Skip to main content
x

የጥቁር ገበያ ነጋዴዎች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መታየት የጀመረው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡ በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ መላ ካልተበጀለት አዝማሚያው እንደሚያሠጋ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው፡፡ ለገበያ አለመረጋጋትና ለምርት እጥረት ሰበብ የሆኑ፣ ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎች መባባስ ተከስቷል፡፡ ለዚህ ድርጊት በርካታ ጉዳዮች ሊመዘዙ እንደሚችሉ ቢታመንም፣ ሰው ሠራሽ ችግሮች የሚፈጥሩት ጫና ግን ከፍተኛ ነው፡፡

የሸቀጥ ዋጋ አይዋጋ

ከሰሞኑ የወጣው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ፣ የሚያዝያ ወር የዋጋ ግሽበት 13.7 በመቶ ማስመዝገቡን ያሳያል፡፡ ይህ ስታትስቲካዊ ስሌትንና ንጽጽርን መሠረት ያደረገ አሐዝ ነው፡፡ ገበያው ግን ከተጠቀሰውም በላይ የዋጋ ለውጥ ሊያሳይ ይችላል፤ እያሳየም ነው፡፡ የኤጀንሲው መረጃ እንዳለ ሆኖ፣ በተጨባጭ የምናየው እውነታ አሳሳቢ የዋጋ ለውጥ እየታየ ስለመሆኑ የሚጠቁም ነው፡፡

ዳቦ ያሳጡ አንጀት ይልጡ

መንግሥት መሠረታዊ የሚባሉ እንደ ስንዴ፣ ዱቄት፣ ዳቦ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት ምርቶችን ሥርጭትና ግብይት በመቆጣጠር እንዲገበያዩ ያደርጋል፡፡  ይህን የሚያደርገውም እንዲህ ያሉትን መሠረታዊ ሸቀጦች በዋጋ እየደጎመ ማቅረቡን በመከራከሪያነት በማቅረብ ነው፡፡ ለዓመታት በዚህ መንገድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ የድጎማ አሠራር በዚህ መንገድ እንዲካሄድ ታምኖበት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

ኢምባሲዎቻችን የውጭ ምንዛሪ እጥረቱን ለመቅረፍ ምን እየሠሩ ነው?

ስለአንድነትና ስለኢትዮጵያዊነት እየሰማን ነው፡፡ ስለፍቅርና ይቅር ባይነትም ሰምተናል፡፡ አንድ እንሁን አንድነታችን ‹‹ተደምሮ›› ወደ መልካም ጐዳና ይወስደናል የሚል መልዕክት ያላቸው አንደበቶችን ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በተደጋጋሚ እየሰማን ነው፡፡

የአዲሱ ካቢኔ አሮጌ ችግሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ ለሕዝብ ባደረጓቸው ንግግሮች በርካታ ጉዳዮችን ዳሰዋል፡፡ መንግሥታቸው በአፋጣኝ ይመልሳቸዋል በማለት ከጠቃቀሷቸው ጉዳዮች ውስጥ የአገልግሎት አሰጣጡን የተመለከተ ውል ይገኝበታል፡፡

የ‹‹ጥሪ›› ዋጋ

በበዓላት ዋዜማ ሰሞን የገበያ ድባብን የሚያመላክቱ መረጃዎችን መገናኛ ብዙኃን ሲዘግቡ እንመለከታለን፡፡  ለበዓል የሚሰናዱ ምግቦችን ለማሰናዳት የሚያስፈልጉ እንደ ቅቤ፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ ሥጋ የመሳሰሉትን ግብዓቶች በተመለከተ ስለዋጋቸው፣ ስለ አቅርቦታቸውና ስለመሳሰለው ጉዳይ በየዘገባው ለማመላከት ይሞከራል፡፡ ከቀደመው ጊዜ ዋጋቸው ጋር በማመሳከር አድማጮች፣ ተመልካቾችና አንባቢዎች መረጃ እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡

በኢኮኖሚው ዙሪያ አሁንም ጥያቄ አለ

የዶ/ር ዓብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በአገሪቱ ፖለቲካዊ ታሪክ ጉልህ ሥፍራ ተሰጥቷቸው ከሚታወሱ ክሰተቶች መካከል አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የእሳቸው አመጣጥና እዚህ ቦታ መድረስ ብዙ ሊያነጋግር ይችላል፡፡ ቢሆንም ሰላማዊ ሽግግር የተፈጸመበት፣ በግድም ይሆን በውድ የእሳቸውን መሾም ያረጋገጡት መራጮቻቸው ብቻ ሳይሆኑ ውጤቱን ተቀብለው የሥልጣን ሽግግሩ እንዲካሄድ ያደረጉት ሁሉ ናቸው የሚለውን አስተያየትም መቀበል ግድ ይላል፡፡

ለሕዝብ ጥያቄ ሕዝባዊ ምላሽ!

ለሦስት ዓመታት የአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት አይሎ፣ ዕጣ ፈንታዋ ምን ይሆን ብሎ ለመተንበይም አስቸጋሪም አስፈሪም እስከመሆን ደርሶ ቆየ፡፡ የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ አባል ድርጅቶች የእርስ በርስ ሽኩቻ ይዘዋል የሚለው ወሬ በገሃድም፣ በሹክሹክታም ሲወራ በመሰንበቱ የዚህ ነገር መቋጫው ምን ይሆን? በማለት ምጥ ያልያዘው አለ ማለት ይከብዳል፡፡

ሕግ ያልገዛቸው ሻጮች

ኢትዮጵያ በዕዝ የኢኮኖሚ ሥርዓት ትመራ የነበረበትን የደርግ መንግሥትን  የግብይት ልማድ የሚያስታውሱ ገጠመኞች በተደጋጋሚ መመልከት ጀምሬያለሁ፡፡ በ1970ዎቹ አጋማሽ መሠረታዊ ሸቀጦች በአብዛኛው ለሸማቹ ይደርሱ የነበረው በቀበሌ የኅብረት ሱቆች በኩል ነበር፡፡ ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ስኳርና ዱቄት የሬዲዮ ባትሪ ድንጋይ ሳይቀር ከቀበሌ የኅብረት ሱቅ በራሽን መግዛት ግድ ይል ነበር፡፡ በወቅቱ ስኳርና ፓስታ መሠረታዊ ሸቀጥ ነበር፡፡