Skip to main content
x

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት ውድመት ሪፖርት እየተጠናቀቀ ነው

በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ምክንያት የደረሰውን ውድመት የሚያጣራው ቡድን ሪፖርት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከሁለቱም ክልሎች ከ900 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ መጠኑ የማይታወቅ ንብረት ወድሟል፡፡

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሥራ አስኪያጅና ሠራተኞች ገዳዮችን ለመያዝ ከፍተኛ አሰሳ እየተካሄደ ነው

ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ አሥር ሰዓት ላይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊና ሾፌር ገዳዮችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ አሰሳ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ማኔጀር ተገደሉ

የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲፕ ካማራ ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. አሥር ሰዓት ላይ ከጸሐፊያቸውና ከሾፌራቸው ጋር ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ 85 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ረጂ በተባለ አካባቢ በሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ መገደላቸው ተሰማ፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ላይ የተጠናቀረውን ሪፖርት ለማቅረብ የፓርላማው ጥሪ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ባጋጠመው የዜጎች መፈናቀል ወቅት የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ያጠናከረውን ሪፖርት ይፋ ለማድረግ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪን እየጠበቀ እንደሆነ ዋና ኮሚሽነሩ አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር)  አስታወቁ፡፡

በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር ውይይት ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር፣ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያቋረጠውን ውይይት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የከተማውን ደረቅ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ የገነባው የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ምክንያት ሥራ በጀመረ በሰባት ወሩ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ይታወሳል፡፡

የሚድሮክ ወርቅ ቀውስ እንደቀጠለ ነው

የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በለገደንቢ ወርቅ ማውጫ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ኩባንያው በአካባቢያችንና ጤናችን ላይ ጉዳት አድርሶብናል በማለት ባነሱት ተቃውሞ ምክንያት የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የኩባንያውን የማዕድን ምርት ፈቃድ አግዷል፡፡

በሶማሌ ክልል በጎርፍ ምክንያት 98 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ

በሚያዝያ ወር በተደረገ ጥናት በሶማሌ ክልል በሸበሌ ዞን 165 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች በጎርፍ መጠቃታቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ 98 ሺሕ ያህል ሰዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በዚህ ሳምንት በወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት፣ በክልሉ በተከሰተው ጎርፍ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ አምስት ሺሕ ቤቶች መውደማቸውን፣ በሸበሌ ዞን የሚገኙ 72 ትምህርት ቤቶችና 63 የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡

በሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ደረሰ

ከወራት በኋላ እንደገና ባገረሸው የሞያሌ የሰላም መደፍረስ መጠነ ሰፊ የሆነ ግጭት ተከስቶ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡ ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር በተመሳሳይ በዚሁ የድንበር ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት፣ ዘጠኝ ንፁኃን ተገድለው ሌሎችም መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ ተወሰነላቸው

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ፣ ገቢውም የክልሎች እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የምክር ቤቱ የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2010 ዓ.ም. መደበኛ ጉባዔውን ላካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳስታወቀው፣ በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ የፌዴራል መንግሥት ግብር በመጣል ገቢውን ለራሱ መሰብሰቡ ከሕገ መንግሥቱ የሚቃረን በመሆኑ፣ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢውን የመጣልና የመሰብሰብ ሥልጣን ለክልሎች እንዲሆን በመንግሥት ደረጃ መወሰኑን አመልክቷል፡፡