መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ማህበራዊ - የቀረሶ ዓሳ ጥብስ (ለ1 ሰው)
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
15 September 2013 ተጻፈ በ 

የቀረሶ ዓሳ ጥብስ (ለ1 ሰው)

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

1 በደንብ ፀድቶ በሎሚና በቁንዶ በርበሬ የተለወሰ የቀረሶ ዓሳ 

 

ግማሽ ሊትር ዘይት 

1 ሎሚ (መለወሻ)

1 የቡና ስኒ የፍርኖ ዱቄት 

ግማሽ ሎሚ (ገበታ የሚቀርብ)

1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ (መለወሻ) 

1 የሻይ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት

1.የሎሚ ጭማቂና ቁንዶ በርበሬ ደባልቆ ዓሳውን መቀባት (መለወስ)፤

2.የፉርኖ ዱቄትና ጨውን ደባልቆ ላዩ ላይ ማገላበጥ፤

3.ዱቄቱን አራግፎ መካከለኛ ሙቀት ባለው በጣም ያልጋለ ዘይት ውስጥ በዝግታ መጥበስ፤

4.ቀንበር (ደረቅ) ሲል እያወጡ ወንፊ መሰል ነገር ላይ ወይም የወጥ ቤት ወረቀት ላይ ማድረግ፤

5.ከሎሚው ጋር ማቅረብ፤

[የወጥ ቤት ወረቀት ማለት የኬክ መጠቅለያ ወይም ቅባት መቋቋም የሚችል ወረቀት ማለት ነው፡፡ ዓሳውን የጠበስንበትንም ዘይት አጥልለን ማስቀመጥና ለሌሎች የዓሳ ዝግጅቶች መጠቀም እንችላለን፡፡]

-ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)