መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ፍሬ ከናፍር - ፍሬ ከናፍር
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

‹‹የሶሪያ መንግሥት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በኬሚካል ጦር መሣርያ ለመፍጀቱ የማያወላዳ ማስረጃ አለን፡፡

ለዚህም በከፍተኛ ደረጃ በራሳችን እንተማመናለን፡፡ በመሆኑም ኮንግረሱ በሶሪያ ለማድረግ ላሰብነው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ድጋፉን እንደሚሰጥ እምነቴ የፀና ነው፡፡››
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን መንግሥት በማያዳግም ሁኔታ ለመቅጣት ያላቸውን ጉጉት ለጋዜጠኞች ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ የኮንግረስ አባላት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቱን እንደሚደግፉት በልበ ሙሉነት ተናግረው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኮንግረስ አባላት ጋር ለመምከር መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሶሪያ መንግሥት ከአሁን በኋላ የኬሚካል ጦር መሣርያን መጠቀም እንዳይችል ‹‹የተመጣጠነ›› ወታደራዊ ዕርምጃ ተወስዶበት አቅሙ እንዲዳከም ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዚህ ዘመቻ በጦር አውሮፕላኖችና በሚሳይሎች አማካይነት ወታደራዊ ጥቃቱ እንደሚፈጸም አስረድተው፣ እንደ ኢራቅ ወይም አፍጋኒስታን የአሜሪካ እግረኛ ወታደሮች ተሳትፎ እንደማይኖር ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡