Skip to main content
x

የቻይና ጎዳናዎችን ያጥለቀለቀው ‹‹ሕገወጥ›› የአትሌቶች ጉዞና ተሳትፎ

ኢትዮጵያ በዓለም የስፖርት መድረክ ከፍ ብላ ከምትታወቅባቸው ኩነቶች ዋነኛው አትሌቲክስ ነው፡፡ ይህ የዘርፍ ምንም እንኳ በበርካታ ወርቃማ ድሎች የታጀበና አገሪቱም ቀና ብላ ከምትታወቅባቸው መድረኮች አንዱ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ውጤታማና ስኬታማ ነው ማለት እንደማይቻል የሚናገሩ አሉ፡፡

መረን የወጡ የኳስ ሜዳ አምባጓሮዎች እስከ መቼ?

የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ በክልል ከተሞች በስታዲየሞች መረን የወጡና ምክንያታዊ ያልሆኑ አምቧጓሮዎችና ውርጅብኞች በርካቶችን ‹‹እግሬን በሰበረው›› ማሰኘት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ደጋፊዎች ችግሮች እንኳ ቢኖሩ ሰከን ብለው መፍትሔውን ከመሻት ይልቅ ክቡር ለሆነው የሰው ልጆች ሕይወትና ንብረት ውድመት ምክንያት እየሆኑ ይገኛል፡፡

126 ሺሕ ኪሎ ሜትር የሚጓዘው የዓለም ዋንጫ የካቲት 17 አዲስ አበባ ይገባል

ብዙዎች የሚመኙት፣ ነገር ግን ጥቂቶች በአራት ዓመት አንድ ጊዜ የሚታደሙበት የዓለም ዋንጫ ዝግጅት በብዙ ውጣ ውረድ የአዘጋጅነቱን ዕድል ባገኘችው ሩሲያ በመጪው ክረምት ይካሄዳል፡፡ በእግር ኳሱ 32 የዓለም ኃያላን የሚፎካከሩበት የዓለም ዋንጫ፣ ከዚያ በፊት ከ50 በላይ አገሮች እንዲጎበኝ በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት ቅዳሜ የካቲት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል፡፡ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ጉብኝት፣ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአሥር አገሮች የጉብኝት ፕሮግራም ተይዞለታል፡፡ የአዘጋጇ ሩሲያ 35 ከተሞችን ጨምሮ ከ50 በላይ በተመረጡ የዓለም አገሮች ይንቀሳቀሳል ተብሏል፡፡

ፊፋ የአስመራጭ ኮሚቴውን ክስ ውድቅ አደረገው

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ)፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያላፀደቀው የፊፋ የምርጫ ሕግ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል በማረጋገጥ፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ ያቀረቡለትን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ጥር 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴሬሽኑ በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ምርጫውንም ፌዴሬሽኑ በራሱ ደንብ እንዲያከናውን አሳስቧል፡፡

ሕጋዊ  አመራር በሌለው ተቋም ስለፍትሕ ማውራት ለማን?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበላይነት ከሚመራቸው ሊጎች መካከል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፤ ከፍተኛ (ሱፐር) ሊግ  እና ብሔራዊ ሊግ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በሁሉም ሊጎች  በጨዋታ ዳኞች ሊሆን ይችላል፣ በሚከሰቱ ስህተቶች ምክንያት የሚደመጡ አስተያየቶችና ትችቶች ከሙያ ሥነ ምግባር ያፈነገጡ እየሆኑ ቀላል የማይባል ጥፋት እያስከተለ ይገኛል፡፡ የክለብ አመራሮችና አሠልጣኞች በተለይ ውጤት ሲርቃቸው ከሙያ ሥነ ምግባር ያፈነገጡ ከፋፋይ አስተያየቶችን ጊዜያዊ መሸሸጊያ ካደረጉት ሰነባብተዋል፡፡

ሦስተኛው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተጀመረ

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች የሚያከናወነውንና ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ገንዘቤ ዲባባና ሐጎስ ገብረ ሕይወት በ1,500 ሜትርና በ3,000 ሜትር አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

የክለብ ምሥረታ ጅምር ስኬት እንደማይሆን ከብርሃንና ሰላም በላይ ምስክር ከየት?

በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች በትልቁ ትኩረት ከሚሰጡት እግር ኳስ ጀምሮ ሌሎችም ስፖርቶች በኢትዮጵያ ሲመሠረቱ እንዴትና ለምን እንዲሁም በምን ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ እንደሚቋቋሙ ብቻ ሳይሆን፣ ተጠያቂነትም ስለሌለው የፈረሱ ቡድኖችና ክለቦች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ይታመናል፡፡ እንዲያውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‹‹አፈርሳለሁ›› የሚለው ቃል ክለብ አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት ሳይቀር ማስፈራሪያ እስከመሆን መድረሱ እየታየና እየተሰማ ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ኢትዮጵያን አደነቀ

የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም በዚሁ እያስመዘገበች ያለውን ውጤት አደነቀ፡፡ አገሪቱ ለዋዳ ፀረ አበረታች ቅመሞች ዘመቻና ለሦስትዮሽ ፕሮግራሞች ትክክለኛ ማሳያ መሆኗን የዋዳ ምክትል ዳይሬክተር ሮበርት ኮህለር ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ፣ ኢትዮጵያ በተለይ በአትሌቲክሱ ዓለም ላይ ያላትን የበላይነት ግምት ውስጥ በማስገባት አበረታች ቅመኞች በይበልጥ ይመለከታቸዋል በሚል ለይቶ ካስቀመጣቸው አምስት አገሮች አንዷ አድርጎ ሲመለከታት ቆይቷል፡፡ በዚሁ መነሻነት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ችግሩን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ፣ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት በማቋቋም እንቅስቃሴ ስታደርግ መቆየቷ አይዘነጋም፡፡