መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ማህበራዊ - ጨጨብሳ (ለ4 ሰው)
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

10 የቡና ስኒ (ግማሽ ኪሎ ግራም) የጤፍ ዱቄት

ግማሽ የሻይ ማንኪያ የዳቦ ቅመም

ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ጨው

ግማሽ የሾርባ ማንኪያ አዋዜ

10 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ

አዘገጃጀት

1.ዱቄቱን በደንብ መንፋት፤

2.የዳቦ ቅመሙን፣ ጨውንና ዱቄቱን በደረቁ በደንብ መቀላቀል፤

3.በትንሽ፣ በትንሹ ውኃ እየጨመሩ እንዳይጓጉል ተጠንቅቆ ማቡካት፤

4.ቀጠን እንዲል አድርጐ አዋህዶ ማቡካት፤

5.በደንብ ከተዋሃደ በኋላ የእንጀራ ምጣድ ላይ መጋገር፤

6.እያገላበጡ ድርቅ እስኪል ማብሰል፤

7.አውጥቶ ቀዝቀዝ ሲል በትንሹ መቆራረስ፤

8.ቅቤውንና አዋዜውን መጥበሻ ላይ ማቅለጥ፤

9.ላዩ ላይ የተቆራረሰውን ቂጣ ጨምሮ ማገላበጥና ቀዝቀዝ ሲል ለገበታ ማቅረብ፡፡

(ከላይ የተሠራውን ዓይነት ጨጨብሳ በገብስ፣ በስንዴ፣ በአጃ፣ በፍርኖ ዱቄት ማዘጋጀት ይቻላል፡፡) 

-ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)