መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ዲያስፖራ - የኢትዮጵያ ወዳጆች ስጦታ
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
25 August 2013 ተጻፈ በ 

የኢትዮጵያ ወዳጆች ስጦታ

በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ፣ በእስያና በአሜሪካ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን በገንዘብና በሙያ ሲረዱ ይስተዋላል፡፡

በወጣትነት፣ በጎልማሳነትና ከጡረታ በኋላ ለአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ኢትዮጵያ በመምጣት ልምዳቸውን ሲያካፍሉ፣ ሲያስተምሩ እንዲሁም በሕክምናው ዘርፍ ሲያገለግሉም ይታያሉ፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ የኢትዮጵያ ወዳጆች በስተጀርባ ደግሞ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ውትወታ ቀላል አይደለም፡፡ 

በዶክተር እናውጋው መሐሪ አስተባባሪነት በኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ የተመሠረተው ፒዩፕል ቱ ፒዩፕል፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑ አሜሪካውያን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እንዲያስተምሩ፣ ልምድ እንዲያካፍሉ፣ እንዲረዱ ከሚያደርጉ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡ 

በፒዩፕል ቱ ፒዩፕልና በኢንተርናሽናል ሜዲካል ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ትብብር በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ልጆች የምልክት ቋንቋን እንዲያውቁ፣ ትምህርት እንዲማሩና በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲረዱ ለማስቻል ሥራዎች ከተጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ 

በድርጅቶቹ ትብብር ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ በባሕር ዳር ከተማ የካቲት 23 መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ይገኝበታል፡፡ የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን፣ በፒዩፕል ቱ ፒዩፕል አስተባባሪነት በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ወዳጆች አሜሪካውያን ድጋፍ ሲያገኙ ቆይተዋል፡፡ 

ትምህርት ቤቱ ከዚህ ቀደም ሲያገኝ የነበረውን ድጋፍ ለማጠናከርና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ መምህራን ጋር ለመምከር 12 አሜሪካውያን መጥተው ነበር፡፡ በኢንተርናሽናል ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ትብብር መሰንበቻውን የልምድ ልውውጥ ካደረጉት 12ቱ የቡድኑ አባላት መካከል ሚስተር ግሪጐሪ ቡኢ እንደተናገሩት፣ አስተርጓሚዎችን፣ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን፣ የምልክት ቋንቋ መምህራንን የያዘው ቡድን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ማኅበረሰብ ጋር የምልክት ቋንቋ በኢትዮጵያ እንዴት መዳበር እንዳለበት፣ የአሜሪካ ልምድ ምን እንደሚመስልና በአሜሪካ የዘርፍ ባለሙያዎች እንዴት እገዛ ሊያደርጉ እንደሚችሉ መክረዋል፡፡ 

መስማት የተሳናቸው ልጆች በአገሪቱ የምልክት ቋንቋ ባለመስፋፋቱ መማር እያቃታቸው መሆኑን የተናገሩት ሚስተር ቡኢ፣ የአማርኛና የእንግሊዝኛ የምልክት ቋንቋዎችን አጣምሮ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለአሜሪካውያኑ የሚከብዳቸው ቢሆንም፣ ከምልክት ቋንቋ መምህራንና ከአስተርጓሚዎች ጋር በመተባበር ሕፃናቱ የትምህርት ገበታ ተቋዳሽ እንዲሆኑ እየረዱ መሆኑና ወደፊትም መርዳት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ 

መስማት የማይችሉትን ለመርዳት ማስተማር የመጀመርያው ዕርምጃ ነው፡፡ ከአሜሪካ የወጣው ቡድንም መሠረታዊ ግብ አድርጐ የተነሳው መስማት የተሳናቸው መማር አለባቸው የሚለውን ነው፡፡ በመሆኑም በባሕር ዳር የካቲት 23 መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት መምህራን ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎችን በሙያና በቁሳቁስ በመርዳት ላይ ይገኛሉ፡፡ 

ተማሪዎቹን በማስተማሩ ረገድ ፈተና የሆነባቸው በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎች መስማት የተሳናቸው ብቻ ሳይሆኑ፣ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው፣ ኦቲስቲክት እንዲሁም ዓይነስውራን ጭምር መሆናቸው ነው፡፡ የተለያየ ዓይነት ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ለማስተማር መሞከር ደግሞ ፈተና ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪዎቹ እንደየችግሮቻቸው ተለይተው መማር የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር አሜሪካ ሲመለሱ ከድርጅቶቹ ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል፡፡