መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹ሶሪያውስጥ በሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች ሕፃናት በዘግናኝ ሁኔታ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በቅርቡ በደማስቆ በደረሰው ጥቃት [የኬሚካል ጦር መሣርያ] ሕፃናት አልቀዋል፡፡ አሁን አንድ ሚሊዮን የሶሪያ ሕፃናት ልብ በሚሰብር ሁኔታ ስደተኛ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ለችግርና ለጥቃት የተጋለጡ ሕፃናት ያለጥፋታቸው ስሜት በማይሰጥ ግጭት እየተጎዱ ነው፡፡ አሁን ሕፃናቱ መጠለያ፣ ምግብና ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ ከምንም ነገር በላይ ደኅንነታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዓይኑን ከሶሪያ ላይ ማንሳት የለበትም፡፡ የሶሪያን ሰላም በአስቸኳይ ለማፈላለግ መንቀሳቀስ አለበት፡፡››

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ዝነኛዋ የፊልም ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ ማክሰኞ ዕለት ካደረገችው ንግግር የተወሰደ፡፡ ይህች የሆሊውድ ኮከብ በቅርቡ በሶሪያ በተፈጸመ የኬሚካል ጦር መሣርያ ጥቃት ሕፃናት ሳይቀሩ መገደላቸው አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ፣ አንድ ሚሊዮን ሕፃናት በመሰደዳቸውና ለችግር በመጋለጣቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት የግድ ነው ብላለች፡፡ አንጀሊና ጆሊ በሰኔ ወር የዓለም የስደተኞች ቀን ሲከበር በጦርነት ውስጥ ያለችውን ሶሪያ ድንበር መጎብኘቷ አይዘነጋም፡፡ በተለይ የሶሪያ ሕፃናት ጉዳይ እንቅልፍ እንደሚነሳት መናገሯም ይታወሳል፡፡