Skip to main content
x

አገርን ወደ ብጥብጥ መውሰድ አሸናፊም ተሸናፊም የማይኖርበት ውድመት ነው!

አገርን ወደ ብጥብጥ ለመግፋት የሚደረጉ አሳዛኝ ጥረቶች በስፋት ይታያሉ፡፡ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ ድረስ የተሠለፉ ኃይሎች መነሻቸውም መድረሻቸውም የሕዝብ አጀንዳ ባለመሆኑ፣ አገሪቱን የማያባራ ቀውስ ውስጥ ለመክተት ይሯሯጣሉ፡፡ ለመንግሥት ሥልጣን ከሚደረገው ሽኩቻ ጀምሮ ብሔርተኝነትን በማራገብ፣ የሕዝብን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ለመናድ የሚደረጉ ጥረቶች በአሳዛኝ ሁኔታ ቀጥለዋል፡፡

መንግሥት የሚከበረው ሕዝብን አክብሮ ሲያስከብር ነው!

ሕዝብና መንግሥት ሆድና ጀርባ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው የግልጽነት መጥፋት ነው፡፡ ግልጽነት ሲጠፋ መተማመን አይኖርም፡፡ መተማመን በሌለበት መከባበር አይታሰብም፡፡ መከባበር ከቤተሰብ ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ጎረቤት ተሻግሮ ወደ ማኅበረሰቡ ይደርሳል፡፡ በዚህ መሠረት መራመድ ሲቻል በአገር ደረጃ መከባበር ባህል ይሆናል፡፡

የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ግዴታ ነው!

ኢትዮጵያውያን በመረጡበት ሥፍራ የመኖር፣ የመሥራት፣ የመዘዋወርና ሀብት የማፍራት መብታቸው በሕግ የተረጋገጠ ቢሆንም ተግባራዊ ባለመሆኑ ብቻ፣ በበርካታ ዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ በደል ተፈጽሟል፡፡ ዜጎች በገዛ አገራቸው ‹‹መጤ›› እየተባሉ ጥቃት ሲፈጸምባቸው፣ ሲፈናቀሉና ሲገደሉ በተደጋጋሚ ጊዜያት ታይቷል፡፡

ለአገር የሚያስፈልጋት የጋራ ኃላፊነት ነው!

ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ከምንም ነገር በላይ የሚያሳስባቸው የአገር ጉዳይ ነው፡፡ የአገር ህልውና የጥቂቶች ጉዳይ ሳይሆን የመላው ሕዝብ ነው፡፡ የጋራ ኃላፊነት የሚመነጨውም በእኩይ ድርጊቶች ሳቢያ የአገር ህልውና እንዳይናጋ ነው፡፡ የአገር ጉዳይ ደንታ የማይሰጣቸው ነውጠኞች ካገኙት ጋር እየተላተሙ አቧራ ሲያስነሱ፣ የአገራቸው ሰላምና ደኅንነት የሚያሳስባቸው ደግሞ በአንድነት በመቆም መከላከል ታሪካዊ ግዴታቸው ነው፡፡

አገር መተዳደር ያለባት በሕግ የበላይነት ሥር ብቻ ነው!

በማንኛውም አገር የመንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነት የሕግ የበላይነትን ማስከበር ነው፡፡ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን የያዙ መንግሥታት ከምንም ነገር በፊት የሚያስቀድሙት የሕግ የበላይነትን ነው፡፡ የሕግ የበላይነት የሚጠቅመው ጠንካራ፣ አስተማማኝና ዘለቄታዊነት ያለው ሥርዓት ለመገንባት ነው፡፡ አምባገነኖች ደግሞ ሕግን በሚመቻቸው መንገድ ቀርፀው ሕገወጥነት የሥልጣናቸው መጠበቂያ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

አገር የግለሰቦች መፈንጫ አትሁን!

የሕግ የበላይነት ባለበት ማንም ሰው ከሕግ በላይ መሆን አይችልም፡፡ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ሕግ ሲጥሱና ራሳቸውን ከሕግ በላይ ሲያደርጉ ግን አገርን ያመሰቃቅላሉ፡፡ ሕገወጥነት እንዲስፋፋና ሥርዓተ አልበኝነት እንዲነግሥ ያደርጋሉ፡፡ በሕገ መንግሥት አማካይነት የቆመ ሥርዓት ሳይቀር ከማፈራረስ አይመለሱም፡፡

ሕዝብን መበጥበጥ ይብቃ!

አሁንም የሰው ክቡር ሕይወት እየተቀጠፈ ነው፡፡ የአካል ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡ ንብረት እየወደመ ነው፡፡ ሰላማዊና ሥልጡን የፖለቲካ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው ችግሮች ገጽታቸውን እየቀያየሩ ሰላምና መረጋጋት እየጠፋ ነው፡፡ ባልታሰበ አጋጣሚ የሆነ ሥፍራ ሁከት ይቀሰቀስና የንፁኃን ሕይወት እንደ ዋዛ ያልፋል፡፡ በዚህ መሀል ሕዝብ ግራ ይጋባል፡፡

አገርንና ሕዝብን የሚያተራምሱ ታሪክ ይፋረዳቸዋል!

እጅግ በጣም ክቡር የሆነው የሰው ሕይወት አሁንም በከንቱ እየጠፋ ነው፡፡ ንፁኃን በሚያሳዝን ሁኔታ እየሞቱ ባሉበት በዚህ አሳዛኝ ጊዜ የሚያሳስበው ምን ያህል ሞቱ የሚለው አይደለም፡፡ ይልቁንም የአንድም ሰው ሕይወት ለምን ለአደጋ ይጋለጣል የሚለው ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊያሳስብ ይገባል፡፡ በከንቱ የሚፈሰው የንፁኃን ደም ያሳምማል፡፡ እያንዳንዱ ቀን መሽቶ እስኪነጋ ድረስ ለሰላም ወዳዱና ለአርቆ አስተዋዩ ሕዝብ እየከበደው ነው፡፡

በሴራ ፖለቲካ አገር አይታመስ!

ግልጽነት በሌለበት አገር በርካታ ብሔራዊ ጉዳዮች ሚስጥር ይሆናሉ፡፡ ሚስጥራዊነት በበዛ ቁጥር እውነቱን ከሐሰት፣ ተጨባጩን ከምናባዊው መለየት ስለማይቻል መላምቶች ይበዛሉ፡፡ የመረጃ ፍሰቱ የተገደበ ስለሚሆንም ሐሜትና አሉባልታ የበላይነቱን ይይዛሉ፡፡ አሁን በኢትዮጵያ የተንሠራፋው ችግር ይህ ነው፡፡

ከአገርና ከሕዝብ በላይ ምንም ነገር የለም!

የአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ትኩሳት ከአገርና ከሕዝብ ዘለቄታዊ ህልውና ጋር ሲነፃፀር፣ በግራ መጋባትና በውዥንብሮች መሞላቱ ግልጽ ነው፡፡ በተለይ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች መካከል መቃቃር ተፈጥሯል ተብሎ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ መሰነባበቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በቀናት ልዩነት ውስጥ የድርጅቱ ነባር አመራሮች ከያዙት ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው መሰማቱ በድርጅቱ ታሪክ አዲስ ቢሆንም፣ በአባል ድርጅቶች መካከል የነበረው መስተጋብር ግን እንደ በፊቱ እንዳልሆነ ግን ግልጽ እየሆነ ለመምጣቱ ሌላው ማሳያ ነው፡፡