መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ዲያስፖራ - ከዌስት ቴይስ እስከ ጐጃሙ አማኑኤል
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
31 March 2013 ተጻፈ በ 

ከዌስት ቴይስ እስከ ጐጃሙ አማኑኤል

በአሜሪካ የነርቭ ሕክምና ባለሙያ የሆኑት አባታቸው በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉና ሥልጠና እንደሚሰጡ ያውቃሉ፡፡

ኢትዮጵያን ለመርዳት ያላቸውን ፍላጐት በተደጋጋሚ ሲገልጹም ይሰማሉ፡፡ ከዚህ ቀደም አባታቸው ኢትዮጵያ መጥተው ለነርቭ ሕክምና ተማሪዎች ሕክምና ሰጥተው ከተመለሱ በኋላ ግን ሁለቱ ልጆቻቸው በቀጣይ አባታቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲሔዱ አብረው እንደሚሔዱ ያቅዳሉ፡፡ ስለኢትዮጵያ ከአባታቸው የተረዱት ታዳጊ ሕፃናት ኢትዮጵያን በአካል አይተው እነሱም የአባታቸውን ዱካ መከተል እንደሚፈልጉ ለቤተሰቦቻቸው ያሳውቃሉ፡፡

በፒዩፕል ቱ ፒዮፕል አገናኝነት ኢትዮጵያ በመመላለስ የነርቭ ሕክምና ሥልጠና የሚሰጡት ዶክተር ሮበርት ሉዊስም ልጆቻቸው ኢትዮጵያ ሲሔዱ በፒዩፕል ቱ ፒዩፕል አማካይነት በጐጃም አማኑኤል የተመሠረተውንና ወላጅ ያጡ ሕፃናት የሚማሩበትን አዳሪ ትምህርት ቤት እንደሚጐበኙ ይነግሯቸዋል፡፡

በአሜሪካ ሃሪኬን ዌስት ቨርጂኒያ በሚገኘው ዌስት ቴይስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑት የ11 ዓመቱ ኤንዞ ሉዊስና የሰባት ዓመቷ ኤማ ሉዊስ እንደ አባታቸው ተሳክቶላቸው ኢትዮጵያን ለማየት የቻሉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እንደገቡም ጉዟቸውን ያደረጉት ጐጃም አማኑኤል በሚገኘውና ወላጅ ያጡ ልጆች ወደሚማሩበት የፒዩፕል ቱ ፒዩፕል አዳሪ ትምህርት ቤት ነው፡፡

ኤንዞ ሉዊስና ኤሚ ሉዊስ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በሚመሩበት ዌስት ቴይስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለት ጊዜ የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረጋቸውንና በዚህም ያገኙትን 800 ዶላር ለአዳሪ ትምህርት ቤት መስጠታቸውን ነግረውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መማርያ ደብተር፣ እርሳስና እስክሪብቶ፣ ሳሙና፣ የጥርስ መታጠቢያና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማምጣታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የ11 ዓመቱ ኤንዞ ለአዳሪ ትምህርት ቤቱ ይዘው የመጡት ገንዘብም ሆነ ቁሳቁስ በቂ ነው ብሎ አያምንም፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ያየውን በሙሉ ወደ ትምህርት ቤቱ ሲመለስ ሪፖርት ስለሚያደርግ የትምህርት ቤት ማኅበረሰብ የበለጠ ሊረዳ እንደሚችል፤ እሱም በቀጣይ የተሻለ ነገር እንደሚያደርግ ተናግሯል፡፡

አብረዋቸው የመጡት እናታቸው ሚስ ሲንዲ ሉዊስ የዌስት ቴይስ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ኢትዮጵያን መርዳት ይፈልጋሉ እኛም እናበረታታለን ብለዋል፡፡ ሚስ ሲንዲ እንደሚሉት፣ ብዙ አሜሪካውያን ኢትዮጵያን መርዳት ይፈልጋሉ፡፡ እሳቸውና ቤተሰባቸው ደግሞ ከብዙዎቹ አንዱ ናቸው፡፡ 

በአሜሪካ ከተመሠረተ 15 ዓመታትን ያስቆጠረው የፒዩፕል ቱ ፒዩፕል መሥራችና ፕሬዚዳንት ዶክተር አናውጋው መሐሪም ብዙ አሜሪካውያን ኢትዮጵያን በተለያየ መልኩ መርዳትና መደገፍ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ ፒዩፕል ቱ ፒዩፕል በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን፣ አሜሪካውያንን እንዲሁም ተቋማትን በኢትዮጵያ ከሚገኙት ተቋማትና ባለሙያዎች ጋር በማገናኘት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ያደርጋል፡፡ በአሜሪካ ያሉ ተቋማትና ባለሙያዎችን፣ ፒዩፕል ቱ ፒዩፕልንና ኢትዮጵያ የሚገኙ ተቋማትና ባለሙያዎች በአንድ በማጣመርና የሦስትዮሽ ግንኙነት በመፍጠርም በኢትዮጵያ በኩል ያሉ ክፍተቶች እንዲታወቁ፣ በአሜሪካ በኩል ሊደረጉ የሚችሉ እገዛዎች እንዲለዩና ሥራዎች በቀጣይነት ተከናውነው ለውጥ ማምጣት እንዲቻል ይሠራል፡፡

ሕፃናቱና ሌሎች አሜሪካውያን ለአዳሪ ትምህርት ቤቱ ካደረጉት እገዛ በተጨማሪ የድርጅቱ አሁኑ ጉዞው ዋና አጀንዳ የድንገተኛ ሕክምናን ማጠናከር ነበር፡፡ በመሆኑም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ ፒዩፕል ቱ ፒዩፕልና ስታንፈርድ ዩኒቨርሲቲ አብረው እንዲሠሩ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፒዩፕል ቱ ፒዩፕልና ዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲ በመተባበርም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድንገተኛ ሕክምና ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከዚህ ጐን ለጐንም ለኢትዮጵያ የሕክምና ተማሪዎች መሠረታዊ የሆነውን የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ ማኑዋል አዘጋጅተው ማምጣታቸውን ዶክተር እናውጋው ገልጸዋል፡፡

ማኑዋሉን ማዘጋጀት የተጀመረው ከ10 ዓመት ወዲህ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የመቐለ ዩኒቨርሲቲና የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በሥርዓተ ትምህርታቸው አካተው ለሕክምና ተማሪዎች እየሰጡ ነው፡፡

ማኑዋሉን ለማዘጋጀት የተለያዩ ምሁራን ቢሳተፉም፡፡ የመጀመርያ እንደመሆኑ በዘርፍ ያለ ባለሙያ ሊያስፋፋውና ሊያሳድገው ይችላል የሚሉት ዶክተር እናውጋው፣ ዋናው ነገር የሕክምና ተማሪዎች ስለኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ በሥርዓተ ትምህርቱ ተካትቶ እንዲማሩ ማድረጉ መጀመሩ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡