መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ፌርማታ - የዝክረ መለስ ጧፎች በዝግጅት ላይ
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
21 August 2013 ተጻፈ በ 

የዝክረ መለስ ጧፎች በዝግጅት ላይ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ነፍስ ኄር መለስ ዜናዊ ካረፉ ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. አንድ ዓመት ሞላቸው:: ዝክረ ዓመታቸውን ለመዘከር በዋዜማው የጧፍ ማብራት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ተከናውኖ ነበር:: ፎቶ ግራፎቹ ቅድመ ዝግጅቱን ያሳያሉ:: ፎቶ በመስፍን ሰሎሞን

መሢ ያገር ቅኔ

አዛኝ ነሽ በእውነቱ÷ እንደ እመ ብርሃን

ክረምቱ ከብዶን÷ ብርድ ብርድ ሲለን

ብድራት የሌለው÷ እሳት ያጫርሽን፡፡

ሙቀት አማጪቱ÷ መሠረት ደፋር

ክረምቱን በሽሽት÷ ሀገር እስኪያቅፍሽ

ዓለም የሞቀሽ÷ ሙቀት ያማጣሽ

ለካ ጠሐይ ነሽ! ለካ እሳት ነሽ፡፡

አዛኝ ነሽ በእውነቱ÷ መሠረት ያልኩሽ

በሰው ሰው ተፈጥሮሽ÷ ለሰው እያደላሽ

ክረምቱን ጨክነሽ÷ ፈጥነሽ አባረርሽ፡፡

ምን ትበል እመ ብርሃን? ምን ትበል ማርያም?

እሳት እያጫሩ÷ ወርቅ ማነጣጠር

በእውነት የእሷ ክብር÷ መገለጫ ነበር፡፡

ክረምት ምሱ በዝቶ÷ ተዘጋግቶ በር

ማን እሳት ሊጭር? ማን እሳት ሊያጭር?

እግር የሚያሟሙቅ÷ ንዳድ ተመልተሽ

ሙቀት ለግሠሽ÷ ክረምት አግባ ሆነሽ

እንዴት ሳላውቅልሽ? እንዴት ሳልሞቅብሽ?

መሢ ባሥር ጣቴ÷ ብዕር እጭርሽ?

ስለዚህ ልቀኝሽ÷ በኅብር ላሰናኝሽ

ሀገር እስኪያነብሽ÷ እስኪመራመርሽ

ሰም ወርቅ ማሰማርያ÷ መንገድ አንቺ አለሽ፡፡

በወርቅ ተመሥጥረሽ÷ በሰም ተኵለሽ

አገባቡን ከፊት÷ እየደረደርሽ

ማንም ላይፈታሽ÷ ማንም ላይችልሽ

መሢ ያገር ቅኔ÷ ፈቺ አደከምሽ፡፡

ለካ ጠሐይ ነሽ! ለካ እሳት ነሽ!

ለካ ቅኔ ነሽ! ለካ ምሥጢር ነሽ!

እንኳን ሊዘርፉሽ እንኳን ሊነጥቁሽ

አልዳስስ እያልሽ÷ ሀገር አፋጀሽ፡፡

ነሐሴ 11 / 2005 ዓ.ም.፤

በኃይለ ልዑል ካሣ / አዲስ አበባ፡፡

******************************* 

የመጀመሪያው ፊደል (አልፋቤት) የየትኛው ቋንቋ ነው?

የሰው ልጅ ከፈጠራቸው ወይም ሊጠቀምባቸው በፀጋ ካገኛቸው ጥባባት ሁሉ ቀዳሚነትንና አስደናቂነት ይዞ የሚገኝ ጥበብ ፊደል ነው ቢባል እብለት አይሆንም፡፡ (በተለይ ከኢትዮጵያ ፊደል የበለጠ ጥበብ (ፍልስፍና) ይኖራል ብዬ በግለ አላምንም፤ ይህ እኔ የደረስኩበት መደምደሚያ ነው፤ የጥበቡን ጥልቀትም ሳስተውለው ግርምም ይለኛል፡፡) ምናልባት ይህንን ያስተዋለው ወንደል ሂ. ሆል የተባለ ጸሐፊ ‹አልፋቤት (ፊደል) የሰው ልጅ አእምሮ ከፈጠራቸው አስደናቂ ጥበባት ውስጥ ያለ ጥርጥር ታላቁ ፈጠራ ነው› (The alphabet is without doubt one of the greatest creations of the human mind.) ብሏል፡፡  በተለይ መጀመሪያ ጥበቡን የፈለሰፈው ማን ነው? የትስ አካባቢ ተጀመረ? ቀዳሚውስ የየትኛው ቋንቋ አልፋቤት (ፊደል) ነው? የሚሉት ጥያቄዎችን መልስ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በጥቅሉ ስለ አልፋቤት አመጣጥ ያጠኑ አብዛኞቹ ሊቃውንት የደረሱበት መደምደሚያ ‹በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ ተመሥርተው በዓለም ላይ ገናና የሆኑት እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፔንኛ… ቋንቋዎች ከሮማይስጥ (ላቲን) ቋንቋ የመጡ ናቸው፤ በመሆኑም አልፋቤታቸወም እንደዚሁ የሮማይስጡን መልክና ቅርፅ የወረሰ ነው፡፡ ሮማይስጥ ደግሞ ከፅርዑ (ግሪኩ) የወጣ ነው፣ እሱም ብቻ ሳይሆን የሩሲያም ቋንቋ እንዲሁ የግሪክ ድቃላ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ ‹የፅርዕ ፊደልና ጽሕፈትስ ከየት መጣ?› ተብሎ ሲጠየቅም ከዕብራውያንና ከፊንቃውያ ተኮርጆ የተወሰድ መሆኑን የሥነ ልሳንና የሥነ ሰብእ ጥናቶች በምስክርነታቸው አረጋግጠዋል፡፡

 የፊንቃውያን ጽሕፈት ምንጭ ደግሞ የባቢሎናዊያን ኩኒፎርምና የግብፁ ሄሮግሊፊክ መሆናቸው የጽሕፈት ስሎቶችና የአልፋቤት ቅርጾችን በማነጻጸር ተደርሶበታል፡፡ የባቢሎኑም ኩኒፎርም ቢሆን በቅርጽ፣ በአናባቢና በተነባቢ ሁኔታ ተቀያይሮ እንጂ ከግብፅ ሄሮግሊፊክ የተቀዳ መሆኑ የታመነ ሆኗል፡፡ የአረብኛም መጻፊያ ፊደል ቢሆን የዕብራይስጥ ልጅ ነው፤ ዕብራይስጥን ሙሴ ከየት አመጣው? መልሱ ከኢትዮጵያ ወይም ከግብፅ ከሚሉ አማራጮች አይዘልም፡፡

 እዚህም ላይ አንዳንድ ምሁራን ሙሴ የተማረው ከኢትዮጵያዊው ዮቶር ስለሆን ከኢትዮጵያ ፊደል ወስዷል ሲሉ ይህንን አንቀበልም የሚሉ ደግሞ የግብጻውያኑን አጻጻፍ ዕብራዉያን ወስደው አሻሽለው ተጠቀሙበት ከማለት አይዘሉም፡፡

-ካሳሁን ዓለሙ ‹‹ኹሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ፡፡›› በሚለው ገጹ እንደከተበው

*****************************

ሰውና እባብ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በጉዞ ላይ እያለ ከአንድ ወንዝ ዳርቻ ላይ ከአንድ እባብ ጋር ተገናኘ፡፡ እባቡም ሰውየው ወንዙን እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡

ሰውየውም “እንዴት አድርጌ?” ብሎ ሲጠይቀው እባቡም “አንገትህ ላይ አድርገኝ፡፡” አለው፡፡

ሰውየው እባቡን ቢፈራውም አንገቱ ላይ አድርጎ አሻገረው፡፡

ወንዙን ከተሻገሩም በኋላ ሰውየው እባቡን “በል አሁን  ከአንገቴ  ላይ  ውረድልኝ፡፡”  ሲለው  እባቡ  ግን አልወርድም፣ እንዲያውም ወደ ዳኛ እንሂድ አለው፡፡”

ሰውየውም  በዚህ  ተስማምቶ ወደ ዳኛ ሲሄድ ዳኛው ጅብ ነበርና ጅቡ ጉዳያቸውን ካዳመጠ በኋላ እባቡን ስለፈራው “እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ፍርድ መስጠት አልችልምና ወደ ጦጣዋ ሂዱ፡፡” አላቸው፡፡ ከዚያም ወደ ጦጣዋ ዘንድ ሄደው ጉዳያቸውን ሲያቀርቡ ጦጣዋ “እሺ፣ መጀመሪያ ግን ዛፍ ላይ ልውጣ፡፡” ስትላቸው እነርሱም “እሺ” አሏት፡፡

ከዚያም ጦጣዋ “በሉ አሁን ሁለታችሁም መጀመሪያ መሬት ላይ መሆን አለባችሁ፡፡” አለቻቸው፡፡

እናም እባቡ መሬት ወረደ፡፡

በዚህ ጊዜ  ጦጣዋ ሰውየውን “ታዲያ አሁን ምን ትጠብቃለህ? በእጅህ ቢላዋ ይዘሃል፡፡ እባቡም መሬት ላይ ነው፡፡” አለችው፡፡ ሰውየውም የጦጣዋ ንግግር ስለገባው እባቡን ገደለው፡፡

-‹‹የትግራይ ተረት›› ከኢትዮጵያ ተረቶች ገጽ የተወሰደ

*****************

የሞስኮ ልዑላን

መሰንበቻውን የዓለም ስፖርት ቤተሰብ በተለይም የአትሌቲክሱ ትኩረቱና ቀልቡ አርፎ የነበረው በሞስኮው 14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ነበረ፡፡ ምንም እንኳ እንደቀደምቱ የዓለም ሻምፒዮናዎች በተመልካቾች ባይጥለቀለቅም፣ ከሞላ ጎደል በስኬት እንደተጠናቀቀ ተነግሮለታል፡፡ የወሬ ምንጮችም ይህንኑ አንፀባርቀዋል፡፡ ሻምፒዮናው ያልተለመደ እንግዳ ነገርም ተከስቶበታል፡፡ ግብረሰዶማዊ መንፈስ በተለይ በሩሲያውያት አትሌቶች ታይቷል፡፡ ከአሸናፊዎች ሰገነት ላይ ቁጢጥ ያሉቱ ሁለት እንስቶች ይህንኑ በከናፈራቸው አሳይተዋል፡፡ ከአትሌቶች ጭምር ተቃውሞም ተነስቶባቸዋል፡፡ 

ያም ሆኖ ሻምፒዮናው በተለይም ለጃማይካውያን የአጭር ርቀት ልዑላን ዩሴይን ቦልት እና ፍሬዘር ፕራይስ እጅግ ተዋጥቶላቸው አልፏል፡፡ ቦልት በ100 እና በ200 ሜትር እንዲሁም በ4x100 ሜትር የዱላ ቅብብል ተፎካካሪዎቹን ጣጥሎ የኦሊምፒክ ድሉን በተመሳሳይ በመድገም ልዑል ሆኗል፡፡ ጃማይካዊቷም እንዲሁ እንደ አገሯ ልጅ ድል በመምታት ልዕልት ሆናለች፡፡ 

ለዘመናት የአጭር ርቀቱን ተቆጣጥረውት የነበሩት አሜሪካውያን የበላይነታቸውን ካጡ እየከራረመ መምጣቱም ታይቷል፡፡ በመካከለኛና ረዥም ርቀት አውራነቱ በምሥራቅ አፍሪካውያኑ የስምጥ ሸለቆ አገሮች በኢትዮጵያና በኬንያ እጅ ሙሉ ለሙሉ እንዳይቀጥል ያደረገው ከሶማሊያ የበቀለው ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ የ5,000 እና የ10,000 ሜትር ወርቆችን እንደ ለንደን ኦሊምፒክ ሁሉ ማሸነፉ ነው፡፡ ኢትዮጵያን እንደ ኦሊምፒኩ ሁሉ በዓለም ሻምፒዮና በድል እያደመቋት ካሉት ውስጥ በመዠመርያው ረድፍ ላይ የሚገኙት መሠረት ደፋር እና ጥሩነሽ ዲባባ ናቸው፡፡ ሁለቱም በለንደን ኦሊምፒክ ያገኙትን የ5,000 ሜትር እና የ10,000 ሜትር ወርቆችን ደግመውታል፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ ክስተት የመካከለኛ ርቀት ሯጭ መሐመድ አማን  ኢትዮጵያ በታሪኳ አግኝታ የማታውቀውን የ800 ሜትር  ወርቅን በአስደናቂ ድሉ አምጥቶላታል፡፡ ሁሉም ወርቃማ አትሌቶች ኢትዮጵያንም አፍሪካንም አንግሠዋል፤አኩርተዋል፡፡