መነሻ ገጽ - ስፖርት - ፈይሴ ታደሰ የፓሪስ ማራቶን ቁንጮ ሆነች
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
10 April 2013 ተጻፈ በ 

ፈይሴ ታደሰ የፓሪስ ማራቶን ቁንጮ ሆነች

ባለፈው እሑድ ፈረንሣይ ውስጥ በተካሔደው 37ኛው የፓሪስ ማራቶን በሴቶች ምድብ ፈይሴ ታደሰ ባለ ድል ሆናለች፡፡ መሪማ መሐመድና ድንቅነሽ ተፈራ ኬንያዊቷን ኦይኒስ ኪርዋን ከመሃላቸው በማስገባት ሁለተኛና አራተኛ ሆነው መፈጸማቸውን ዶቸ ቬሌ ዘግቧል፡፡

በወንዶች ኬንያዊው ፔተር ሶሜ ሲያሸንፍ፣ ያጠናቀቀበት ጊዜም 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ ነበር፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት የፓሪስ ማራቶንን ያሸነፈውና ዘንድሮም ድሉን ይደግማል  ተብሎ የተጠበቀው ታደሰ ቶላ ሁለተኛ ሲሆን፣ ሌላው ኬንያዊ ኤሪክ እንዲየማ  በሦስተኛነት ፈጽሟል፡፡

ዘገባው፣ በፓሪሱ ማራቶን በወንዶች ባጫ መገርሣ፣ ሣህሌ ዋርጋ፣ አብርሃም ግርማና ገዛኸኝ ዓለማየሁ ፤ እንዲሁም  በሴቶች ድንቅነሽ ተፈራና ፋንቱ ጂማ ከመጀመሪያዎቹ አሥር ፈጣን ሯጮች መካከል መሆናቸው የኢትዮጵያን አትሌቶች ጥንካሬ ያመለከተ ነበር ብሏል።

በሌላ በኩልም በሳምንቱ መጨረሻ በቼክ ሬፑብሊክ መዲና ፕራግ በተካሔደው  ግማሽ ማራቶን ሩጫ በወንዶች ኤርትራውያን  ዘረሰናይ ታደሰና አማኑኤል መሰል አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ሲያሸንፉ፣ ኬንያዊው ጆን ኪፕሳንግ ሦስተኛነቱን ወስዷል፡፡ በሴቶች ኬንያዊቷ ግሌዲይስ ቼሬኖ ስታሸንፍ ወርቅነሽ ደገፋ ሩጫውን በሁለተኝነት መፈጸሟን ዶቼ ቬሌ ዘግቧል፡፡