መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ማህበራዊ - ልዩ ልዩ ዳቦ
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online

ልዩ ልዩ የዳቦ ዓይነቶች ለማዘጋጀት የሚውለው ሊጥ አንድ ዓይነት ሲሆን፣ ዳቦዎቹ የሚለያዩትም በሚጨመርባቸው የቅመም ዓይነቶች ብቻ ነው፡፡


ለዳቦዎቹ ሊጥ መሥሪያነት የሚውሉ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
•    7 ጆግ (5 ኪሎ ግራም) የፉርኖ ዱቄት
•    2 የሾርባ ማንኪያ እርሾ
•    5 የሾርባ ማንኪያ ስኳር
•    3 የሾርባ ማንኪያ ጨው
•    2 የሾርባ ማንኪያ የዳቦ ቅመም

አዘገጃጀት
1.    እርሾውን ለብ ያለ ውሃ ውስጥ መጨመር፤
2.    አንድ የሾርባ ማንኪያ ስኳር ጨምሮ ማማሰል፤
3.    እርሾው ተበጥብጦ ኩፍ ሲል ዱቄቱ ላይ ጨምሮ ትንሽ ለብ ባለ ውሃ የዳቦ ቅመሙን፣ ጨውንና ቀሪውን ስኳር ቀላቅሎ እየደጋገሙ ማሸት፤
4.    እንዲቦካ መተውና እንዳይጠቁር በጨርቅ መሸፈን፤
5.    በደንብ መቡካቱ ሲታወቅ ሶስቴ ማሸት፤
6.    ሊጡ በጣም እንዳይወፍር ወይም እንዳይቀጥን መጠንቀቅ፡፡
[በዚህ መልኩ የተዘጋጀ ሊጥ በሚከተለው ዘዴ ለአምስቱም የዳቦ ዓይነቶች መሥሪያነት ሊውል ይችላል]

ሀ. የጦስኝ ዳቦ
አዘገጃጀት
1.    ከላይ የተዘጋጀው ሊጥ ላይ አንድ የቡና ስኒ ንፁህ አረንጓዴ ጦስኝ መነስነስና አብሮ ማቡካት፤
2.    ኮባ የተነጠፈበት መጋገሪያ ላይ መጠፍጠፍና ኩፍ እንዲል መተው፤
3.    በጣም ተነስቶ ሳይጨርስ መጋገርና በጥንቃቄ ማውጣት፡፡

ለ. የዘቢብ ዳቦ
አዘገጃጀት
1.    አንድ የቡና ስኒ (150 ግራም) ዘቢብ ቀደም ሲል ከተዘጋጀው ሊጥ ጋር መቀላቀል፤
2.    ወዲያው መጠፍጠፍና ትንሽ ኩፍ ሲል መጋገር፡፡
[ዘቢብ ውስጥ ውሃ ስላለ ሊጡ ከላይ ከተጨመረ በኋላ ሲል ወዲያውኑ መጋገር ያስፈልጋል፡፡]
ደብረወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)