Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

ኤፖች (Ape) የምንላቸው በአፍሪካ ደኖችና በደቡብ ምሥራቅ እስያ ደኖች ውስጥ የሚገኙ ጭራ የሌላቸው የሰውና የጦጣዎች ዘመዶች ናቸው፡፡

በቀድሞ ዘመን ብዙ የኤፕ ዘመዶች በአውሮፓም ይኖሩ እንደነበር ከዚያ የሚገኙት ቅሪተ አካሎች ያረጋግጣሉ፡፡ አሁን ግን በምድር ላይ የሚገኙት በአንድ ዝርያ ውስጥ ያሉ 9 የትናንሽ ኤፖች ብቸኛ ዝርያዎችና፣ በሦስት ዝርያዎች ውስጥ የተመደቡ የትላልቅ ኤፖች ብቸኛ ዝርያዎች ብቻ ናቸው፡፡

ትላልቆቹ ኤፖች፣ የእስያው ኦራንጉታንና፣ የአፍሪካዎቹ ችምፓንዚና ጎሪላ ናቸው፡፡ ቺምፓንዚዎቹ በሁለት ብቸኛ ዝርያዎች ውስጥ ይጠቃለላሉ፡፡ አንደኛው ተራው ቺምፓንዚ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ አጭሬው ቺምፓንዚ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስለተራው ቺምፓንዚ፣ ጎሪላ እና ኡራንግኡታን ይቀርባል፡፡ 

ኤፖች በብዙ አካላዊ መዋቀሮች ከጦጣዎችና ከዝንጀሮዎች ይለያሉ፡፡ በነዚህ ልዩነቶቻቸው የተነሳ የሚመደቡት ከሰው ጋር በአንድነት፣ በአንድ ልእለ ዘመድ ነው፡፡ ከዝንጀሮዎችና ከጦጣዎች ጋር ያላቸው ዋና ዋና ልዩነት ለመጥቀስ ያህል፣ በጣም ረጃጅም ክንዶች፣ እጆችና እግሮች፣ ትልቅ አውራ ጣት፣ ሰፊ የዳሌ አጥንት፣ የብራኳ አጥንት ጀርባቸው ላይ መሆን ሰፊ ደረትና ፍርንባ ያላቸውና፣ ጅራት የሌላቸው መሆናቸው ነው፡፡

ኤፖች የደን ኗሪዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ዕፀ በልና፣ ከዕፀዋትም ቅጠልና ፍራፍሬ የሚበሉ ናቸው፡፡ ከጦጣና ዝንጀሮ ይልቅ በይበልጥ ኑሯቸው እዛፍ ላይ ነው፡፡ ታላላቅ ኤፖች ሁሉ ለመተኛትና ለእረፍት ጎጆ ይቀልሳሉ፡፡ ነገር ግን በማኅበራዊ ባህርያቸው አንዱ ብቸኛ ዝርያ ከሌላው የተለየ ነው፡፡ እያንዳንዱ ብቸኛ ዝርያ የተለየ ማኅበራዊ አደረጃጀት፣ የወንድና የሴት ሥርዓት ልዩነትና፣ የቡድን አሠራር አለው፡፡ እያንዳንዳቸው መጠናቸው ትላልቅ ስለሆነ፣ የሕይወት ዘመናቸውና የእርግዝናቸው ዕድሜ ረጃጅም ነው፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ የሚወልዱት አንድ ልጅ ብቻ ሲሆን፣ የእርግዝና ጊዜያቸው ከው ተመሳሳይ ነው፡፡

-ሰሎሞን ይርጋ ‹‹አጥቢዎች››(2000)