መነሻ ገጽ - ስፖርት - ቅዱስ ጊዮርጊስ አሠልጣኙን አሰናበተ
Buy Valtrex Online Buy Albuterol inhaler Online Buy Prinivil Online
28 August 2013 ተጻፈ በ 

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሠልጣኙን አሰናበተ

-ቡድኑ እሑድ ከቱኒዚያ ሲፋክሴን ጋር ይጫወታል

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጀርመናዊውን አሠልጣኝ ሚሸል ክሩገርን ማሰናበቱ ተሰማ፡፡

ቡድኑ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቱኒዚያው ሴፋክሴን ጋር ለመጫወት ዓርብ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡ 

ክለቡ አምና ለዘንድሮው የውድድር ዓመት በሚዘጋጅበት ወቅት እንዲያሠለጥኑት ለሁለት ዓመት ኮንትራት የፈረሙት ክሩገር አንድ ዓመት ቢቀራቸውም አሰናብቷቸዋል፡፡ ሰበቡም ከሁለት ሳምንት በፊት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሴፋክሴን አስተናግዶ በሜዳውና በደጋፊው ፊት 3ለ1 በመሸነፉ ነው፡፡ በወቅቱ የክለቡ ደጋፊዎች የጀርመናዊውን አሠልጣኝ ስም እየጠሩ ‹‹ይውጡልን›› በሚል ተቃውሞ ድምፅ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ 

አሠልጣኙ አንድ ዓመት ኮንትራት እየቀራቸው እንዴት ሰንብቱን ተቀበሉ? ለሚለው፣ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተረፈ አምበርብር ክለቡና አሠልጣኙ በጉዳዩ ተግባብተው የተስማሙበት ስንብት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከስምንቱ ጠንካራ ክለቦች አንዱ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሴፋክሴን ምንም እንኳ 3ለ1 ቢሸነፍም በመልስ ጨዋታ ውጤቱን ለመገልበጥ እንደሚጫወት እምነታቸው መሆኑን የሚናገሩ የክለቡ ደጋፊዎች አሉ፡፡ ቡድኑ ከነገ በስቲያ ወደ ቱኒዚያ አምርቶ እሑድ የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል፡፡ 

የጀርመናዊው አሠልጣኝ ምክትል ሆኖ የቆየው ፋሲል ተካልኝ በበኩሉ፣ የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋቾች በቅጣትና ጉዳት ተሟልተው አለመገኘታቸው ክፍተቱን የጎላ ቢያደርገውም፣ በቀሩት ልጆች የቻልነውን ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ብሏል፡፡ 

እንደ ምክትል አሠልጣኙ፣ በቅጣት ከቡድኑ እንደማይካተቱ ከሚታወቁት በረኛው ሮበርት ኦዱካራ፣ ተከላካዩ ኤልያስ ቢያድግልኝ፣ ከፊት መስመር አዳነ ግርማና ኡመድ ኡክሪ በሁለት ቢጫ ከጨዋታው ውጪ ናቸው፡፡ አሉላ ግርማ ደግሞ በጉዳት ሌላው ከቡድኑ ከማይካተቱት ስለመሆኑ ጭምር ተናግሯል፡፡