባባይ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ስሞታ ባታቀርብም፣ ፕሬዚዳንት ሙጋቤ አሸናፊ የሆኑት ሕዝቡን በጦር ኃይሉና በፀጥታ ኃይሉ በማስፈራራታቸው ነው የሚለውን ታምንበታለች፡፡

ለዚህም ነው የአሜሪካ መንግሥት በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጭምር ፊት የተነሳውን የሙጋቤ መንግሥት የፖለቲካ ሥነ ምኅዳሩን እንዲያስተካክል በመጠየቅ ላይ ያለው፡፡ ሙጋቤ ግን የሕዝቡን ውሳኔ ማንም ሊቀለብሰው እንደማይችል በመግለጽ፣ ‹‹ሕዝቡ ዲሞክራሲን በድምፁ አስፍኗል፤›› በማለት ይሞግታሉ፡፡ የምዕራቡ ዓለም ግን ላለፉት 33 ዓመታት ዚምባቡዌን የገዙትን ሙጋቤ፣ ‹‹በዲሞክራሲ ላይ ማሾፍ ይብቃዎት፤›› እያላቸው ነው፡፡