መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ልዩ ልዩ - ዝንቅ - የአስኮው ‹‹ፏፏቴ››
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
18 August 2013 ተጻፈ በ 

የአስኮው ‹‹ፏፏቴ››

ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ከአራዳ ጊዮርጊስ ወደ አስኮ ጊዮርጊስ ያደርሰኝ ዘንድ ፒያሳ ላይ የተሳፈርኩበት ሚኒባስ ታክሲ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጋ ስደርስ አንድ ትዕይንት አሳየኝ፡፡

ከባድና ቀላል ተሸከርካሪዎች መንገዱን ዘግተውት ቆመዋል፡፡ መንገዱ በግንባታ ላይ ስለሆነ አንደኛው መተላለፊያ ተዘግቶ ይሆን የሚል ሐሳብም ቢያድርብንም ጉዳዩ ሌላ ሆኖ ተገኘ፡፡ ለካ የከፊል መንገዱን ወጣ ገባነት ሊያስተካክል የተንቀሳቀሰው ዶዘር መንገዱን እጠርጋለሁ ሲል ዋናውን የውኃ መስመር ሲመነግለው የግዮን ሆቴልን ፏፏቴ የሚያስንቅ ‹‹ፏፏቴ›› ወዲያው በመፈጠሩ ኖሯል መንገዱን የዘጋው፡፡ አንዱም ተሳፋሪ ‹‹አዲሱ የአስኮ ፏፏቴ›› ተገኘ ብሎት አርፍ አለ፡፡ ወግና ፎቶ በሔኖክ ያሬድ

------- ------- --- ---------- ----------------

የአገር ሰምና ወርቅ 

/ደመቀ ከበደ - ጣና ዳር/

ጥሩነሽ ከውድድሩ በፊት ለጋዜጠኞች የሰጠችውን ቃለ-ምልልስ ሰምታችሁ ይሆን??

እሱን ሰማሁ፤ ሩጫዋንም አየሁ - ለክብሯ ይህንን ፃፍኩ፡፡ //ከንባብ አስቀድሞ ግን 

ይህ ግጥም የጥሩዬን የአገር ፍቅር ለማላቅና የእኛን ወርቅ ያለማጣት ጉጉት ለማተለቅ እንጅ የሌሎችን ልጆቻችንን ውጤት ለማናናቅ እንዳልተፃፈ ልብ ይባልልኝ፡፡//

------- ------- --- ---------- ----------------

ልለምንህ ጣና - ልማጠንህ ዓባይ - አዋሽ እሺ በለኝ

አገሬ ተድራ - አገር ጠርቻለሁ - የአገር ድግስ አለኝ፤

አገሩን የዳረ - አገር ህዝብ የጠራ

ለአገር የጠመቀ - ለአገር የደገሰ፣

መሬቱ እንጀራው ነው - ሀይቁም ወይንጠጁ

መች ይጨንቀውና - ደረሰ አልደረሰ፤

ይኸው አገር መጣ!

ይኸው አገር ወጣ!

አገር ድግስ በይ - አገር ላይ የወጣ - አገር ሊያይ የመጣ

ብትታየው ጊዜ - አገር ሙሽራዬ - ከአገር ሁሉ በልጣ

አገር ልቡ ቆመ - አገር ማድነቂያ አጣ - አገር አቅም አጣ፡፡

ይኸው ይቺውልህ፤

በአገር ፍቅር ቬሎ - በአገር ሰረገላ

አገር ስትመዘን - በሰው ተመስላ

ይህን ታህላለች

ይህን ትመስላለች

በል ሀቅ እንፈልቅቅ - ከሯጭ ህብረ - ቀለም

በአትሌት ሰምና ወርቅ - በ‹‹ሀገር›› ቀልድ የለም!!

ለዚያም ነው ጥሩዬ

አገር በልቧ አዝላ - በአገር ተውባ

በአገራት ሙሽሮች - በአገራት ተከባ

በአገር አደባባይ - አገር ስታገባ

አገር ወዲያ ጥላ - ወደ አገር ስትገባ

አገር ምድሩ ያለው - ጉሮዬ ወሸባ!!

ነው እንጅ ነውና!!

‹‹ጥሩ›› አገር ብትሆን ነው - አገርን ያከለች - አገር የተሰጠች

ከአገር ተፎካክራ - አገር ያስከተለች - አገር የበለጠች!!

ይኸው ነው ቀለሙ - ይኸው ነው እውነቱ

እሷ ስታሸንፍ - እኛ ሁላችንም - የጨፈርንበቱ!!

ስማ ጋዜጠኛ፤

ይኸውልህ እውነት - የሀቅ ህብረ - ቀለም

በጥሩነሽ አገር - ስለ አገር ቀልድ የለም፡፡

//ካላመንክ ጠይቃት - ከአንደበቷ ስማ

እንዲህ ትልሃለች - አገር አስቀድማ...//

‹‹ለሌላ አገር አትሌት - እንኳን ሜዳሊያ - መጨረስም ድል ነው

ለኔ አገር ህዝብ ግን - ብር ሽንፈት ሲሆን - ነሀስም ውራ ነው፤

በቃ በኔ ሀገር - ድል ነው እሚባለው

ወርቁን ከነክብሩ - ያስገኘህ ጊዜ ነው!!››

ይህ ነው ሰምና ወርቅ - በጥሩነሽ አገር - የአገር ህብረ - ቀለም

ወርቅ ለለመደ - ነሀስ ግድ አይሰጥም - ብርም ድል አይደለም፡፡

ነሐሴ 5 - 2005 ዓ.ም.

********************* 

አምላክ እና አምላካት 

በአንድ ወቅት አንድ ሐሰተኛ ሰባኪ በኪላፊስ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ቤተ- መቅደስ በራፍ ላይ ሆኖ ብዙ አምላካት እንዳሉ ሰበከ፡፡ ምዕመኑንም በልባቸው “ይህንንማ እናውቀዋለን፡፡ አብረውን እየኖሩ በሄድንበት ሁሉ ይሄዱ የለም እንዴ?” ሲሉ አሰቡ፡፡ 

ብዙም ሳይቆይ አንድ ሰው በገበያው መሃል በመቆም መሰበክ ጀመረ “አምላክ የለም” እያለ፡፡ ብዙዎች አምላካቱን ይፈሯቸው ስለነበር በንግግሩ ተደሰቱ፡፡ 

በአንድ ሌላ ቀን አንድ አንደበተ-ርቱዕ ብቅ አለና ስብከቱን አስተጋባ፡፡ “አምላክ አንድ ነው፡፡” ህዝቡ ከብዙ አምላካት ይልቅ አንድ አምላክ ፍትሃዊ ፍርድ ይሰጣል ብለው ስላላሰቡ በንግግሩ ተከፉ፡፡ 

***********************

“የተጠበሰ እንቁላል”

የሆቴልን ነገር ሆቴል ያነሣዋል፡፡ አንድ አሜሪካዊና አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ አንድ ሆቴል ገብተው አሜሪካዊው የተጠበሰ እንቁላል፣ ኢትዮጵያዊው ደግሞ የተጠበሰ ዶሮ አዝዘው እየተመገቡ እንዳሉ ኢትዮጵያው የቀረበለትን ዶሮ አጥንት ሲቆረጣጥም የተመለከተው አሜሪካዊ በኢትዮጵያው ለማፌዝ “ለውሾቹ ምን ተረፋቸው” ብሎ ሲጠይቀው ኢትዮጵያዊው ፈጠን ብሎ “የተጠበሰ እንቁላል” ብሎ መለሰለት፡፡ 

 

በዚያው ዓመት ሌላ አንድ ሰባኪ መጣና “በነፋሱ ውስጥ አንድ ሆነው የሚኖሩ ሶስት አምላክ አሉ፡፡ እጅግ የከበረች እና ሰፊ የሆነች ሚስትም እህትም የምትሆን እናት አለቻቸው” ብሎ ተናገረ፡፡ 

ይሄን ጊዜ ሁሉም ደስ አላቸው “አምላካቱ ሶስት መሆናቸው በሃጢአታችን ላይ እንዲከራከሩ ስለሚያደርጋቸው ጥሩ ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ የተከበረች እናታቸው ለእኛ ምስኪን ሃጢያተኞች ትከራከርልናለች” በማለት አሰቡ፡፡ 

ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ የኪላፊስ ከተማ ነዋሪዎች አምላክ ብዙ ነው፣ አንድ ነው፣ የለም አንድም ሶስትም ነው እያሉ ከመከራከራቸው በተጨማሪ ስለተከበረችው የአምላካት እናትም እየተነታረኩ ነው፡፡ 

ካህሊል ጂብራን “የጥበብ መንገድ” (1998)

************* 

“እንግሊዝ ጨው ስግተው”

ልጃቸው ቁልፍ የዋጠባቸው ሴት በፍጥነት ወደ ሐኪም ቤት ይዘው ይሔዱና ለዶክተሩ ችግሩን ይነግሩታል፡፡ ዶክተሩም ቁልፉን ለማውጣት ተኝቶ ቀዶ ሕክምና እንደሚደረግለት ሲነግራቸው እናት በመናደድ ተነሥተው ልጃቸውን ይዘው ለመሔድ ሲዘጋጁ “ወዴት ልትወስዱት ነው ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ ሴትዮዋም “የልጄን ሆድም አላስቀድድም ቁልፌንም እንግሊዝ ጨው በጥብጩ ባፉ ባፉ ስግተው ይተፋታል” ሲሉ መለሱለት፡፡ 

- ‹‹የወግ ገበታ››

**************** 

‹‹አብዝተው እስካልወለዱ ድረስ…››

እንግሊዝን በመጎብኘት ላይ ያለ አንድ የየል ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አንዱን የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ መምህር አገኘውና ስለእንግሊዝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠባይ ጠየቀው፡፡ 

‹‹ወንዶቹን እንዲያጨሱ ትፈቅዱላቸዋላችሁ? ሲል አሜሪካኑ ጠየቀ፡፡

‹‹አንፈቅድላቸውም›› ሲል እንግሊዛዊው መለሰ፡፡

‹‹መጠጥ ይጠጣሉ?››

‹‹በፍፁም አይጠጡም››

‹‹ልጃገረዶችንስ እንዲያወጡ ትፈቅዱላቸዋላችሁ?›› አሜሪካኑ ጠየቀ፡፡

‹‹ኦ ይህማ የተፈቀደ ነው›› አለ፤ እንግሊዛዊው ቀጥሎም ‹‹ይኸውም አብዝተው እስካልወለዱ ድረስ ነው›› አለው፡፡

-አዳነ ቸኮል ‹‹የቀልዶች ማዕበል›› (2000) 

 

**********