መነሻ ገጽ - ሌሎች አምዶች - ማህበራዊ ጉዳዮች - ወጣት - ኢትዮጵያ - ከቢልቦርድ ምርጥ 40ዎች አንዷ
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
21 August 2013 ተጻፈ በ 

ኢትዮጵያ - ከቢልቦርድ ምርጥ 40ዎች አንዷ

ወይዘሪት ኢትዮጵያ ሀብተ ማርያም መስከረም 1972 ዓ.ም. ላይ ነው የተወለደችው፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት ኩባንያዎች ውስጥ ትልቁ በሆነውና የዩኒቨርሳል ሙዚቃ ቡድን አካል በሆነው ሞታውን ሙዚቃ አሳታሚ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናት፡፡

በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነቷም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሱ አፍሪካ-አሜሪካውያት መካከል አንዷ ለመሆን እንዳበቃት ቢልቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች መሰንበቻውን ዘግበውላታል፡፡  

ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት ደረጃ አስተዋጽኦ ካደረጉት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ፣ ታዋቂና ታላላቅ የሆኑ የሙዚቃ ሰዎች ሥራዎችን ለማሳተም በመወሰኗ ነው፡፡ ከእነዚህ ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ውስጥ የመልቲ ፕላቲኒየምና የግራሚ ሽልማት አሸናፊ የሆነው አርቲስትና የዘፈን ደራሲ ክሪስ ብራውን፣ የዘፈን ደራሲዋና አቀንቃኟ ኬሪ ሂልሰን፣ ባለ ጎልድ ሪከርዲንግና የዘፈን ደራሲ የሆነችው አቀንቃኟ ሲያራ ይገኙበታል፡፡ 

በተጨማሪም በራዲዮ ወይም በቴሌቪዥን የሙዚቃ ሥራዎችን በሚያሰራጭ ተቋም (ሕዝብ ካዳመጣቸው በኋላ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው ወደ ትልቅ ደረጃና ሽያጭ እንዲደርስ ምክንያት የሆነ ተቋም) አማካይነት የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ደራሲና የዓመቱ ምርጥ አዘጋጅ ተብለው ለመሰየም የበቁ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሥራዎች እንዲታተሙ በማድረግ፣ ሙያዊ ብቃታቸው ወደ ስኬት እንዲያመራ ምክንያት ሆናላቸዋለች፡፡ 

ከእነዚህ ስኬታማ የሙዚቃ ሰዎች መካከል ፖሎው ዳ ዶን፣ አንድሬ ሜሪት፣ ካንደስ ኔልሰን፣ ባሌዋ ሙሐመድ፣ እዝቅኤል ሊዊስ፣ ሮኪ ሲቲ እንዲሁም ብራያን ኬኔዲ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ 

ኢትዮጵያ የቢልቦርድ ምርጥ 40 ሰዎች ውስጥ አንዷ ሆና ተመርጣለች፡፡ እርሷም ለተጎናጸፈችው ስኬቷ ተጨማሪ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ እንዲሁ፣ የባለ መልቲ ፕላቲኒየም ሪከርዲንግና የግራሚ ሽልማት አሸናፊ የሆኑት የእነ ሜሪጂ ብላይጅ፣ ፊፍቲ ሴንት፣ ኤሚኒየም፣ ጄርሚ፣ አሜሪ፣ አሻንቲ፣ ጂል ስካት፣ ፕሪንስ፣ ኒኮል ሼርዚንገር፣ አይስ ኪዮብ፣ ራፋኤል ሳዲቅ፣ ስዊዝ ቢትዝ፣ ዲ ኤም ኤክስ፣ አሸር ሮዝ፣ ቢስታይ ቦይስ፣ አር ኬሊ፣ ቤቢ ፌስና ኪይሻ ኮል ሥራዎች ለሕትመት በቅተው ዓለም ላይ ላሉ አድናቂዎቻቸው ጆሮ ዘንድ እንዲደርሱ የበኩሏን በማድረጓ ነው፡፡ 

አትላንታ የተወለደችው ኢትዮጵያ የሙዚቃ አሳታሚ ኩባንያዎች ውስጥ እግሯ መርገጥ የጀመረው ገና የ14 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር፡፡ ከዚያም ቀጥላ እኤአ በ2001 ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ኤድመንደ ሙዚቃ አሳታሚ ውስጥ ክሬቲቭ ማናጀር በመሆን አገልግላለች፡፡ ይህ በሆነ ከሁለት ዓመታት በኋላ ዩኒቨርሳል ሙዚቃ አሳታሚ ቡድን ለኢትዮጵያ ባደረገላት ጥሪ መሠረት ጥሪውን ተቀብላ እስካሁን ድረስ እያገለገለች ሲሆን አስር ዓመትም ሞልቷታል፡፡ 

ሙዚቃዎች እንዲታተሙ የመወሰንና ምርጥ ሽያጭ ሊያስገኙ የሚችሉ ዘፈኖችን የመምረጥ ችሎታ አላት የተባለላት ኢትዮጵያ፣ ሞታውን ማግኔት ሆኖ ወጣት አርቲስቶችን የሚስብና ወጣት ሙዚቃ አድማጮችን መሠረት ያደረገ የንግድ ተቋም እንዲሆን አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑ እየተነገራለት ነው፡፡